2010–2019 (እ.አ.አ)
አባትነት - የዘለአለም እጣ ፈንታችን
ኤፕረል 2015


10:29

አባትነት - የዘለአለም እጣ ፈንታችን

እያንዳንዳችን የዘለአለም አባቶች በመሆን በዚህ ህይወት የአብን ሙሉ በረከቶች እና የእርሱን ስራ እና ክብር መሟላት እንደሰትባቸው።

አባቴ በወጣትነቴ ከፍተኛ ትምህርት አስተማረኝ። የአለማዊ ነገሮችን እያፈቀርኩኝ እንዳለሁ ተሰማው። ገንዘብ ሲኖረኝ፣ ሁልጊዜም ለራሴ ለሚሆን ነገር ላይ ወዲያም አጠፋዋለሁ።

Painting of a father talking to son in front of window with a view of the city below

አንድ ቀን ከሰዓት ላይ አዲስ ጫማዎች ሊገዛልኝ ወሰደኝ። በሱቁ ሁለተኛ ደረጃ ላይ፣ በመስኮት ወደ ውጪ ከእርሱ ጋር እንድመለከት ጠየቀኝ።

“ምን ትመለከታለህ?” ብሎ ጠየቀኝ።

ህንጻዎች፣ ሰማይ፣ ሰዎች” ነበር መልሴ።

“ስንት?”

“ብዙ!”

ከዚያም ይህን ሳንቲም ከኪሱ አወጣ። ለእኔ እየሰጠም፣ እንዲህ ጠየቀኝ፣ “ይህ ምንድን ነው?”

ወዲያውም አወኩት፣ “በብር የተሰራ የአንድ ዶላር ሳንቲም!”

ስለኬምስትሪ ያለውን እውቀት በመጠቀም፣ እንዲህ አለ፣ ያንን የብር ዶላር ሳንቲም አቅልጠህ ከትክክለኛ ግብአቶች ጋር ብታቀላቅለው፣ ሲልቨር ናይትሬት ይኖርሀል። ይህን መስኮት በሲልቨር ናይትሬት ብንሸፍነው፣ ምን ማየት ትችላለህ?”

መልሱን አላወኩም ነበር፣ ስለዚህ ወደ ሙሉ ርዝመት ወዳለው መስታወት ወሰደኝ እና፣ “አሁን ምን ታያለህ?” ብሎ ጠየቀኝ።

Father and son looking in a mirror at a clothing store.

“እራሴን አያለሁ።”

“አይደለም፣” ብሎ መለሰ፣ “የምታየው ብር አንተን አንፀባርቆ ሲያሳይህ ነው። በብሩ ላይ ካተኮርክ፣ የምታየው በሙሉ ራስህን ብቻ ነው፣ እናም እንደ መጋረጃም፣ ይህ የሰማይ አባት ለአንተ ያዘጋጀውን ዘለአለማዊ እጣ ፈንታ በግልጽ ለመመልከት እንዳትችል ያደርጋል።”

“ሌሪ፣” ብሎ ቀጠለ፣ “‘የዚህን አለም ነገሮች አትፈል[ግ] ነገር ግን አስቀድ[መህ] የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመገንባት፣ እና ጽድቁንም ለመመስረት ፈል[ግ]፣ እና እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይጨመር[ልሀ]ል’” (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 6፥38 [በማቴዎስ 6፥33፣ የግርጌ ማስታወሻ ])።

ዶላሩን እንድወስደው እና በምንም አይነት መንገድ እንዳይጠፋብኝ እንዳደርግ ነገረኝ። በየተመለከትኩበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ የሰማይ አባት ለእኔ ያለውን ዘለአለማዊ እጣ ፈንታ እንዳስብበት ነው።

አባቴን እና እንዴት እንዳስተማረኝ እወዳለሁ። እንደ እርሱ ለመሆን ፈለኩኝ። ጥሩ አባት ለመሆን ፍላጎት በልቤ ተከለልኝ፣ እናም ጥልቅ ተስፋዬም ምሳሌውን በደንብ እየተከተልኩኝ መሆኔ ነው።

ፕሬዘደንት ቶማስ  ኤስ. ሞንሰን በብዙ ጊዜ ውሳኔዎቻችን እጣ ፈንታዎቻችንን ይወስናሉ እናም ዘለአለማዊ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል (“Decisions Determine Destiny” [Church Educational System fireside, Nov.  6, 2005], 2, lds.org/broadcasts ተመልከቱ)።

