2010–2019 (እ.አ.አ)
መንግስትህ ይምጣ
ኤፕረል 2015


15:32

መንግስትህ ይምጣ

መንግስቱን በምድር ላይ ለመመስረት የሚያደርገውን ታዕምራቶች ማየት እና ማመን የጌታ እጅ በህይወታችን ውስጥ እንደሚሰራ ለማየትና ለማመን ለመቻል ይረዳናል።

ስንዘምር፣ በ200 አገሮች ውስጥ በ75 በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ብዙ ሺህ አባላት 1አብረን ድምጻችንን ወደ እግዚአብሄር በማድረግ ይህን መዝመራችንን ሳስብበት በስሜት እነካለሁ፥

ና፣ አንተ የንጉሶች ንጉስ!

ለረጅም ጊዜ እንጥብቅሀለን፣

በክንድህ ፍወሳ ይዘህ፣

ህዝብህን ነጻ ለማድረግ።2

ና፣ አንተ የንጉሶች ንጉስ! 3 እኛ የአለም አቀፍ የሚያምኑ የትልቅ ቤተሰብ ክፍል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶች ነን።

ስሙን በራሳችን ላይ ወስደናል፣ እናም በየሳምንቱም ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ እርሱን ለማስታወስ እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን። ከፍጹም የራቅን ነን፣ ነገር ግን በእምነታችን ትሁት ነን። እናምነዋለን። እናመልከዋለን። እንከተለዋለን። በዝልቅ እናፈቅረዋለን። ከአለም ሁሉ ታላቅ የሆነው ስራ የእርሱ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች፣ በዘመናት በሙሉ ለረጅም ጊዜ በሚያምኑት በጉጉት በሚጠበቀው፣ የጌታ ዳግም ምፅዓት በፊት በሆኑት ቀናት እየኖርን ነን።በጦር እና በጦር ወሬ ቀናት፣ በፍጥረት መአቶች ቀናት፣ አለም በመምታታት እና በብጥበጣ በሚጎተትበት ቀናት ውስጥ እንኖራለን።

ነገር ግን ወንጌል ለአለም በሙሉ በሚወሰድበት፣ ጌታ “በጻድቅነት እና በእግዚአብሔር ሀይል”4 የሚያሳጥቃቸውና “ንጹህ ህዝብ አነሳለሁ” ብሎ ቃል በገባበት በአስደናቂ በዳግም መመለስ ዘመንም እንኖራለን።5

በእነዚህ ቀናት እንደሰታለን፣ እናም ትግላችንን እና እርግጠኛ አለመሆናችንን በብርታት ለመቋቋም እንድንችልም እንፀልያለን። አንዳንድ ችግሮች ከሌሎች የበለጡ ናቸው፣ ነገር ግን ሁሉም ችግር ያጋጥማቸዋል። ሽማግሌ ኒል ኤ፣ ማክስዌል እንዳሉት፣ “አሁን ሁሉም ነገሮች በፍጹምነት የሚካሄዱላችሁ ከሆኑ፣ ጠብቁ።” ይህም ሟችነታችን ነው።

ምንም እንኳን ጌታ “እንዳንፈራ”6 በተደጋጋሚ እንድንረጋገጥ ቢያደርግም፣ በፈተናዎች መካከል እያለን ከዚህ አለም አሳልፎ የሚመለከት አስተያየት ማግኘት ቀላል አይደለም።

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን የዘለአለማዊ አስተያት ስለመኖር በጣም አስፈላጊ ትምህርት አስተምረውኛል።

ከስምንት አመት በፊት ከፕሬዘደንት ሞንሰን ጋር በባቡር በስዊዘርላንድ ስንጓዝ፣ ስለከባዱ ሀላፊነታቸው ጠየቅኳቸው። መልሳቸው እምነቴን አጠናከረው። ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዲህ አሉ፣ “በቀዳሚ አመራር ውስጥ፣ ይህን ስራ ወደፊት ለመግፋት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። ነገር ግን ይህ የጌታ ስራ ነው። ይህን ይመራል። እርሱም ይህን ይቆጣጠራል። ለመክፈት የማንችለውን በሮች ሲከፍት እና ለማከናወን የማንችላቸውን ታዕምራቶችን ሲያከናውን ስንመለከት እንደነቃለን።”7

