ሀላፊነትን ብትወስዱ
ሀላፊነታችንን በመማር፣ ትክክለኛ ውሳኔዎችን በማድረግ፣ እንደነዚያ ውሳኔዎች በመተግበር፣ እና የአባታችንን ፍቃድ በመቀበል ወደ ፊት እንግፋ።
በሰሜን ቺሊ በተወለድኩበት ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመስበክ ሚስኦናዊያን ሲደርሱ ገና 12 አመቴ ነበር። አንድ እሁድ ቀን፣ ለስድስት ወራት አነስተኛ ቅርንጫፍ ከተካፈልኩ በኋላ፣ ቅዱስ ቁርባን የሚያሳልፍው ሚስኦናዊ ዳቦውን አቀረበልኝ። ተመለከትኩት እና ረጋ ባለ ድምጽ “አልችልም” አልኩት።
“ለምን?” ብሎ መለሰልኛ።
እነዲህ አልኩት፣ “ምክንያቱም የቤተክርስቲያን አባል አይደለሁም።”1
ሚስኦናዊው ማመን አልቻለም። አይኖቹ ያበሩ ነበር። “ግን ይሄ ወጣት ልጅ በእያንዳንዱ ጉባኤ ይገኛል! እንዴት የቤተክርስቲያን አባል ላይሆን ይችላል?” ብሎ እንዳሰበ እገምታለሁ።
በቀጣዩ ቀን፣ ሚሰኦናዊያን በፍጥነት እቤቴ ተገኙ፣ እና መላው ቤተሰቤን ለማስተማር የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ። ቤተሰቤ ፍላጎት ስላልነበራቸው፣ ሚስኦናዊያኑ እንዲቀጥሉ በራስ መተማመን እንዲሰማቸው ያደረገው የእኔ ከስድስት ወራት በላይ በየሳምንቱ ቤተክርስቲያን መገኘቴ ብቻ ነው። በመጨረሻም፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል እንድሆን ሲጋብዙኝ ስጠብቀው የነበረው ታላቅ ጊዜ መጣ። ትንሽ ልጅ ስለሆንኩ የቤተሰብ ፍቃድ እንደሚያስፈልገኝ ሚስኦናዊያኑ አብራሩልኝ። ተወዳጅ ምላሹ “ልጄ፣ ህጋዊ እድሜህ ሲደርስ የራስህን ውሳኔ ለመወሰን ትችላለህ” እነደሚሆን በማሰብ አባቴን ለማግኘት ሄድኩ።
ሚስኦናዊያኑ እያናገሩት ሳለ፣ የምፈልገውን ፍቃድ እንዲሰጠኝ ልቡ እንዲነካ ከልብ እየጸለይኩ ነበር። ለሚስኦናዊያኑ የሰጣቸው ምላሽ የሚከተለው ነበር፤ “ሚስኦኖች፣ ልጄ ጆርጅ ላለፉት ስድስት ወራት ሁሌ እሁድ በማለዳ ሲነሳ፣ ምርጥ ልብሶቹን ሲያደርግ፣ እና ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄድ እመለከት ነበር። በህይወቱ የቤተክርስቲያኑን መልካም ተጽእኖ ብቻ ነው ያየሁት።” እናም ወደ እኔ በማስመልከት እንደዚህ በማለት አስገረመኝ፣ “ልጄ፣ ለዚህ ውሳኔ ሀላፊነቱን የምትወስድ ከሆነ፣ ለመጠመቅ የእኔን ፍቃድ ሰጥቼሀለሁ።” አባቴን አቀፍኩት፣ ሳምኩት እና ስላደረገው ነገር አመሰገንኩት። በቀጣዩ ቀን ተጠመኩኝ። ያለፈው ሳምንት የዛ በህይወቴ አስፈላጊ ወቅት 47ኛ አመት ተቆጠረ።