ከዚያም፣ የዘለአለማዊ እጣ ፈንታችንን፣ በልዩ መልኩም የሰማይ አባት እንድናገኝ የሚፈልገንን አንዱን፣ ማለትም የዘለአለማዊ አባትነትን ግልጽ እይታ ማግኘት አይገባንምን? የዘለአለማዊ እጣ ፈንታችን ውሳኔዎቻችንን በሙሉ የሚወስኑ ይሁኑ። ምንም እንኳን እነዚያ ውሳኔዎች አስቸጋሪ ቢሆኑም፣ አብ ይደግፈናል።

ስለእንደዚህ አይነት እይታ ሀይል የተማርኩት ከ 12 እና 13 አመት ወንድ ልጆቼ ጋር በ50/20 ፉክክር ስሳተፍ ነበር። 50/20 50 ማይልን (80 ኪ.ሜ.) ከሀያ ሰዓታት በፊት የመፈጸም ፉክክርን ያካትታል። ከምሽቱ 3 ሰአት ጀመርን እና ምሽቱን ሙሉ እና በሚቀጥለውም ቀን ተራመድን። ይህም በጣም የሚያደክም 19 ሰዓት ነበር፣ ስኬታማም ነበርን።

ወደ ቤት ስንመለስም፣ አስደናቂ ባለቤት እና እናት ጥሩ እራት ብታዘጋጅም በምንም አይነት መንገድ ይህን ምግብ ወዳልነካንበት ቤት ውስጥ የገባነው እየተንፏቀቅን ነበር ማለት ይቻላል። ታላቁ ወንድ ልጄ ወደ ታች ወደ መኝታው እየተንፏቀቀ ሲሄድ፣ ታናሹ ልጄ ደግሞ በጣም ደክሞት በሶፋው ላይ ወደቀ።

ጉዳት የሚሰማው እረፍት ከወሰድኩኝ በኋላም፣ ወደ ታናሹ ልጄ ሄጄ በህይወት እንዳለ ተመለከትኩኝ።

“ደህናን ነህ?” ብዬ ጠየኩት።

“አባዬ፣ ይህ ካደረኳቸው ነገሮች በሙሉ በላይ ከባድ ነበር፣ እና ይህን እንደገና በምንም ማድረግ አልፈልግም።”

እኔም ይህን በምንም ለማድረግ እንደማልፈልግ ልነግረው አልነበረም። በምትኩም፣ ይህን ከባድ ነገር በማከናወኑ እንዴት እንደኮራሁበት ነገርኩት። ወደፊት ለሚያጋጥሙት ከባድ ነገሮች እንደሚያዘጋጀው አውቄ ነበር። ያንን እያሰብኩኝ እንዲህ አልኩት፣ “ልጄ ሆይ፣ ይህን ቃል ልግባልህ። ሚስዮን ስትሄድ፣ በአንድ ቀን ውስጥ 80 ኪ. ሜ. አትጓዝም።”

“ጥሩ ነው አባዬ! እንደዛ ከሆነ እሄዳለሁ።”

እነዚያ ቀላል ቃላት ነፍሴን በምስጋና እና ደስታ ሞሉት።

ከዚያም ወደ ታላቁ ወንድ ልጄ ወደታች ሄድኩኝ። በአጠገቡ ተኛሁ እና ነካሁት “ልጄ ሆይ፣ ደህና ነህ?”

“አባዬ፣ ያ በህይወቴ ካደረኳቸው ነገሮች በሙሉ የሚያስቸግር ነበር፣ ይህን በምንም እንደገና አላደርግም።” አይኖቹ ተዘጉ --ከዛ ተከፈቱ--እና እንዲህ አለ፣ “ልጄ እንዳደር ካልፈለገ በስተቀር።”

ለእርሱ ምስጋና እንዳለኝ ስገልጽለት እምባዎች በአይኔ መጡ። እኔ ከነበርኩት የተሻለ አባት እንደሚሆን ነገርኩት።ልቤ ሙሉ ነበር ምክንያቱም በዚህ ወጣትነቱ ከሁሉም በላይ ቅዱስ የሆነው የክህነት ሀላፊነቱ አባት መሆን እንደሆነ ተረድቶ ነበር። በዚህ ሀላፊነት እና ርዕስ፣ ማለትም እግዚአብሔር ራሱ ከእርሱ ጋር ስንነጋገር እንድንጠቀመው በሚፈልገን ርዕስ፣ ምንም ፍርሀት አልነበረውም። በልጄ ውስጥ የነበረውን የአባትነትን ፍላጎት የመመገብ ሀላፊነት እንዳለኝ አወኩኝ።