ወንድሞች እና እህቶች፣ መንግስቱን በምድር ላይ ለመመስረት የሚያደርገውን ታዕምራቶች ማየት እና ማመን የጌታ እጅ በህይወታችን ውስጥ እንደሚሰራ ለማየትና ለማመን ለመቻል ይረዳናል።

ጌታ እንዳወጀው፣ “የራሴን ስራ ለማከናወን እችላለሁ።”8 እያንዳንዳችን ክፍላችንን ለማድረግ እንጥራለን፣ ነገር ግን እርሱ ዋናው ፈጣሪው ነው። በአባቱ አመራር፣ አለምን ፈጠረ። “ሁሉም ነገሮች በእርሱ ነበር የተሰሩት፤ እናም ያለእርሱ የተሰራው ሁኑ ምንም አይሰራም።”9 በመንፈስ ስንነሳና ስንነቃ፣ በአለም ውስጥ እጁን እናያለን እናም በግል ህይወታችንም እጁን እናያለን።

ምሳሌ ልስጣችሁ።

በ1831 (እ.አ.አ)፣ በ600 የቤተክርስቲያኗ አባላት ብቻ፣ ጌታ እንዲህ አወጀ፣ “በምድርም ለሰው የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎችም ተሰጥተዋል፣ እናም ከዚህም ወንጌሉ ፣ እጅም ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ፣ ወደ ምድር ዳርቻምይገፋል።”10

ነቢዩ ኔፊ ከአለም ህዝብ ጋር ሲመዛዘኑ የቤተክርስቲያኗ አባላት “ትንሽ” እንድሚሆኑ ነገር ግን “በምድር ፊት በሙሉ” እንደሚሆኑ አስቀድሞ ተመልክቶ ነበር።11

የጌታ እጅ መንግስቱን የሚመሰርትባቸው ሶስት ምሳሌዎች ዛሬ ያስተዋወቋቸው ቤተመቅደሶች ናቸው። ከጥቂት አመታት በፊት፣ በሄቲ፣ በታይላንድ እና በአይቭሪ ኮስት ቤተመቅደሶች ይገነባሉ ብሎ ማን አሰበ?

የቤተመቅደስ ቦታዎች በጂኦግራፊ ስምምነት የሚወሰንበት አይደለም። ይህም የሚከናወነውን ታላቅ ስራ እና በትውልዶች ቤቱን የሚንከባከቡና እንደ ቅርስ የሚመለከቱትን ቅዱሳን ጻድቅነትን በማሳየት የሚመጣው በራዕይ በኩል በነቢይ ነው።12

Thomas S. Monson of the Quorum of the Twelve Apostles, visiting Haiti.  On April 17, 1983 he dedicated Haiti for the preaching of the gospel and also dedicated a site for the first meetinghouse to be built in Haiti.  It was the first visit to the island by a member of the Quorum of the Twelve.  (Ensign Aug. 1983, p. 79; Church News, May 22, 1983, p. 4)
A group of Missionaries with Elder Andersen

ባለቤቴ ካቲ እና እኔ ሄቲን ከሁለት አመት በፊት ጎብኝተን ነበር። ፖርት-ኦ-ፕሪንስን አሳልፎ በሚመለከት ተራራ ላይ፣ ከሄቲ ቅዱሳን ጋር አገሩ በሽማግሌ ቶማስ ኤስ ሞንሰን ከ30 አመት በፊት የተቀደሰበትን ቀን ለማክበር አብረን ተገኘን። በ2010 (እ.አ.አ) የነበረውን ደምሳሺ የምድር መናወጥን ማናችንንም አንረሳም። በታማኝ አባላት እና ብርቱ ከሆኑ ከሄቲ ከመጡ የሚስዮን ቡድኖች ጋር በዚህች ደሴት አገር የምትገኘው ቤተክርስቲያን በማደግና በመጠናከር ቀጥላለች። ነጭ ለብሰው፣ የጌታን ቤት ለማስተዳደር እና ቅዱስ ስርአቶትን ለማከናወን የቅዱስ ክህነት ሀይል እያላቸው እነዚህን የእግዚኣብሄርን ቅዱሳን ፃድቅነት በአዕምሮዬ ስመለከት፣ እምነቴ ከፍ ይላል።

Sathit and Juthamas Kaivaivatana of Bangkok Thailand.
President Kaivaivatana and other members of the Thailand Bangkok Thailand North Stake leadership..

