2010–2019 (እ.አ.አ)
የወንጌል ዘለአለማዊ ገጽታ
ኤፕረል 2015


10:45

የወንጌል ዘለአለማዊ ገጽታ

ዘላለማዊነትን ለሚለውጡ ውሳኔዎች የወንጌል ዘላለማዊ ገፅታን መኖር አስፈላጊ ነው።

ለሙሴ በተሰጠው ራዕይ፣ የሰማይአባታችን ለማወጅ ያሰበውን እንዲህ ተነግሮናል፤ “እነሆ፣ የሰውን ሟች አለመሆን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ለማምጣት፣ ይህ የእኔ ስራ እና ክብር ነው።”1 በዚያ አርፍተነገር መሰረት፣ ለሁሉም ሙሉ ደስታ የመቀበል እድልን መስጠት የአብ ፍላጎት ነው። የኋለኛው ቀን መገለጦች የሚገልጹት የሰማይ አባታችን ታልቅ የደስታ እቅድ ለሁሉም ልጆቹ እንደፈጠረ፣ በጣም ልዩ የሆነው እቅዱ ከእርሱ ጋር ለመኖር እንድንመለስ ነው።

ይህንን የደስታ እቅድ መረዳት ዘለአለማዊ ገጽታን ያቀርብልናል እና ትእዛዛቱን፣ ስርአቱን፣ ቃልኪዳኑን፣ ፈተናዎችእናመከራዎችንእውነተኛዋጋእንድንሰጥይረዳናል።

አንዱ ቁልፍ መርህ ከአልማ የመጣ ነው፤ “ስለዚህ እግዚአብሔር የቤዛነት እቅድ ማዘጋጀቱን እንዲያውቁ ካደረገ በኋላ፣ መጥፎ እንዳይሰሩ ትእዛዛትን ሰጣቸው።”2

የማስተማር ሂደቱን የጊዜ ደረጃ ማጤን አስደሳች ነው። የሰማይ አባታችን የቤዛነት እቅድን መጀመሪያ ለአዳም እና ሔዋን አስተማረ እና ከዛም ትእዛዛትን ሰጣቸው።

ይሄ ታላቅ እውነት ነው። እቅዱን መረዳት ሰዎች ትእዛዛትን እንዲጠብቁ፣ የተሻሉ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ እና ትክክለኛ መነሳሻዎች እንዲኖራቸው ይረዳል።

በቤተክርስቲያን ባገለገልኩበት ጊዜ፣ በተለያዩ አገራት የቤተክርስቲያን አባላትን መሰጠት እና እምነት ተመልክቻለሁ፣ አንዳንዶቹ ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግጭቶች አሉባቸው። በእነዚህ ታማኝ አባላት ውስጥ በብዛት ያጋጠመኝ የጋራ ነገር እነርሱ ያላቸው ዘለአለማዊ ገጽታ ነው። የወንጌል ዘለአለማዊ ገጽታ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የምንሸፍነውን ቦታ እንድንረዳ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንድንቀበል እና በእነሱ አማካኝነት እንድናድግ፣ ውሳኔዎችን እንድንወስን፣ እና በመለኮታዊ አቅማችን ላይ ህይወታችንን ወደ መመስረት ይመራናል።

ገጽታ ነገሮችን በተወሰነ እርቀት ላይ ስንመለከት የምናይበት መንገድ ነው፣ እና በእውነተኛ ዋጋቸው እንድንደሰት ይፈቅድልናል።

ልክ ጫካ ውስጥ ሆኖ ከዛፍ ፊትለፊት እንደመሆን ነው። ወደ ኋላ ራመድ ካላልን በቀር፣ ጫካ በእውነት ምን እንደሆነ ልንረዳ አንችልም። በብራዚል እና ፔሩ ድንበሮች አጠገብ የሚገኘውን፣ በለቲሺያ ውስጥ የአማዞንን ደን አንዴ ጎብኝቼ ነበር። በላዩ ላይ እስክበር እና ገጽታውን እስካገኝ ድረስ ልደሰትበት አልቻልኩ ምነበር።

ልጆቻችን ትንሽ ሳሉ፣ ምንድነው የሚታያችሁ? የሚል በቴሌቪዢን ጣቢያ የሚተላለፈውን ዝግጅት ይመለከቱ ነበር። ቪዲዮው አንድ ምስልን በጣም አቅርቦ ያሳያል እና በቴሌቪዢን መስኮቱ ላይ ያለው ምስል ቀስ በቀስ እየሰፋ ሲሄድ ልጆቹ ምን እንደሆነ መገመት ነበረባቸው። እቃው ሙሉ ለሙሉ መታየት ሲጀምር፣ ድመት፣ ተክል፣ ፍሬ፣ ወዘተ እንደነበር በቀላሉ መናገር ይቻላል።

