ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 4–10 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 14-17፦“ቁሙ፣ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ“


“ሚያዝያ 4–10 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 14-17፦ ‘ቁሙ፣ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ፣‘“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“ሚያዝያ 4–10 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 14-17፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ቀይ ባህር

ቀይ ባህር

ሚያዝያ 4–10 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፀአት 14–17

“ቁሙ፣ዛሬ ለናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ“

እግዚያብሄር ሙሴን ስለተሞክሮዎቹ “ለመታሰቢያ በመጽሃፍ“ እንዲጽፍ በኢያሱም ጆሮ “እንዲናገር“ አዘዘው(ኦሪት ዘፀአት 17፥14)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንፈሳዊ ተሞክሮዎቻችሁን መመዝገብ እናንተ እና የምትወዷቸው የጌታን መልካምነት እንድታስታውሱ ይረዳል፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እስራኤላውያን ወጥመድ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ በአንድ በኩል ቀይ ባህር ነበር በሌላ በኩል ደግሞ የፈርኦን ሰራዊት እየገሰገሰ ነበር፡፡ ከግብጽ የማምለጣቸው ነገር በአጭሩ የሚቀጭ መስሎ ነበረ፡፡ ነገር ግን እግዚያብሄር እስራኤላውያን ለትውልድ ሁሉ እንዲያስታውሱት የሚፈልገው መልዕክት ነበረው:“አትፍሩ … እግዚያብሄር ስለናንተ ይዋጋል” (ኦሪት ዘፀአት 14፥13–14)፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣የእግዚያብሄር ህዝብ እምነት እና ድፍረት ፈልጎ በነበረ ጊዜ ወደዚህ የእስራኤል ተዐምራዊ ነጻ የመውጣት ዘገባ ፊቱን መልሷል፡፡ ኔፊ ወንድሞቹን ለማነሳሳት በፈለገ ጊዜ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ”ልክ እንደ ሙሴ ጠንካሮች እንሁን፣ እነሆ እርሱ በእውነት የቀይ ባሕርን ውሃ ተናገረው፣ ውሃውም ወዲያና ወዲህ ተከፈለ፣ አባቶቻችንም በውስጡ ተሻግረው ከግዛት በደረቅ ምድር ወጡ” (1 ኔፊ 4፥2)። ንጉስ ሊምሂ ምርኮኛ ህዝቡ “ራሳ[ቸውን] እንዲያቀኑ እና [እንዲ]ደሰቱ” በፈለገ ጊዜ ይህንኑ ታሪክ አስታወሳቸው(ሞዛያ 7፥19)። አልማም ለወንድ ለልጆቹ ስለ እግዚያብሄር ሃይል ለመመስከር በፈለገ ጊዜ ይህንኑ ታሪክ ነበር የጠቀሰው( አልማ 36፥28ይመልከቱ)። እናም እኛ ነጻ መውጣት ስንፈልግ—ትንሽ ተጨማሪ እምነት ስንፈልግ፣“[ለመቆም] እና የጌታን ማዳን [ለማየት]” ስንፈልግ—“ጌታ በዚያን ቀን እስራኤልን እንደዚህ ከግብጻውያን እጅ [እንደ]አዳነ“ ማስታወስ እንችላለን(ኦሪት ዘፍጥረት 14፥13, 30)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘጸአት 14

እግዚያብሄር እኔን የማዳን ኃይል አለው።

ኦሪት ዘፀአት 14፥1–10ን ስታነቡ፣የፈርኦን ሰራዊት በተቃረበ ጊዜ እስራኤላውያን እንዴት ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል ገምቱ። ምናልባት የተጋፈጣችሁትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለማለፍ ተአምር እንደሚያስፈልጋችሁ ይሰማችሁ ይሆናል። ከ ኦሪት ዘፀአት14፥13–31 በህይወታችሁ የእግዚያብሄርን ማዳን እንድትፈልጉ ሊረዳችሁ የሚችል ምን ነገር ትማራላችሁ? እግዚያብሄር ከመከራ ማዳንን ስለሚሰጥባቸው መንገዶች ምን ተምራችኋል? የእርሱን የማዳን ሃይል በህይወታችሁ እንዴት እንዳያችሁ አሰላስሉ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2–3፤ ኤል. ቶም ፔሪ፣ “The Power of Deliverance፣” ሊያሆና ግንቦት 2012(እ.አ.አ)፣ 94–97፤ የመጽሃፍ ቅዱስ ካርታዎች፣ ቁ. 2, “Israel’s Exodus from Egypt and Entry into Canaan” ይመልከቱ።