የጌታን ቤት በወብታማዋ ባንኮክ ከተማ ውስጥ ማን አስቦበት ነበር ቡዳን በሚያመኩበት በታይላንድ አገር ውስጥ ክርስቲያኖች አንድ ከመቶ የሚሆኑ ናቸው።፡እንደ ሄቲ፣ ጌታ የባንኮክ የምድር ተመራጮችን ሰብስቧል። ከጥቂት ወራት በፊት በዚያ እያለን፣ ከሳቲት እና ከጌው ኪያቫልቫታና እና ከታማኝ ልጆቻቸው ጋር ተገናኘን። ሳቲት የቤተክርስቲያኗ አባል የሆነው በ17 አመቱ ነበር እናም በአገሩ እንደሚስዮንነት አገለገለ። በኋላም ከጌው ጋር በሀይማኖት ትምህርት ቤት ውስት ተገናኘ፣ እናም በማኒላ ቤተመቅደስ ውስጥ ታተሙ። በ1993 (እ.አ.አ) የኪያቫልቫታና ቤተሰብ እንቅልፍ በያእው መኪና ነጂ ተገጩ። ሳቲት ከደረቱ በታች ደነዘዘ። እምነታቸው ምንም አለተወላወለም። ሳቲት በባንኮክ ኢንተርናሲዮናል ትምህርት ቤት ውስጥ አስደናቂ አስተማሪ ነው።፡በታይላንድ ባንኮክ ሰሜን ካስማ እንደ ፕሬዘደንት ያገለግላል። የእግዚአብሔር ታዕምራት በስራው እና በግል ህይወታችን ውስጥ አሉ።

Couples in the Ivory Coast

በአይቭሪ ኮስት ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን ታዕምራት ሁለት የተጋቡ ሰዎች ስም ሳይጠቀም ለመነገር አይቻልም፥ ፊልፕና አነሊስ አሳርድ እና ሉሲንና አገት አፉኢ። የቤተክርስቲያኗ አባል የሆኑት አንዶቹ በጀርመን እና ሌላው በፈረንሳይ በመጋባታቸው ወጣትነታቸው ነበር። በ1980 (እ.አ.አ)፣ ሳይተዋወቁ፣ ፊልፕና ሉሲን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ወደ አፍሪካ አገራቸው በመመለስ እንደሚሳቡ ይሰማቸው ነበር። በጀርመን የሚኖሩት እህት አሳርድ ቤተሰባቸውን ለመተው እና ወንድም አሳርድ ብዙ የሚያከናውኑበትን የኢንጅነር ስራን ትተው እንዲሄዱ መፍቀድ በጣም ልዩ የሆነ እምነት ያስፈል ነበር። እነዚህ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በአይቭሪ ኮስት ውስጥ ነበር እናም የሰንበት ትምህርትን ጀመሩ። ያም ከ30 አመት በፊት ነበር። አሁን ስምንት ካስማዎች እና ከ27 ሺህ በላይ የሆኑ አባላት በዚህ በሚያስደንቀው የአፍሪካ አገር ውስጥ ይገኛሉ። የአፉኢ ቤተሰብ አሁንም በክድር ያገለግላሉ፣ በቅርብ በአካር ጋና ቤተመቅደስ ውስጥ አገልግሎታቸውን የፈጸሙት የአሳርድ ቤተሰብም እንዲሁ እያደረጉ ናቸው።

የእግዚአብሔር እጅ ስራውን ወደፊት ሲገፋ ለመመልከት ትችላላሁ?የጌታን እጅ በሄቲ ውስጥ ባሉት ሚስዮኖች ወይም በታይላንድ ውስጥ ባሉት በኪያቫልቫታና ህይወት ላይ ለመመልከት ትችላላሁን። የእግዚአብሔርን እጅ በአሳርድና በአፉኢ ህይወት ውስጥ ለመመልከት ትችላልችሁን? የእግዚአብሔርን እጅ በህይወታችሁ ለመመልከት ትችላላችሁን?

“በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ካለመመስከር … በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም።”13

የእግዚአብሔር ታዕምራት በሄቲ፣ በታይላንድ፣ ወይም በአይቭሪ ኮስት ብቻ የሚሆኑ አይደሉም።14 በአካባቢያችሁ ተመልከቱ። እጁ በዚያም አለ። “እግዚአብሔር … ለህዝቦቹ ያስባል፤ አዎን፣ ህዝቡን ያስባል፣ እናም ከአንጀቱ ምህረትን ሲያደርግ በምድር ላይ ሁሉ ይሆናል።”15

አንዳንዴ የጌታ እጅን በሌሎች ህይወት ውስጥ እንመለከታለን፣ ግን “እጁን በራሴ ህይወት ውስጥ በተጨማሪ ለመመልከት እንዴት እችላለሁ?” ብለን እንገረማለን።

አዳኝ እንዲህ አለ

“አትጠራጠሩ”16

“አትፍሩ”17

“[ከ]ድንቢጦች አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። …

“እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።”18

በጠላት ሲከበብ ወደነቢዩ ኤልያስ ስላለቀሰው ወጣት እናስታውስ፥ “ወዮ! ምን እናደርጋለን?”19

ኤልያስም እንዲህ መለሰ፥

“ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ”

“ኤልሳዕም፣ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ ተራራው በፈረሶች እና የእሳት ሰረጌላዎች ተሞልቶ አየም።”20

የጌታን እጅ በህይወታችሁ ለመመልከት ትእዛዛትን ስትጠብቁና በእምነት ስትጸልዩ፣ የመንፈስ አይናችሁን በተጨማሪም ይከፍትላችኋል፣ እናም ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ በግልጽ ትመለከታላችሁ።

ቅዱስ መጻህፍት እንደሚያስተምሩን “ወደፊት በሚመጣው እምነት ፀንታችሁ ቁሙ።”21 ምን ይመጣል? አዳኝ እንደጸለየው፥

“በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤

“መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን።”22

ሁላችንም “ና፣ አንተ የንጉሶች ንጉስ” የሚለውን ዘምረናል።

የአዳኝ ወደ ምድር መመለስን ስንጠብቅ እምነታችን ያድጋል። የእርሱ መምጣት ሀሳብ ነፍሴን ያነሳሳዋል። አስደናቂ ይሆናል። ሀሳቡና ታላቅነቱ፣ እና አስደናቂነቱ ሟች አይኖች ካዩት ወይም ካጋጠማቸው ምንም ነገር በላይ የሚበልጥ ይሆናል።

በዚያ ቀን፣ በጨርቅ ተጨቅልሎ በግርግም ላይ ተኝቶ አይመጣም፣23 ነገር ግን “በሀይልና በሰማይ ደመና፣ በታላቅ ክብር [ተሸፍኖ]፣ ከሁሉም ቅዱሳን መላእክት ጋር” ይመጣል።24 “የመላእክት አለቃን ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት” እንሰማለን።25 ጸሀይ እና ጨረቃ ይቀየራሉ፣ እናም “ከዋክብትም ከስፍራቸው ይወረወራሉ።”26 እናንተ እና እኔ፣ ወይም ከእኛ በኋላ የሚመጡት፣ “ቅዱሳንም ከአራቱ የምድር ማዕዘናት፣”27 “በቅምጸት ይለወጣሉ እና እርሱን ያገኑት ዘንድም ይነጠቃሉ።”28 በጻድቅነት የሚቱትም፣ “እነርሱ ደግመውም በሰማይ አዕማድ መካከል … ይነጠቃሉ።”29

ከዚያም፣ ለመታሰብ ከሚቻል በላይ የሆነ ያጋጥማል፥ ጌታ እንዳለው “ስጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ያዩኛል።”30 ይህ እንዴት ይሆናል? አናውቅም። ነገርግ ግን እንደተተነበየበትይሆናል። በአምልኮ እንንበረከካለን። “ጌታም ድምጹን ያሰማል፣ እናም የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይሰሙታል።”31 “እንደ ብዙ ውሀዎች ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ይሰማል።”32 “ጌታ፣ እንዲሁም አዳኝ፣ በህዝቡ መካከል ይቆማል።”33

