የጥናት እርዳታዎች
9. የብሉይ ኪዳን አለም


9. የብሉይ ኪዳን አለም

የመፅሐፍ ቅዱስ ካርታ ፱

ኮከስስ

የካስፒያን ባህር

አራራት ተራራ?

ብላክ ባህር

ኡራርቱ

ሖር

ትሮይ

ኬጢያውያን

ዑር?

ሐራን (ሁለቱ ወንዞች መካከል)

አሶር

ከርከሚሽ

መስጼጦምያ

ነነዌ

ኤፍራጥስ ወንዝ

አሦር

አርካድ

የዱራ ሜዳ

ሱሳ

የታይግረስ ወንዝ

ባቢሎን

ሩድ

ኪቲም (ቆጵሮስ)

ባቢሎን (ሰናዖር)

ሶርያ

ከፍቶር (ቀርጤስ)

ኤላም

ሲዶን

ፎኒሲያ

ደማስቆ

ባቢሎን

ጢሮስ

የአረብ በረሀ

ዑር?

ኪኔሬት ባሕር (ገሊላ)

መጊዶ

ታላቅ ባህር (የሜድትሬኒያን ባህር)

ኢየሩሳሌም

የበታች ባህር (የፋርስ ባህረ ሰሌጣ)

ከነዓን

የጨው ባሕር (የሞት ባህር)

ቤርሳቤህ

የናይል ሸለቅ

ጌሴም

ምድያም

የፉጥ በረሀ

ዔጽዮንጋብር

ግብፅ

አባይ

የሲና ተራራ? (ኮሬብ)

ቀይ ባህር

ኪሎ ሜትር

0100200300400

ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ

1 2 3 4

1

2

2

3

4

5

6

7

8

9

10

11

12

13

14

15

16

17

  1. አራራት ተራራ በባህል የኖኅ መርከብ ያረፈበት ቦታ (ዘፍጥ. ፰፥፬)። እርግጠኛው ቦታ አይታወቅም።

  2. ዑር በኤፍራጥስ ወንዝ መጀመሪያ የሚገኝ የአብርሐም የመጀመሪያ መኖሪያ ቦታ፣ በእዚህም መስዋዕት ሊሆን ነበር፣ የያህዌ መልአክን አየ፣ እናም ኡሪም እና ቱሚምን ተቀበለ (ዘፍጥ. ፲፩፥፳፰–፲፪፥፩አብር. ፩፫፥፩)። (ደግሞም በሰሜን መስጼጦምያ ውስጥ የሚገኘውን የዑር ምትክ ቦታን ተመልከቱ።)

  3. ባቢሎን (ሰናዖር) መጀመሪያ በካም ልጅ በኩሽ እና በናምሩድ የተሰፈረበት ቦታ። በሰናዖር ሚዳዎች ውስጥ በባቢሎን ማማ ዘመን ይሬዳውያን የመጡበት ቦታ። በኋላም የባቢሎን የክልል ዋና ከተማ እና የባቢሎን ንጉሶች፣ በተጨማሪም ኢየሩሳሌም ከተደመሰሰች በኋላ ብዙ አይሁዶችን በምርኮ ወደ ከተማዋ የወሰደው የናቡከደነዖር፣ መኖሪያ (፭፻፹፯ ም.ዓ.)። አይሁዶችን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተመቅደስን እንዲገነቡ እስከፈቀደላቸው የንጉስ ቂሮስ ጊዜ ድረስ ለ፸ አመት አይሁዶች በምርኮ ቀሩ። ነቢዩ ዳንኤል ደግሞም በናቡከደነዖር፣ ብልጣሶር፣ እና በዳርዮስ ቀዳማዊ ስር ኖረ (ዘፍጥ. ፲፥፲፲፩፥፩–፱፪ ነገሥ. ፳፬–፳፭ኤር. ፳፯፥፩–፳፱፥፲ሕዝ. ፩፥፩ዳን. ፩–፲፪ኦምኒ ፩፥፳፪ኤተር ፩፥፴፫–፵፫)።