ኦሪት ዘጸአት 15፥22–27።

ጌታ መራራ ነገሮችን ጣፋጭ ማድረግ ይችላል።

ኦሪት ዘጸአት 15፥22–27 የእስራኤልን ወደ ተስፋይቱ ምድር ጉዙ ስታነቡ በህይወታችሁ እንደ መራ ውሃ “መራራ“ የመሰሉ ነገሮችን አስቡ። እነዚህን ጥቅሶች ስታሰላስሉ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ አስገቡ:ጌታ በህይወታችሁ ያሉትን መራራ ነገሮች ጣፋጭ ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? እነዚህ ተሞክሮዎች በህይወታችሁ ውስጥ ምን ዋጋ ነበራቸው? ቁጥር 26 እና 27 ድምጹን ስንሰማ ጌታ እንዴት እንደሚባርከን ምን ይጠቁማል?

ኦሪት ዘጸአት 15፥23–2716፥1-1517፥1–7

በአስቸጋረ ጊዜያት ውስጥ ብሆንም እንኳን በጌታ መታመን እችላለሁ።

አግዚያብሄር ካደረገላቸው ከዚያ ሁሉ ነገር በኋላም እንኳን የነበሩበት ሁኔታ ከባድ እየሆነ ሲመጣ በማጉረምረማቸው ወይም በማማረራቸው ምከንያት እስራኤላውያንን መተቸት ይፈትናል። ነገር ግን ኦሪት ዘጸአት 15፥23–2716፥1–1517፥1–7ን ስታነቡ፣ይህንኑ አይነት ነገር አድርጋችሁ ታውቁ እንደነበረ አስቡ። ከእስራኤላውያን ተሞክሮ ብዙ እንዳታጉረመርሙ እና ይበልጥ በእግዚያብሄር እንድትታመኑ የሚረዳችሁ ምን ነገር ትማራላችሁ? ለምሳሌ፦እስራኤላውያን ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች ምላሽ በሰጡበት መንገድ እና ሙሴ ምላሽ በሰጠበት መንገድ መካከል ምን ልዩነቶችን ታስተውላላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች ስለእግዚያብሄር ምን ያስተምሯችኋል?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 2፥11–12፤ “Sin of Murmuring” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።

ምስል
አንዲት ሴት መና ስትሰበስብ

ከእግዚያብሄር የመጣ መና አስራኤላውያንን በአካል መገበ ፤ እኛም እንዲሁ በየቀኑ መንፈሳዊ ምግብ እንፈልጋለን። ፍሬስኮ በሌኦፖልድ ብሩክነር

ኦሪት ዘጸአት 16

መንፈሳዊ ምግብ በየቀኑ መፈለግ አለብኝ።

ኦሪት ዘጸአት 16ውስጥ ከሚገኘው የመና ተአምር ልንማራቸው የምንችለው ብዙ መንፈሳዊ ትምህርቶች አሉ። እስራኤላውያን መናውን ስለመሰብሰብ፣ስለመጠቀም እና ስለማስቀመጥ የተሰጣቸውን ዝርዝር መመሪያ አስተውሉ( ኦሪት ዘጸአት 16፥16፣ 19፣ 22–26ይመልከቱ)። በየቀኑመንፈሳዊ ምግብ ስትፈልጉ በነዚህ መመሪያዎች ውስጥ ለናንተ የሚሆኑ ምን ነገር ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ዮሃንስ 6፥31–35፣ 48–58 እንዲሁም “Daily Bread: Pattern,” “Daily Bread: Experience,” እና “Daily Bread: Change” (ChurchofJesusChrist.org) የሚሉትን ቪዲዮዎች ይመልከቱ።