እነዚህ የአዳኝ ቃላት ለእኔ እንደ አባትነቴ ጥልቅ የሆነ ትርጉም ያዙ።

“አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና” (ዮሐንስ 5፥19)።

“አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች [አላደርግም]” (ዮሐንስ 8፥28)።

ከሰማይ ወላጆች ሴት ልጅ ጋር የተጋባሁ አባት እና ባለቤት መሆንን እወዳለሁ። ይህም ከህይወቴ በጣም እርካታ ከሚሰጡት ሁሉ የበለጠ ነው። በዚያ ምሽት አምስቱ ወንድ ልጆቼ እና እህታቸው ከጋብቻ፣ ከአባትነት፣ እና ከቤተሰብ የሚመጣውን ደስታ በእኔ ሁልጊዜ እንዲመለከቱ ተስፋዬ ነው።

አባቶች፣ “ወንጌልን በሁሉም ጊዜዎች ስበኩ፣ እና አስፈላጊ ሲሆንም ቃላትን ተጠቀሙ” (አሲሲ ፍራንሲስ ብለውታል ይባላል) የሚለውን አባባል እንደሰማችሁት እርግጠኛ ነኝ። ልጆቻችሁን በየቀኑ አባት መሆን ምን እንደሆነ እያስተማራችሁ ነው። ለሚቀጥለው ትውልድ መሰረትን እየጣላችሁ ናችሁ። ወንድ ልጆቻችሁ ባሎች እና አባቶች መሆንን እናንተ እንዴት ይህን ሀላፊነት እንደምታሟሉ በመመልከታቸው ይማራሉ። ለምሳሌ፥

እናታቸውን ምን ያህል እንደምትወዱ እና እንደምታከብሩ እናም ምን ያህል የእነርሱ አባት መሆናችሁን እንደምትወዱት ያውቃሉ?

የወደፊት ባለቤታቸውን እና ልጆቻቸውን እንዴት እንደሚንከባከቧቸው የሚማሩት እናንተ እያንዳንዳቸውን የሰማይ አባት እንደሚንከባከባቸው ስትንከባከቧቸው በሚመለከቱበት ጊዜ ነው።

በምሳሌአችሁ በኩል፣ ሴትነትን እንዴት ማክበር እና መጠበቅ እንዳለባቸው መማር ይችላሉ።

በቤታችሁ ውስጥ፣ ቤተሰባቸውን በፍቅር እና በፅድቅነት መምራትን ይማራሉ። በጊዜያዊ እና በመንፈሳዊ ሁኔታዎች ለቤተሰባቸው ህይወት የሚያስፈልጉትን እና ጥበቃዎችን ስለመስጠትም መማር ይችላሉ (“ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ፣” Ensign orLiahona, Nov. 2010, 129 ተመልከቱ)።

ወንድሞች፣ በነፍሴ ሀይል በሙሉ፣ ይህን ጥያቄ እንድታስቡበት እጠይቃለሁ፥ “ወንዶች ልጆቻችሁ የሰማይ አባት እዲያደርጉ የሚፈልገውን ለማድረግ ስትጥሩ ያያሉን?

መልሱ አዎን እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ። መልሱ አይደለም ከሆነ፣ ይህን ለመቀየር አልረፈደም፣ ነገር ግን ዛሬ መጀመር አለባችሁ። የሰማይ አባት እንደሚረዳችሁ እመሰክራለሁ።

አሁን ወጣት ወንዶች፣ የመልከ ፀዴቅ ክህነትን ለመቀበል፣ ቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓትን ለመቀበል፣ በሙሉ ጊዜ ሚስዮን የማገልል ሀላፊነታችሁን እና ግዴታችሁን ለማሟላት፣ እና ከዚያም ለረግም ጊዜ ሳትጠብቁ፣ ከእግዚአብሔር ሴት ልጅ ጋር በቤተመቅደስ ውስጥ ለመጋባት እና ቤተሰብ ለመመስረት እየተዘጋጃችሁ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ። ከዚያም ቤተሰባችሁን በመንፈሳዊ ነገሮች በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ትመራላችሁ (ት. እና ቃ. 20፥4446፥2107፥12 ተመልከቱ)።

ብዙ ወጣት ወንዶችን ይህን ጠይቄ ነበር፣ “ለምንድን ነው እዚህ ያላችሁት?”