  4. ሱሳ በዳርዮስ ቀዳማዊ (ታላቁ ዳርዮስ)፣ ዘርዘስ (አርጤክስስ)፣ እና አርጤክስስ ስር የፋርሳዊው ግዛት ዋና ከተማ ነበረች። በብርቱነቷ እና በእምነቷ የአይሁድ ህዝቦችን ያዳነችው የንግስት አስቴር መኖሪያም ነበር። ዳንኤል እናም በኋላም ነህምያ በእዚህ ቦታ አገለገሉ (ነሀ. ፩፥፩፪፥፩አስቴ. ፩፥፩ዳን. ፰፥፪)።

  5. የዱራ ሜዳ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ በናቡከደነፆር የተሰራውን የወርቅ ምስልን ለማምለክ እምቢ ሲሉ ወደ እቶን እሳት ተጣሉ፤ የእግዚአብሔር ልጅ አዳናቸው፣ እናም ከእቶን እሳት ምንም ሳይጎዱ ወጡ (ዳን. ፫)።

  6. አሶር አሦር በነነዌ የምትከተል የአሶር ዋና ከተማ። በ፯፻፳፩ ም.ዓ.፣ የአሶር ገዢዎች ስልምናሶር አምስተኛው እና ሳርጎን ሁለተኛው የእስራኤልን የሰሜን ግዛት አሸነፈ እናም አስር ጎሳዎች በምርኮ ወሰዱ (፪ ነገሥ. ፲፬–፲፭፲፯–፲፱)። አሶር በባቢሎን እስከተሸነፈችበት እስከ ፮፻፲፪ ም.ዓ. ድረስ ይሁዳን ታስፈራራ ነበር።

  7. ነነዌ የአሶር ዋና ከተማ። አሶር የይሁዳን ምድር በሕዝቅያስ ግዛት እና በነቢዩ ኢሳይያስ ጊዜ አጠቃች። የይሁዳ ዋና ከተማ መልአክ ፻፹፭ ሺህ የአሶር ወታደሮችን በመምታቱ ምክንያት የይሁዳ ዋና ከተማ ኢየሩሳሌም በተአምራት ዳነች (፪ ነገሥ. ፲፱፥፴፪–፴፯)። ጌታ ነቢዩ ዮናስን ይህችን ከተማ ንስሀ እንድትገባ እንዲጠራ ነገረው (ዮና. ፩፥፪፫፥፩–፬)።

  8. ሐራን አብርሐም ወደ ከነዓን ከመሄዱ በፊት በእዚህ ቦታ ሰፈረ። የአብርሐም አባት እና ወንድም በእዚህ ቦታ ቀሩ። ርብቃ (የይስሐቅ ባለቤት)፣ ራሔል፣ ልያ፣ ባላ፣ እና ዘለፋ (የያዕቆብ ሚስቶች) ከእዚህ አካባቢ የመጡ ነበሩ (ዘፍጥ. ፲፩፥፴፩–፴፪፳፬፥፲፳፱፥፬–፮አብር. ፪፥፬–፭)።

  9. ከርከሚሽ በእዚህ ቦታ ፈርዖን ኒካዑ በናቡከደነፆር ተሸነፈ፣ ይህም በከነዓን የነበራትን የግብፅ ሀይል ፈጸመ (፪ ዜና ፴፭፥፳–፴፮፥፮)።

  10. ሲዶን ይህ ከተማ የተመሰረተው በካም የልጅ ልጅ ሲዶን ነበር፣ እናም የከነዓን የደቡብ ከተማ ነው (ዘፍጥ. ፲፥፲፭–፳)። ይህም ወደ እስራኤል በኣልን ማምለክ ያስተዋወቀችው የኤልዛቤል ቤት ነበር (፩ ነገሥ. ፲፮፥፴–፴፫)።

