2. የእስራኤል ከግብፅ መሰደድ እና ወደ ከነዓን መግባት
-
ሱኮት ዕብራውያን የመጀመሪያውን የሰፈሩበትን ቦታ ለቅቀው ሲሄዱ፣ ጌታ በቀን በዳመና እናም በሌሊት በእሳት ዓምድ ረዳቸው (ዘፀአ. ፲፫፥፳–፳፪)።
-
ማራ ጌታ የማራን ውሀዎች ፈወሰ (ዘፀአ. ፲፭፥፳፫–፳፮)።
-
ኤሊም እስራኤል በ፲፪ ምንጮች አጠገብ ሰፈሩ (ዘፀአ. ፲፭፥፳፯)።
-
የሲን ምድረበዳ ጌታ እስራኤልን ለመመገብ መና እና ኩዌል ላከ(ዘፀአ. ፲፮)።
-
ራፊዲም እስራኤል ከአማሌቅ ጋር ተዋጉ (ዘፀአ. ፲፯፥፰–፲፮)።
-
የሲና ተራራ (የኮሬብ ተራራ ወይም ጀቤል ሙሳ) ጌታ አስር ቃላትን ገለጸ (ዘፀአ. ፲፱–፳)።
-
የሲና ምድረበዳ እስራኤል ታቦት ሰራች (ዘፀአ. ፳፭–፴)።
-
የምድረበዳ መስፈሪያ ቦታ ሰባ ሽማግሌዎች ሙሴን ህዝቡን በመግዛት እንዲረዱት ተጠሩ (ዘኁል. ፲፩፥፲፮–፲፯)።
-
ዔጽዮንጋብር እስራኤል በኤሳው እና በአሞን ህዝቦች ምድር ውስጥ አለፉ (ዘዳግ. ፪)።
-
ቃዴስ በርኔ ሙሴ ሰላዮች ወደ ቃል ኪዳን ምድር ላከ፤ እስራኤል አመጸች እና ወደ ምድሯ አልገባችም፤ ቃዴስ እንደ እስራኤል ዋና መስፈሪያ ቦታ አገለገለ (ዘኁል. ፲፫፥፩–፫፣ ፲፯–፴፫፤ ፲፬፤ ፴፪፥፰፤ ዘዳግ. ፪፥፲፬)።
-
የምስራቅ ምድረበዳ እስራኤል ከኤዶም እና ከሞአብ ጋር መዋጋትን አስወገዱ (ዘኁል. ፳፥፲፬–፳፩፤ ፳፪–፳፬)።
-
የአሮኖን ወንዝ እስራኤል ከእነርሱ ጋር የተዋጉትን አሞናውያን አጠፉ (ዘዳግ. ፪፥፳፬–፴፯)።
-
የናባ ተራራ ሙሴ የቃል ኪዳን ምድርን አየ (ዘዳግ. ፴፬፥፩–፬)። ሙሴ የመጨረሻ ሶስት ስብከቱን ሰበከ (ዘዳግ. ፩–፴፪)።
-
የሞአብ ሜዳ ጌታ ምድሩን እንዲከፋፈሉ እና በእዚያ የሚኖሩትን እንዲያጠፉ ነገራቸው (ዘኁል. ፴፫፥፶–፶፮)።
-
የዮርዳኖስ ወንዝ እስራኤል የዮርዳኖስን ወንዝ በደረቀ ምድር ላይ ተሻገሩ። በጌልገላ አጠገብ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ በታች የመጡ ድንጋዮች እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መከፈል ማስታወሻ ተቀመጡ (ኢያ. ፫፥፩–፭፥፩)።
-
ኢያሪኮ የእስራኤል ልጆች ከተማውን ያዙ እናም ደመሰሱ (ኢያ. ፮)።