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን ምን ሀላፊነት አለብን? ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ እንደሚከተለው ገልፀውታል፤ “የሚከተሉት ሁለት ታላቅ ሀላፊነቶች አሉን፣… መጀመሪያ፣ የራሳችንን ደህንነት መሻት፤ እና፣ ሁለተኛ፣ ለሌሎች ሰዎች ያለብን ግዴታ።”2
እነዚህ እንግዲህ የሰማይ አባታችን የሰጠን ዋና ሀላፊነቶች ናቸው፤ የራሳችንን እና የሌሎችን ደህንነት መሻት፣ ደህንነት ማለት አባታችን ለታዛዥ ልጆቹ ያቀረበውን ከፍተኛ የክብር ደረጃ መድረስ መሆኑን በመረዳት።3 እነዚህ ለእኛ የተሰጡን ሀላፊነቶችን-- እና እኛም በነጻነት የተቀበልናቸው-- ቅድሚያ የምንሰጣቸው፣ ፍላጎታችንን፣ ውሳኔዎቻችንን፣ እና የየቀን ድርጊታችንን የሚያመላክት መሆን አለበት።
ያንን ወደ መረዳት ለመጣ ሰው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያአት ክፍያ አማካኝነት፣ መንግስተ ሰማይ በእውነትም ቅርብ ናት፣ ያንን ለማግኘት አለመቻል ኩነኔ ያስከትላል። ስለዚህ፣ ልክ የስኬት ተቃራኒው ውድቀት እንደሆነ፣ የደህንነት ተቃራኒ ኩነኔ ነው። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዲህ አስተማሩ “ሰዎች ምርጥነት በአቅራቢያ መሆኑን አንዴ ካዩ ባልተሟላ ነገር ለዘላቂ ደስተኛ መሆን አይችሉም።”4 እናም መንግስተ ሳማይ እንደሚቻል ካወቅን እንዴት ከመንግስተ ሰማይ ባነሰ ነገር ልንደሰት እንችላለን?
እርሱ እንደሆነው እንድንሆን ላለው ግምት ምላሽ ለመስጠትም ቢሆን፣ ለሰማይ አባታችን ሀላፊነትን ለመውሰድ ያለንን ፍላጎት ለማሟላት አራት ቁልፍ መርሆዎችን እንዳካፍል ፍቀዱልኝ።
1. ሀላፊነታችንን መማር
የእግዚአብሔርን ፍላጎት ከሆነ የምናደርገው፣ ለእርሱ ሀላፊነትን የምንወስድ ከሆነ፣ በመማር፣ በመረዳት፣ በመቀበል፣ እና ለእኛ እርሱ እንዳለው ፍላጎት በመኖር መጀመር ይኖርብናል። ጌታ እንዲህ ብሏል፣ “ስለዚህ አሁን ሁሉም ሰው በተመደበበት ክፍል በጽኑ ትጋት ለመስራት ሀላፊነቱን ይማር።”5 የሰማይ አባታችን የሚጠብቅብንን እና እንድናደርግ የሚፈልገውን መረዳታችንን እርግጠኛ ካልሆንን የፍላጎት መኖር ብቻ በቂ አይደለም።
አሊስ ኢን በወንደርላንድ በሚባለው ታሪክ ውስጥ፣ አሊስ በየትኛው መንገድ መሄድ እናዳለባት አታውቅም፣ ስለዚህ ድመቷንቼሻየርን እንዲህ ጠየቀች፣ “ከዚህ ወዴት መንገድ መሄድ እንዳለብኝ እባክሽ ልትነግሪኝ ትችያለሽ?”