ኦሪት ዘጸአት 17፥1–7

ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ አለቴ እና ህያው ውሃዬ ነው።

ኦሪት ዘጸአት 17፥1–7ን ስታነቡ ስለ ጌታ አስቡ። ለናንተ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አለት የሆነው እንዴት ነው?( መዝሙረ ዳዊት 62፥6–7ሄለማን 5፥12ን ይመልከቱ)። እንደ ውሃ የሆነው እንዴት ነው? ( ዮሃንስ 4፥10–141 ቆሮንቶስ 10፥1–41 ኔፊ 11፥25ን ይመልከቱ)።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፀአት 14፥13–22የቤተሰባችሁ አባላት ሙሴ ቀይ ባህርን እንደከፈለው በጎድጓዳ እቃ ውስጥ ወይም በገላ መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ያለን ውሃ “ለመክፈል“ በመሞከር ሊደሰቱ ይችላሉ። ቀይ ባህር ያለ እግዚያብሄር እርዳታ ሊከፈል የማይችል እንደነበር እንዲገነዘቡ እርዷቸው። በሕይወታችን እና በቅድመአያቶቻችን ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ሃይል ያየነው እንዴት ነው ?

ኦሪት ዘጸአት 15፥1–21በተዐምር ቀይ ባህርን ከተሻገሩ በኋላ በ ኦሪት ዘጸአት 15፥1–21ውስጥ የሚገኘውን የሙሴ መዝሙር የሚባለውን የምስጋና መዝሙር ዘመሩ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚያብሄር ለእስራኤላውያን ስላደረገላቸው ነገሮች የሚመሰክሩ ሃረጎችን እና ሌሎች ትርጉም ያላቸው ሃረጎችን እንደ ቤተሰብ ፈልጉ። ከዚያም እግዚያብሄር ስላደረገላችሁ ነገር ቤተሰባችሁን የሚያስታውስ አንድ መዝሙር ልትዘምሩ ትችላላችሁ።

ኦሪት ዘጸአት 16፥1–517፥1-7 ኦሪት ዘጸአት 16፥1–5 እና 17፥1-7 ን ማንበብ አዳኙ እንደ ህይወት እንጀራ፣እንደ ህያው ውሃ እና እንደ አለታችን መሆኑ ምን ማለት እንደሆነ ወደሚዳስስ ውይይት ሊመራ ይችላል። እነዚህ ታሪኮች ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርግልንን የሚያስታውሱን እንዴት ነው? እንደውይይታችሁ አንድ አካል፣ ዮሃንስ 4፥10–146፥29–35፣ 48–51ሄላማን 5፥12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79ን ልታነቡ ትችላላችሁ።

ኦሪት ዘጸአት 17፥8–16አሮን እና ሖር የሙሴን እጅ የሚይዙበትን ታሪክ ልትተውኑ እና እግዚያብሄር እንዲመሩን የጠራቸውን እንዴት እንደምንደገግፍ እንደሚያመለክት ልትወያዩ ትችላላችሁ። የአሮንን እና የሖርን ምሳሌ (በመላው ምዕራፍ 15–17እንደተገለጸው) ከእስራኤላውያን በሙሴ ላይ ማጉረምረም ጋር ልታነጻጽሩትም ትችላላችሁ ። መሪዎቻችንን ልንደግፋቸው እና ልንረዳቸው የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? ይህንን ስናደርግ ለእኛ እና ለመሪዎቻችን ምን በረከቶች ይመጣሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “የእስራኤል አዳኝ፣ ” መዝሙሮች፣ ቁጥር 6።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የራሳችሁን መንፈሳዊ ግንዛቤ ፈልጉ። በግል እና በቤተሰብ ጥናታችሁ በነዚሀ የጥናት መዘርዝሮች ውስጥ ባሉ ጎልተው በወጡ ጥቅሶች ራሳችሁን አትወሰኑ። ምናልባት እዚህ አጽንኦት ያልተሰጣቸው በነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ጌታ ለናንተ መልዕክት አለው ። በጸሎት መነሳሳትን ፈልጉ፡፡

ምስል
ሙሴ ቀይ ባህርን ሲከፍል

ሙሴ ቀይ ባህርን ሲከፍል ምስል በሮበርት ቲ. ባሬት

አትም