  11. ጢሮስ ይህችም በአሶር ውስጥ አስፈላጊ የንግድ እና የባህር ወደብ ከተማ ነበረች። የጢሮስ ኪራም እንጨት እና ወርቅ እንዲሁም ባለሟተኞች ሰለሞንን ቤተመቅደሱን ሲሰራ እንዲረዱት ላከ (፩ ነገሥ. ፭፥፩–፲፣ ፲፰፱፥፲፩)።

  12. ደማስቆ አብርሐም ሎጥን ከእዚህ ቦታ አጠገብ አዳነው። ይህችም የአሶር ዋና ከተማ ነበረች። በንጉስ ዳዊት ዘመነ መንግስት፣ እስራኤላውያን ይህችን ከተማ አሸነፉ። ኤልያስ አዛሄል የደማስቆ ንጉስ እንዲሆን ቀባው (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፬–፲፭፪ ሳሙ. ፰፥፭–፮፩ ነገሥ. ፲፱፥፲፭)።

  13. ከነዓን አብርሐም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ እናትውልዶቻቸው ይህን ምድር እንደ ዘለአለማዊ ውርስ ተሰጣቸው (ዘፍጥ. ፲፯፥፰፳፰)።

  14. የሲና ተራራ (ኮሬብ) ጌታ ሙሴ በሚነድ ቍጥቋጦ አነጋገረው (ዘፀአ. ፫፥፩–፪)። ሙሴ ህግ እና አስርቱ ቃላት ተሰጥተውት ነበር (ዘፀአ. ፲፱–፳)። ጌታ ከኤልያስ ጋር በትንሽ የዝምታ ድምፅ አነጋገረው (፩ ነገሥ. ፲፱፥፰–፲፪)።

  15. ዔጽዮንጋብር ንጉስ ሰለሞን በዔጽዮንጋብር “የባህር ሀይል መርከብ” ገንብቶ ነበር (፩ ነገሥ. ፱፥፳፮)። ምናልባት የሰለሞንን ታዋቂነት ከሰማች በኋላ የሳባ ንግስት የመጣችው በእዚህ የባህር ወደብ ላይ ነው (፩ ነገሥ. ፲፥፩–፲፫)።

  16. ግብፅ አብርሐም በዑር በነበረው ታላቅ ርሀብ ምክንያት ወደ እዚህ ተጓዘ (አብር. ፪፥፩፣ ፳፩)። ጌታ አብርሐምን ለግብጾች እርሱ የገለጸለትን እንዲያስተምር ነገረው (አብር. ፫፥፲፭)። የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ባርነት ከሸጡት በኋላ (ዘፍጥ. ፴፯፥፳፰)፣ ዮሴፍ በእዚህ ቦታ የጲጥፋራ ቤት ገዢ ሆነ። ወደ እስር ቤት ተጣለ። የፈርዖኑን ህልም ተረጎመ እናም በግብፅ ውስጥ የስልጣን ሀላፊነት ተሰጠው። ዮሴፍ እና ወንድሞቹ እንደገና ተገናኙ። ያዕቆብ እና ቤተሰቡ ወደ እዚህ መጡ (ዘፍጥ. ፴፱–፵፮)። የእስራኤል ልጆች በግብፅ በቆዩበት ጊዜ በጌሤም ውስጥ ይኖሩ ነበር (ዘፍጥ. ፵፯፥፮)።

    እስራኤላውያን ተባዙ “እናም አጅግም ጸኑ”፤ ከእዚያም በኋላ ግብጻዊያን ባሪያዎች እንዲሆኑ አደረጓቸው (ዘፀአ. ፩፥፯–፲፬)። ከብዙ ወረርሽኝ በኋላ ፈሮዖኑ እስራኤል ከግብጽ እንዲወጡ ፈቀደላቸው (ዘፀአ. ፲፪፥፴፩–፵፩)። ኤርምያስ ወደ ግብጽ ተወሰደ (ኤር. ፵፫፥፬–፯)።

  17. ከፍቶር (ቀርጤስ) የጥንት የሚኖዓን ምድር ነበር።