ድመቷ መልሳ፣ “ያ በጣም የተመሰረተው የት ለመድረስ ባለሽ ፍላጎት ላይ ነው።”
አሊስ እንዲህ አለች፣ “የት እንደሆነ ብዙም አይጨንቀኝም”
“ስለዚህ በየት መንገድ መሄድሽ ለውጥ አያመጣም” አለች ድመቷ።6
በመሆኑም፣ “ፍሬው ሰውን ደስተኛ ለማድረግ የሚፈለገው ዛፍ”-- “ወደ ህይወት የሚመራው መንገድ”7 ጠባብ እንደሆነ፣ በመንገዱ ለመጓዝ ጥረት እንደሚያስፈልግ፣ እና “ጥቂቶች እንደሚያገኙት” እናውቃለን።8
ኔፊ እንዲህ ያስተምራል “ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች ሁሉ የክርስቶስ ቃል ይነግራችኋል”9 ከዛ ጨምሮም “ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ መንፈስ ቅዱስ ያሳያችኋል።”10 ስለዚህ፣ ሀላፊነታችንን ለመማር የሚያስችሉንን ምንጮች የምናገኘው ከጥንት እና የዘመኑ ነብያት እናም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የምንቀበለው የግል መገለጥ ናቸው።
2. ውሳኔዎቹን መወሰን
ስለ ተመለሰው ወንጌል፣ ስለ አንድ ትእዛዝ፣ ከጥሪ አገልግሎት ጋር ስለተያያዘ ሀላፊነት፣ ወይም ቤተመቅደስ ስለምንፈጽመው ቃልኪዳን ተምረንም ይሁን፣በዚያ አዲስ እውቀት ተመስርተን ለመተግበር ወይም ላለመተግበር ምርጫው የእኛ ነው። እንደ ቅዱስ የጥምቀት ወይም የቤተመቅደስ ስርአት ቃልኪዳኖችን ለመግባት እያንዳንዱ ሰው በነፃነት ለእራሱ ወይም ለራሷ ይመርጣሉ። በጥንት የሀይማኖት ሰዎች ህይወት መሀላ መግባት የተለመደ ስለነበር፣ የድሮው ህግ እንዲህ ይደነግጋል “በስሜ በሀሰት አትማሉ።”11 ስለሆነም፣ በሜሪዲያን ጊዜ፣ ከፍ ያለውን መሰጠታችንን የምንጠብቅበትን መንገድ አዎ ማለት አዎ ነው እና አይ ማለት አይ ነው ብሎ አዳኛችን አስተማረ።12 አንድ ሰው ቃሉ ለሌው ሰው እውነተኛነትን እና መሰጠትን ለመመስረት በቂ መሆን አለበት እና ለሰማይ አባት ሲሆን ደሞ የበለጠ ነው። መሰጠትን ማክበር የቃላችን እውነተኛነት እና ታማኝነት መገለጫ እየሆነ ይመጣል።
3. እንደዛው መተግበር
ሀላፊነታችንን ከተማርን በኋላ እና ከትምህርቱ እና መረዳታችን ጋር በማዛመድ ውሳኔዎችን ካደረግን በኋላ፣ እንደዚያው መተግበር አለብን።
ለአባቱ መሰጠትን ከማሳካት ጽኑ ቁርጠኝነት ሀይለኛ ምሳሌ የሚገኘው በአዳኛችን ተሞክሮ ሽባው ሰው እንዲፈወስ ወደ እሱ ያመጡት ነው። “ኢየሱስ እምነታቸውን አይቶ ሽበውን፣ አንተ ልጅ ሀጢያትህ ተሰረየችልህ አለው።”13 ለሀጢያታችን ይቅርታን ለማግኘት የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን፣ ግን ሽበው ሰው በተፈወሰበት ወቅት፣ ታላቁ ክስተት ገና አልተከናወነም፣ ጌተሰማኒ ገና ሊከሰት ነበር። ስለሆነም፣ ኢየሱስ ሽባውን የባረከው ለመቆም እና የመራመድ አቅም እንዲያገኝ ብቻ አልነበረም፣ ነገር ግን ለሀጢያቱ ይቅርታንም ጨምሮ ሰጠው፣ ከአባቱ ጋር የገባውን ቃል እንደሚፈጽም፣ እንደማይወድቅ፣ እና በጌተሰማኒ እና በመስቀሉ ለማድረግ ቃል የገባውን እንደሚያደርግ የማያጠራጥር ምልክት ሰጠ።