በአንድ ሁኔታ ያንን ዝግጅት ሲመለከቱ አስታውሳለሁ እና በጣም አቅርቦ አንድ በጣም ለነሱ የሚያስጠላ ዘጊ የሚመስል ነገርን አሳየ፤ ነገር ግን ምስሉ እየሰፋ ሲመጣ፣ በጣም የሚያጓጋ ፒዛ እንደነበረ አስተዋሉ። ከዛ ለእኔ እንዲህ አሉ፣ “አባዬ፣ ልክ እንደዛ ያለውን አንድ ግዛልን!” ምን እንደነበረ ከተረዱ በኋላ፣ ለእነርሱ በመጀመሪያ የማያስደስት መስሎ የታየው ነገር መጨረሻ ላይ በጣም የሚስብ ነገር ሆነ።

ሌላ ተሞክሮ ላካፍላችሁ። በቤታችን ውስጥ ልጆቻችን ምስል በመገጣጠም መጫወት ይወዱ ነበር። ምን አልባት ሁላችንም በመገጣጠም የመጫወት እድሉ ነበረን። አንዳንዶቹ ከብዙ ትንንሽ ቁርጥራጮች የተሰሩ ናቸው።አንዱ ልጃችን (ማንነቱን ለመጠበቅ ስሙን አልጠቅስም) በእያንዳንዱ ቁራጭ ላይ ትኩረት ያደርግ እንደነበር አስታውሳለሁ፣ እና አንዱ ባሰብው ቦታ ላይ አልገባ ሲል፣ ይናደዳል እና ያም ጥሩ እናዳልሆነ ያስባል እና ሊወረውረው ይፈልጋል። በመጨረሻም፣ እያንዳንዱ ትንሽ ቁራጭ በተወሰነ ጊዜያት እንደሚገጥም ባያውቅም፣ በመጨረሻው ምስል ውስጥ ቦታ እንዳለው ሲረዳ ጨዋታውን ለመደ።

ይሄ የጌታን እቅድ የማሰላሰያ አንዱ መንገድ ነው። በተናጠል በእያንዳንዱ ክፍሎች እራሳችንን ማሳሰብ የለብንም ነገር ግን በምትኩ ሙሉ ምስሉን ወደ ትኩረት ለማምጣት መሞከር ነው፣ የመጨረሻ ውጤቱ ምን እንደ ሚሆን በማሰብ። በእቅዱ ላይ እንዲገጥም እያንዳንዱ ቁራጭ የት መሆን እንዳለበት ጌታ ያውቃል። በታላቁ የደስታ እቅድ መሰረት ሁሉም ትእዛዛት ዘለአለማዊ ጠቀሜታ አላቸው።

ዘለአለማዊ ዋጋ ያላቸውን ውሳኔዎች ከሟችነት ገጽታ ያለመወሰናችን በጣም አስፈላጊ ነው። ዘለአለማዊ ተጽእኖ ላላቸው ውሳኔዎች፣ የወንጌል ምልከታ መኖሩ ወሳኝ ነው።

ሽማግሌ ኔይል ኤ. ማክስዌል እንዳስተማሩት፤ “በታላቅ እና መሰረታዊ ተስፋ ብንደገፍም፣ አንዳንድ የብልህ አሰራር ተስፋችን ሌላጉዳዮች ናቸው። ለደሞዝ እድገት፣ ልዩ ለሆነ የፍቅር ቀጠሮ፣ በምርጫ ለማሸነፍ፣ ወይም ለትልቅ ቤት-- ለሚስተዋሉ ወይም ለማይስተዋሉ ነገሮች ተስፋ እናደርግ ይሆናል። በአባታችን እቅድ ማመን በተጨማደደ የአጭር ጊዜ ተስፋ ውስጥም ቢሆን ጽናት ይሰጠናል። ቀሊል መንስኤ በሚመስል ሁኔታ ቢቀርብም ለመልካም መንስኤ ተጠምደን በመስራት እንድንቆይ ያደርጋል ( ት. እና ቃ. 58፥27)።3

ዘለአለማዊ ምልከታ ያለመኖር ወይም ማጣት ምድራዊ ምልከታን እንደ የግል ደረጃችን እንዲሆን እና ከእግዚአብሔር ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ውሳኔ እንድናደርግ ያደርጋል።