ከዚያም የሰማይ መላእክት እና ቅዱሳን በምድር ላይ የሚገናኙበት ይመጣል።34 ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስፈላጊ፣ ኢሳይያስ እንዳወጀም፣ “በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ፣”35 እናም “ስጋ ለባሽ ሁሉ መካከል ይነግሳል።”36

በዚያም ቀን፣ ተጠራጣሪዎች ጸጥተኛ ይሆናሉ፣ ክርስቶስ ኢየሱስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የአለም አዳኝ እና ቤዛ እንደሆነ “ሁሉም ጆሮዎች ይሰሙታልና፣ … ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል መላስም ሁሉ ይናዘዛል።”37

ዛሬ ፋሲካ ነው። በአለም አቀፍ ካሉ ክርስቲያኖች ጋር በግርማዊ ትንሳኤው እና በተስፋ ቃል በተሰጥን ከሞት መነሳትም እንደሰታለን። ከምናፈቅራቸው ጋር እነዚህን ግርማዊ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ በመገምገም እንዘጋጅ፣ እናም መንግስትህ ትምጣ። “ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን።” የሚለው ፀሎቱም የእኛ ይሁን። እርሱ ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ፣ ”ና፣ አንተ የንጉሶች ንጉስ።”38 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. አጠቃላይ ጉባኤ በ94 ቋንቋዎች ቢተረጎምም፣ ሁሉም ቋንቋዎች ጉባኤው በሚከናወንበት ጊዜ ወይም ሁሉም የጉባኤ ስብሰባዎች የሚተላለፉ አይደሉም። ለዚህ አጠቃላይ ጉባኤ የእሁድ ከሰዓት በኋላ ስብሰባ፣ 75 ቋንቋዎች ጉባኤው በሚከናወንበት ጊዜ ይተላለፋሉ።

  2. “ና, ኦ አንተ የንጉሶች ንጉስ፣” Hymns, no. 59.

  3. በማክሰኞ፣ መጋቢት 31፣ 2015 (እ.አ.አ)፣ የቀዳሚ አመራር ቢሮ በሚያዝያ 5 እሁድ ከሰዓት በኋላ ስብሰባ ላይ የተሰበሰቡት “ና፣ ኦ አንተ የንጉሶች ንጉስ” የሚለውንመዝሙር ከዘመሩ በኋላ ንግግር እንደማደርግ ኢሜል ልከውልኝ ነበር። በፓርሊ ፒ. ፕራት የተጻፈው የዚህ ታላቅ የዳግም መመለስ መዝሙር አዳኝ ወደ ምድር እንዲመለስ በትሁት የሚለመንበት ነው። ከምንዘምራቸው ሌሎች መዝሙሮች በላይ ይህ የጉባኤ መልእክቴን በግልጽ የሚያሳይ ነው። በሁሉም ቦታ የሚገኙ ቅዱሳን አብረው በዚህ በፋሲካ ቀን በአንድነት ድምጻችንን ከፍ አድርገን “ና፣ ኦ አንተ የንጉሶች ንጉስ፣ አንተን ለረጅም ጊዜ ጠብቀናል” በማለት ስንዘምር፣ ልቤን በዝልቅ ነክቶታል። ለአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ምን መዝሙር እንደሚዘመር እኔ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለኝ በማወቅ፣ “መንግስትህ ትምጣ” የሚል ርዕስ ያለውን ንግግሬን መዝሙር የሚመርጡት አንብበውት ስለአዳኝ ዳግም ምፅዓት መዝሙር መርጠው እንደሆነ በሀሳቤ መጣ። በኋላም የታበርናክል ዘማሪዎች መሪ ይህን መዝሙር ለቀዳሚ አመራር በሀሳብ ያቀረቡት ንግግሮ ለቀዳሚ አመራር እንዲተረጎም ከመላኬ ሳምንቶች በፊት በመጋቢት መጀመሪያ ላይ እንደሆነ አወቅሁኝ። “ና፣ ኦ አንተ የንጉሶች ንጉስ” የሚለውንመዝሙር ባለፈ ጊዜ በአጠቃላይ ጉባኤ የተዘመረው በጥቅምት 2002 (እ.አ.አ) ነበር። ሁላችንም ክፍላችንን ለማከናወን እንጥራለን፣ ነገር ግን እርሱ ታላቁ ነዳፊ ነው።

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100፥16.