ልንጓዝበት የመረጥነው መንገድ ጠባብ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን የሚጠይቁ እና በመንገዱ ለመቆየት እና ለመግፋት የተቻለንን ጥረት እንድናደርግ የሚጠይቁ ፈተናዎች በመንገዱ ላይ አሉ።ንስሀ ልንገባ እና ታዛዥ እና ታጋሽ ልንሆን ይገባል በዙሪያችን የከበቡንን ሁኔታዎች ባንረዳም፣ እንኳን ንስሀ ልንገባ እና ታዛዥ እና ታጋሽ ልንሆን ይገባል።ሌሎችን ይቅር ማለትና በተማርነው እና በመረጥነው መሰረት መኖር አለብን።
4. የአባትን ፍላጎት በፍቃድ መቀበል
ደቀመዝሙርነት ሀላፊነትን መማር፣ ትክክለኛ ወውሳኔዎችን ማድረግ፣ እና እንደዚያው ማድረግን ብቻ አይደለም ከእኛ የሚጠብቀው፣ ነገር ግን ከእኛ የቅድስና ፍላጎት ወይም ከምርጫችን ጋር አንድ ባይሆንም፣ ፍቃደኝነታችንን እና የእግዚአብሔርን ፍላጎት የመቀበል ብቃታችንን ማጎልበትም ወሳኝ ነው።
ወደ ጌታ የመጣው ለምፃም ይደንቀኛል እና ባህሪውን አደንቃለሁ፣ “ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና፣ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።”14 ለምጻሙ ምንም ነገር አልጠየቀም፣ ፍላጎቶቹ የተቀደሱ ቢሆንም እንኳ፣ በቀላሉ የጌታን ፍቃድ ለመቀበል ፍቃደኛ ነበር።
ከጥቂት አመታት በፊት ጓደኞቼ የሆኑት ውድ ታማኝ ጥንዶች፣ ለረጅም ጊዜ ሲጸልዩበት የነበረውን ወንድ ልጅ የመውለድ ፋላጎት እውን በመሆን ተባረኩ። ጓደኞቻችን እና ያኔ ብቸኛ የነበረችው ሴት ልጃቸው በአዲሱ ወንድ ልጅ መምጠት ሲደሰቱ ቤቱ በደስታ ተሞላ። ስለሆነም፣አንድ ቀን፣ ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፤ ሶስት አመት ብቻ የነበረው ትንሹ ወንድ ልጅ በድንገት ኮማ ውስጥ ገባ። ሁኔታውን እንደሰማሁ፣ በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ድጋፋችንን ለመግለጽ ለጓደኛዬ ደወልኩ። የእርሱ ምላሽ ግን ለእኔ ትምህርት ነበር። እንዲህ አለ፣ “ወደ እራሱ ለመውሰድ የአባቱ ፍቃድ ከሆነ፣ እኛ እንቀበላለን።” የጓደኛዬ ቃላት ጠቂትም ማጉረምረም፣ አመጸኛነት፣ ወይም ሀዘን አልነበረውም። በተቃራኒው፣ በቃላቱ ሊሰማኝ የቻለው ለዛ ጥቂት ጊዜ ትንሹ ልጅን በመስጠት ስላስደሰታቸው ለእግዚአብሔር አመስጋኝነት ብቻ ነበር፣ እንዲሁም የአባትን ፍቃድ ለመቀበል የእርሱን ሙሉ ፍላጎት ነው። ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ያ ትንሹ ወደ መንግስተ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ።
ሀላፊነታችንን በመማር፣ ትክክለኛ ውሳኔዎችን በማድረግ፣ እንደነዚያ ውሳኔዎች በመተግበር፣ እና የአባታችንን ፍቃድ በመቀበል ወደ ፊት እንግፋ።
ከ47 አመታት በፊት አባቴ እንድወስን ስላደረገኝ ውሳኔ አመስጋኝ እና ደስተኛ ነኝ። ከጊዜ በኋላ፣ ለዚያ ለውሳኔ ሀላፊነትን እንድወስድ የሰጠኝ ሁኔታ--- ለሰማይ አባቴ ሀላፊነት ወሳጅ መሆን እና የእራሴን እና የሌሎችን ደህንነት መሻት፣ በዚያም የበለጠ አባቴ እንደሚጠብቅብኝ እና እንድሆን እንደሚፈልገው መሆን ማለት እንደሆነ እየተረዳሁ መጣሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።