እስከአሁንም፣ “አባት ለመሆን ለመማር፣ በዚያም የሰማይ አባት ያለውን ሁሉ ለመቀበል ለመዘጋጀት እና ብቁ ለመሆን” ብሎ የመለሰ ማንም የለም።

የአሮናዊ ክህነት ሀላፊነታችሁን በትምህርት እና ቃል ኪዳን ክፍል 20 ውስጥ እንደተገለጹት እንመልከታቸው። እነዚህን ሀላፊነቶች ቤተሰባችሁን ከምታገለግሉበት ኃላፊነት ጋር ሳገናኝ የሚሰማችሁን ስሜት አስተውሉ።

“[ቤተሰቦቻችሁን] ወደክርስቶስእንዲመጡ [ጋብዙ]” (ቁጥር 59)።

“ዘወትር “ጠብቋቸው፣ እና እነርሱን [እርዱ እናም አጠናክሩ]” (ቁጥር 53)።

የቤተሰብ አባሎቻችሁን “[ስበኩ፣ አስተምሩ፣ አብራሩ፣ አጥብቆ ምከሩ፣ እናም ጥመቁ]” (ቁጥር 46)።

“በሚስጥር እና በድምፅ እንዲጸልዩ እና የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ በጥብቅ [አበረታቱ]” (ቁጥር 47)።

“ምንም ጥፋት [በቤተሰባችሁ] እንዳይኖር፣ እንዲሁም … እርስ በራሳቸው እንዳይከፋፉ፣ እንዳይወሻሹ፣ እንዳይተማሙ፣ ወይም ክፉ እንዳይነጋገሩ [ጠብቁ]” (ክፍል 54)።

“[ቤተሰባችሁ] በየጊዜው እንዲሰበሰቡ አድርጉ” (ቁጥር 55)።

አባታችሁን እንደ ቤተሰብ በሀላፊነቱ እርዱት። እናታችሁን አባታችሁ በማይኖርበት ጊዜ በክህነት ጥንካሬ ደግፉ (ክፍል 52፣ 56 ተመልከቱ)።

ስትጠየቁም፣ “ሌሎች ካህናትን፣ መምህራንን፣ እናም ዲያቆናትን” በቤተሰባችሁ ሹሙ (ክፍል 48)።

ይህ የአባት ስራ እና ሀላፊነት አይመስልምን?

A young man reading a a Church publication.

የአሮናዊ ክህነት ሀላፊነቶችን ማሟላት ወጣት ወንዶችን ለአባትነት ያዘጋጃል። ለእግዚአብሔር ሀላፊነት የሚባለው መፅሄት ሀላፊነታችሁን ለመማር እና ለማሟላት ልዩ እቅዶችን ለማውጣት መሳሪያ መሆን ይችላል። ይህም የሰማይ አባትን ፍላጎት ስትፈልጉ እና ይህን ለማሟላት አላማ ሲኖራችሁ እንደ መመሪያ እና እርዳታ መሆን ይችላል።

የሰማይ አባት በዚህ ጊዜ ወደዚህ ያመጣችሁ ለልዩ ስራ እና ለዘለአለማዊ አላማ ነው። ያም አላማ ምን እንደሆነ በግልጽ እንድትመለከቱት እና እንድትረዱት ይፈልጋል። እርሱ አባታችሁ ነው፣ እናም ወደ እርሱ ለመመሪያ መዞር ትችላላችሁ።

የሰማይ አባት ስለእያንዳንዳችን እንደሚያስብ እና ዘለአለማዊ እጣ ፈንታችንን ለማሳካት የግል እቅድ ለእኛ እንዳለው አውቃለሁ። አንድያ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ፍጹም ያልሆንበትን በኃጢያት ክፍያ በኩል እንዲያሸንፍልን ልኮታል። በእርሱ ከተመካን ምስክር፣ ጓደኛ፣ እና ለዘለአለም ወደምንሄድበት መድረሻችን መመሪያ እንዲሆነን በመንፈስ ቅዱስ ባርኮናል። የአብን ሙሉ በረከት እና የእርሱን ስራናየእርሱን ክብር (ሙሴ 1፥39) ተመልከቱ) የዘለአለም አባቶች በመሆን እንዲሟላ በዚህ ህይወት እንደሰትበት። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።