ኔፊ ስለነበረው ባህሪይ እና ስለላማን እና ልሙኤል ባህሪ መጽሐፈ ሞርሞን ይጠቅሳል። ሁሉም በበርካታ ስቃዮች እና ችግር ተሰቃይተዋል፤ ቢሆንም፣ ስለስቃዮች የነበራቸው አመለካከት በጣም የተለያየ ነበር። ኔፊ እንዲህ አለ፣ “እናም የጌታ በረከት በእኛ ላይ ታላቅ ስለነበር በምድረ በዳ ውስጥ ለመኖር ስንል ጥሬ ስጋ ስንበላ ሴቶቻችን ልጆቻቸውን በበቂ ሁኔታ አጠቡአቸው፤ እናም እነርሱ ጠንካራ ነበሩ፣ አዎን፣ ልክ እንደ ወንዶቹ ካለምንም ማጉረምረም ጉዞአቸውን በትዕግስት ጀመሩ።”4

ላማን እና ልሙኤል፣ በሌላ ጎኑ፣ በመሪሩ አጉረመረሙ። “እናም ላማን እና ልሙኤል ታላቅ በመሆናቸው በአባታቸው ላይ አጉረመረሙ። እና ይህንን ያደረጉት የዚያን የፈጠራቸውን አምላክ ስራ ስላላወቁ ነው።”5 “የእግዚአብሔርን ስራ” ባለማወቅ ወይም ትኩረት ባለመስጠት፣ “በምድረበዳው ውስጥ ለእነዚህ በርካታ ዓመታት ተንከራተትን፤ እናም ሴቶቻችንም እርጉዝ በነበሩበት ጊዜ ለፉ፣ እናም በምድረበዳ ውስጥ ልጆችን ወለዱ፣ እናም ከሞት በስተቀር በሁሉም ነገሮች ተሰቃዩ፤ እናም በእነዚህ ነገሮች ከመሰቃየት ከኢየሩሳሌም ሳይወጡ ቢሞቱ ይሻል ነበር” በማለት ጮሁ።6

እነዚያ ሁለት በጣም የተለያዩ ባህሪያት ነበሩ፣ ያጋጠሙአቸው ችግሮች እና ስቃዮች ተመሳሳይ ቢሆኑም እንኳ። በእርግጥ፣ ምልከታቸው የተለያየ ነበር።

ፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል የሚከተለውን ጻፉ፤ “ሟችነትን እንደ ሙሉ ህይወት አድርገን ካየነው፣ ከዛም ህመም፣ ሀዘን፣ ውድቀት፣ እና ስህተት፣ ጥፋት ይሆን ነበር። ነገር ግን ሕይወትን ከቅድመ ምድራዊ ሕይወት እስከ ሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወት እንዳለ እንደ ዘላለማዊ ነገር ከተመለከትናት፣ ሁሉም ክስተቶች በተገቢው ምልከታ ውስጥ ይቀመጥ ይሆናል።”7

ሽማግሌ ዴቪድ ቢ ሄይት ነገሮችን በተገቢው ምልከታ የማየትን አስፈላጊነት ለማብራራት የቀራጩን ሚካኤል አንጀሎን ታሪክ ተናገሩ፤“ቀራጩ የእምነበረድ ማእዘኑን ሲቀርጽ፣ አንድ ልጅ በየቀኑ እየመጣ እና እያፈረ ይመለከታል። የዴቪድ ምስል ሲቀርብ እና ከድንጋዩ ሲወጣ፣ ለአለም መገረም ሲጠናቀቅ፣ ልጁ ሚካኤል አንጀሎን ጠየቀ፣ ‘እዚያ ውስጥ እንደነበር እንዴት አወቅክ?’”8

የእብነበረዱን ማእዘን ቀራጩ ያየው እና ሲሰራ ይመለከት የነበረው ልጅ ምልከታቸው የተለያየ ነበር። በድንጋዩ የሚሆነውን አቅሞች ላይ የአርቲስቱ ራእይ የጥበብ ስራ እንዲፈጥር አስቻለው።

ጌታ በእያንዳንዳችን ማሳካት የሚፈልገውን ያውቃል። በህይወታችን ልናሳካ የሚገባውን አይነት ለውጥ ያውቃል፣ እና ልንመክረው መብቱ የለንም። ሀሳቡ ከሀሳባችን በላይ ነው።9

ለዘለአለም ደስታችን እቅድ ያዘጋጀ አፍቃሪው፣ ፍትሁ፣ እና መሀሪው የሰማይ አባት እንዳለን እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ልጁ እንደሆነ እና የአለም አዳኝ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን የእግዚአብሔር ነብይ እንደሆኑ አውቃለሁ። እነዚህን ነገሮች የምለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜል።