12. ኢየሩሳሌም በኢየሱስ ጊዜ
-
ጎልጎታ የኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ሊሆን የሚችል ቦታ (ማቴ. ፳፯፥፴፫–፴፯)።
-
የአትክልት ስፍራ መቃብር የኢየሱስ ሰውነት ያረፈበት ሊሆን የሚችል አንድ ቦታ (ዮሐ. ፲፱፥፴፰–፵፪)። ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ለመግደላዊ ማርያም በመቃብሩ ውጪ በሚገኘው የአትክልት ስፍራ ውስጥ ታየ (ዮሐ. ፳፥፩–፲፯)።
-
የአንቶኒያ ምሽግ ኢየሱስ የተከሰሰበት፣ ተፈረደበት፣ ተሰደበበት፣ እና የተገረፈበት በእዚህ ቦታ ላይ ይሆናል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰–፲፱፥፲፮)። ጳውሎስ ታሰረ እናም የተቀየረበትን ታሪክ ነገረ (የሐዋ. ፳፩፥፴፩–፳፪፥፳፩)።
-
የቤተ ሳይዳ መጠመቂያ ገናዳ ኢየሱስ ሽባን ሰው በሰንበት ፈወሰ (ዮሐ. ፭፥፪–፱)።
-
ቤተመቅደስ ገብርኤል ለዘካርያስ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ነገረው (ሉቃ. ፩፥፭–፳፭)። የቤተመቅደስ መጋረጃ በአዳኝ ሞት ጊዜ ተቀደደ (ማቴ. ፳፯፥፶፩)።
-
የሰለሞን ሰቀላ ኢየሱስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አወጀ። አይሁዶች ኢየሱስን ለመውገር ሞከሩ (ዮሐ. ፲፥፳፪–፴፱)። ጴጥሮስ አንካሳ ሰውን ከፈወሰ በኋላ ንስሀ መግባትን ሰበከ (የሐዋ. ፫፥፲፩–፳፮)።
-
መልካም ደጅ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ አንካሳ ሰው ፈወሱ (የሐዋ. ፫፥፩–፲)።
-
የቤተመቅደስ ጫፍ ኢየሱስ በሰይጣን ተፈተነ (ማቴ. ፬፥፭–፯) (ይህ ድርጊት ሊደርስ የቻለበት ቦታ።)
-
ቅዱስ ተራራ (የማይታወቅ ቦታ)
-
በባህል አብርሐም ይስሐቅን የሚሰዋበት መሰዊያ በእዚህ ቦታ ገነባ ይባላል (ዘፍጥ. ፳፪፥፱–፲፬)።
-
ሰለሞን ቤተመቅደስን ገነባ (፩ ነገሥ. ፮፥፩–፲፤ ፪ ዜና ፫፥፩)።
-
ባቢሎን ቤተመቅደሱን በ፭፻፹፯ ም.ዓ. ደመሰሱት (፪ ነገሥ. ፳፭፥፰–፱)።
-
ዘሩባቤል ቤተመቅደስን በ፭፻፲፭ ም.ዓ. እንደገና ገናባ (ዕዝ. ፫፥፰–፲፤ ፭፥፪፤ ፮፥፲፬–፲፮)።
-
ሄሮድስ የቤተመቅደስ አደባባይን አስፋፋ እናም በ፲፯ ም.ዓ. ቤተመቅደስን እንደገና መገንባት ጀመረ። ኢየሱስ በህጻንነቱ በእዚህ ቀረበ (ሉቃ. ፪፥፳፪–፴፱)።
-
በ፲፪ አመቱ ኢየሱስ በቤተመቅደስ አስተማረ (ሉቃ. ፪፥፵፩–፶)።
-
ኢየሱስ ቤተመቅደስን አጸዳ (ማቴ. ፳፩፥፲፪–፲፮፤ ዮሐ. ፪፥፲፫–፲፯)።
-
ኢየሱስ በተለያዩ ጊዜዎች በቤተመቅደስ አስተማረ (ማቴ. ፳፩፥፳፫–፳፫፥፴፱፤ ዮሐ. ፯፥፲፬–፰፥፶፱)።
-
በቲቶ ስር ሮሜዎች ቤተመቅደስን በ፸ ዓ.ም. ደመሰሱ።
-
-
ጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ኢየሱስ ተሰቃየ፣ ተካደ፣ እናም ታሰረ (ማቴ. ፳፮፥፴፮–፵፮፤ ሉቃ. ፳፪፥፴፱–፶፬)።
-
ደብረ ዘይት ተራራ
-
ኢየሱስ የኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ መደምሰስን አስቀድሞ ነገረ። ስለዳግም ምፅዓት ደግሞም ተናገረ (ማቴ. ፳፬፥፫–፳፭፥፵፮፤ ደግሞም ጆ. ስ.—ማቴ ተመልከቱ)።
-
ከእዚህ ቦታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ አረገ (የሐዋ. ፩፥፱–፲፪)።
-
በጥቅምት ፳፬ ቀን ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.)፣ ሽማግሌው ኦርሰን ሀይድ ቅዱስ ምድርን ለአብርሐም ልጆች በዳግም መመለስ ቀደሰ።
-
-
የግዮን ምንጭ ሰለሞን እንደንጉስ ተቀባ (፩ ነገሥ. ፩፥፴፰–፴፱)። ሕዝቅያስ ከምንጩ ወደ ከተማው ውሀ ለማምጣት መንገድ አስቆፈረ (፪ ዜና ፴፪፥፴)።
-
የውኃው በር ዕዝራ የሙሴን ህግ ለህዝቡ አነበበ እናም ተረጎመ (ነሀ. ፰፥፩–፰)።
-
ሄኖም ሸለቆ ልጅ ከመሰዋት በተጨማሪ የሀሰት ጣዖት ሞሎክ አመለኩት (፪ ነገሥ. ፳፫፥፲፤ ፪ ዜና ፳፰፥፫)።
-
የቀያፋ ቤት ኢየሱስ በቀያፋ ቤት ተወሰደ (ማቴ. ፳፮፥፶፯–፷፰)። ጴጥሮስ ኢየሱስን ያውቅ እንደነበረ ካደ (ማቴ. ፳፮፥፷፱–፸፭)።
-
ታላቅ አዳራሽ በባህል ይህ ኢየሱስ የፋሲካ ምግብን የበላበት እና ቅዱስ ቁርባንን የጀመረበት ቦታ ነው (ማቴ. ፳፮፥፳–፴)። የሐዋሪያትን እግሮች አጠበ (ዮሐ. ፲፫፥፬–፲፯) እናም አስተማራቸው (ዮሐ. ፲፫፥፲፰–፲፯፥፳፮)።
-
የሄሮድስ ቤተመንግስት ክርስቶስ በሄሮድስ ፊት ቀረበ፣ ምናልባት በእዚህ ቦታ (ሉቃ. ፳፫፥፯–፲፩)።
-
ኢየሩሳሌም (የማይታወቅ ቦታ)
-
መልከ ጼዴቅ እንደ ሳሌም ንጉስ ገዛ (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰)።
-
ንጉስ ዳዊት የኢያቡሳውያን ከተማን አሸነፈ (፪ ሳሙ. ፭፥፯፤ ፩ ዜና ፲፩፥፬–፯)።
-
በ፭፻፹፯ ም.ዓ. ከተማው በባቢሎን ተደመሰሰ (፪ ነገሥ. ፳፭፥፩–፲፩)።
-
በበዓለ ኀምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ ብዙዎችን ሞላ (የሐዋ. ፪፥፩–፬)።
-
ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ታሰሩ እናም በሸንጎዎች ፊት ቀረቡ (የሐዋ. ፬፥፩–፳፫)።
-
ሐናንያ እና ሰጲራ ለጌታ ዋሹ እናም ሞቱ (የሐዋ. ፭፥፩–፲)።
-
ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ታሰሩ፣ ነገር ግን መልአክ ከእስር ቤት አዳናቸው (የሐዋ. ፭፥፲፯–፳)።
-
ሐዋሪያት ሰባት ሰዎች እንዲረዷቸው መረጡ (የሐዋ. ፮፥፩–፮)።
-
የእስጢፋኖስን ምስክርን አይሁዶች አስወገዱ፣ እናም እስኪሞት ድረስ ተወገረ (የሐዋ. ፮፥፰–፯፥፷)።
-
ያዕቆብ ሰማዕት ሆነ (የሐዋ. ፲፪፥፩–፪)።
-
መልአክ ጴጥሮስን ከእስር ቤት አወጣው (የሐዋ. ፲፪፥፭–፲፩)።
-
ሐዋሪያት የግርዘት ጉዳይን ወሰኑ (የሐዋ. ፲፭፥፭–፳፱)።
-
በቲቶ ስር ሮሜዎች ቤተመቅደስን በ፸ ዓ.ም. ደመሰሱ።
-