  5. 1 ኔፊ 14፥14.

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥55.

  7. የግል አጋጣሚ, ግንቦት 1997.

  8. 2 ኔፊ 27፥20.

  9. ዮሀንስ 1፥3.

  10. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥2.

  11. 1 ኔፊ 14፥12.

  12. በ2011 (እ.አ.አ) ክረምት፣ በብራዚል እየኖርኩኝ እያለሁ፣ መረጃዎቹን ለፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ ይነግሯቸዋል ብዬ ተስፋ እያለኝ፣ ለቀዳሚ አመራር አባል ፕሬዘደንት ጄምስ ኢ. ፋውስት በጉጉት በቹሪቲባ ከተማ ውስጥ ስለሚኖሩት ቅዱሳን አስደናቂ ነገሮችን ነገርኳቸው። ፕሬዘደንት ፋውስት ከመጨረሴ በፊት አቆሙኝ። “ኒል፣ፕሬዘደንትን አናግባባም። ቤተመቅደስ የሚገነባበት ውሳኔ በጌታ እና በነቢዩ መካከል ነው”አሉኝ። የቹሪቲባ ብራዚል ቤተመቅደስ በ2008 (እ.አ.አ) ተቀደሰ።

  13. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥21.

  14. ከጌታ እጅ ታላቅ ታዕምራቶች አንዱ መንግስቶ በዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ በእያንዳንዱ ጋዛቶች ከተማዎች እና መንደሮች ውስጥ መንግስቱ መሰራጨቱ ነው። በግንቦት 2006 (እ.አ.አ) በዴንተን ቴክሳስ የካስማ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዳደር ተመድቤ ነበር። በካስማው ፕሬዘደንት፣ ፕሬዘደንት ቯን ኤ. አንድረስ ቤት ውስጥ ቆይቼ ነበር። እህት አንድረስ በዴንተን ስለነበሩ የመጀመሪያ ቤተክርስቲያም፣ በወላጆቻቸው በጆን እና ማርጋሬት ፖርተር በመጀመር፣ ነገሩኝ። በመጀመሪያ የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት ብቻ ነበር። ነገር ግንየፖርተር ቤተሰብ ወንጌሉን ከራግስዴል ቤተሰብ ጋር ተካፈሉ፣ እነርሱም ከኖብል እና ማርቲኖስ ቤተሰቦች ጋር ተካፈሉ። ሚስዮኖች አስፈላጊ ሀላፊነታቸውንም በእርግጥ አከናውነዋል። ብዙ ቤተሰቦች የቤተክርስቲያኗ አባል ሆኑ። ሌሎችም ከምዕራብ ወደ ዴንተን መጡ። ዛሬ፣ ትንሽ ቅርንጫፍ በነበረበት ቦታ ውስጥ፣ አራት ካስማዎች አሉ፣እና በ16 አመቱ የሜተክርስቲያኗ አባል የሆነው ከማርቲንኖ ወንድ ልጆች አንዱም፣ ሽማግሌ ጄምስ ቢ. ማርቲኖ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ባለስልጣን አሁንም ያገለግላሉ።

  15. አልማ 26፥37.

  16. ማቴዎስ 21፥21.

  17. ማርቆስ ፥36.

  18. ማቴዎስ 10፥29, 31.

  19. 2 ነገስት 6፥15.

  20. 2 ነገስት 6፥16–17.

  21. ሞዛያ 4፥11.

  22. ማቴዎስ 6፥9–10፥ ደግሞ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥6 ተመልከቱ

  23. ሉቃስ 2፥12.

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥44.

  25. 1 ተሰሌንቆ 4፥16.

  26. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥49.

  27. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥46.

  28. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥96.

  29. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥97.

  30. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥23.

  31. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥49.

  32. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥22.

  33. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥25.

  34. ሙሴ 7፥63 ተመልከቱ

  35. ኢሳያስ 52፥10.

  36. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥25.

  37. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥104.

  38. ማቴዎስ 6፥10.