የጥናት እርዳታዎች
13. የሐዋርያው ጳውሎስ የሚስዮን ጉዞ


13. የሐዋርያው ጳውሎስ የሚስዮን ጉዞ

የመፅሐፍ ቅዱስ ካርታ ፲፫

ካርታ

የመጀመሪያ ጉዞ

ሁለተኛ ጉዞ

ሶስተኛ ጉዞ

ወደ ሮሜ ጉዞ

ጣልያን

ብላክ ባህር

ሮሜ

መቄዶንያ

ጳንጦስ

ሦስት ማደሪያ

ቢታንያ

አፍዩስ ፋሩስ

ተሰሎንቄ

ፊልጶስ

ፑቲዮሉስ

ጢሮአዳ

ቤርያ

ገላትያ

ሳሞጥራስ

ሚስያ

እስያ

ፐርጋሙም

ቀጰዶቅያ

አንጾኪያ

ሉድ

ፍርግያም

ሰምርኔስ

ኢቆንዮን

ጠርሴስ

ኪዩ

ኤፌሶን

ጲስድያ

ልስጥራ

አቴና

ቆሮንቶስ

ሎዶቅያ

ሬጊዩም

አካይያ

ሚሊጢን

ጵንፍልያም

ደርቤ

ሉቅያ

ጴርጌ

አንጾኪያ

ፍጥሞ

ቀሬና

ሰራኩስ

ሙራ

ቀኒዶስ

ሩድ

ቆጵሮስ

ስልማና

መላጥያ (ማልታ)

ቀርጤስ

ጳፉ

ሲዶን

ሶርያ

ጢሮስ

መልካም ወደብ

ፎኒሲያ

ደማስቆ

ፕቶሌማስ

የሜድትሬኒያን ባህር

ቂሣርያ

ሰማርያ

ኢዮጴ

ኢየሩሳሌም

ጋዛ

ቀሬና

እስክንድርያ

ግብፅ

ፉጥ

ኪሎ ሜትር

0100200300400

ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ

1 2 3 4

1

2

3

4

5

6

7

8

9

10

11

12

13

14

15

16

17

18

19

20

21

22

23

24

25

26

27

  1. ጋዛ ፊልጶስ ወደ ጋዛ ሲጓዝ ስለክርስቶስ ሰበከ እናም ኢትዮጵያዊ ጃንደረባን አጠመቀ (የሐዋ. ፰፥፳፮–፴፱)።

  2. ኢየሩሳሌም በኢየሩሳሌም ስለነበሩት ድርጊቶች ካርታ 12 ተመልከቱ።

  3. ኢዮጴ ጴጥሮስ እግዚአብሔር ለአህዛቦች ንስሀ የመግባት ስጦታን እንደሰጠ ራዕይ ተቀበለ (የሐዋ. ፲፲፩፥፭–፲፰)። ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት አስነሳ (የሐዋ. ፱፥፴፮–፵፪)።

  4. ሰማርያ ፊልጶስ በሰማርያ ውስጥ ሰበከ (የሐዋ. ፰፥፭–፲፫)፣ እናም ጴጥሮስ እና ዮሐንስ በኋላም በእዚህ ቦታ አስተማሩ (የሐዋ. ፰፥፲፬–፳፭)። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ከሰጡ በኋላ፣ አስማተኛው ስምዖን ይህን ስጦታ ከእነርሱ ለመግዛት ፈለገ (የሐዋ. ፰፥፱–፳፬)።

  5. ቂሣርያ መልአክ ለመቶ አለቃው ቆርኔሌዎስ ካገለገለ በኋላ፣ ጴጥሮስ እንዲጠመቅ ፈቀደለት (የሐዋ. ፲)። በእዚህ ቦታ ጳውሎስ በአግሪጳ ፊት ተከራከረ (የሐዋ. ፳፭–፳፮፤ ደግሞም ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፳፬–፳፭)።

  6. ደማስቆ ኢየሱስ ለሳዖል ታየ (የሐዋ. ፱፥፩–፯)። ሐናንያ ሳዖል ለማየት እንዲችል ካደረገ በኋላ፣ ሳዖል ተጠመቀ እናም አገልግሎቱን ጀመረ (የሐዋ. ፱፥፲–፳፯)።

  7. አንጾኪያ (በአሶር ውስጥ) በእዚህ ቦታ ደቀመዛሙርት ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን ተብለው ተጠሩ (የሐዋ. ፲፩፥፳፮)። አጋቦስ ስለርዓብ ተነበየ (የሐዋ. ፲፩፥፳፯–፳፰)። በአንጾኪያ ስለግርዘት በሚመለከት ጥል ተጀመረ (የሐዋ. ፲፬፥፳፮–፳፰፲፭፥፩–፱)። በአንጾኪያ ጳውሎስ ከሲላስ፣ በርናባስ፣ እና ይሁዳ በርስያን ጋር ሁለተኛውን ሚስዮን ጀመረ (የሐዋ. ፲፭፥፳፪፣ ፴፣ ፴፭)።

  8. ጠርሴስ የጳውሎስ ቤት ከተማ፤ ጳውሎስ በወንድሞች ህይወቱን ለመጠበቅ ወደ እዚህ ተልኮ ነበር (የሐዋ. ፱፥፳፱–፴)።

  9. ቆጵሮስ ከተሰደደ በኋላ፣ አንዳንድ ቅዱሳን ከእዚህ ምድር ሸሹ (የሐዋ. ፲፩፥፲፱)። ጳውሎስ በመጀመሪያው የሚስዮን ጉዞው በቆጵሮስ በኩል ተጓዘ (የሐዋ. ፲፫፥፬–፭)፣ በኋላም በርናባስና ማርቆስ በእዚህ ተጓዙ (የሐዋ. ፲፭፥፴፱)።

  10. ጳፉ ጳውሎስ በእዚህ ቦታ አስማተኛን ረገመ (የሐዋ. ፲፫፥፮–፲፩)።

  11. ደርቤ ጳውሎስ እና በርናባስ በዚህ ከተማ ወንጌልን ሰበኩ (የሐዋ. ፲፬፥፮–፯፣ ፳–፳፩)።

  12. ልስጥራ ጳውሎስ አካለ ስንኩልን ሲፈውስ፣ እርሱ እና በርናባስ እንደ አምላኮች ሰላምታ ተሰጣቸው። ጳውሎስ ተናገረ እናም የሞተ መሰላቸው ነገር ግን ተነሳ እናም መስበክን ቀጠለ (የሐዋ. ፲፬፥፮–፳፩)። የጢሞቴዎስ ቤት (የሐዋ. ፲፮፥፩–፫)።

  13. ኢቆንዮን በመጀመሪያው ሚስዮናቸው፣ ጳውሎስ እና በርናባስ በእዚህ ቦታ ሰበኩ እናም ለመወገር አስፈራርተዋቸው ነበር (የሐዋ. ፲፫፥፶፩–፲፬፥፯)።

  14. ሎዶቅያ እና ቈላስይስ ሎዶቅያ ጳውሎስ ከጎበኛቸው እና ደብዳቤ ከተቀበለባቸው የቤተክርስቲያኗ ቅርንጫፎች አንዱ ነው (ቄላ. ፬፥፲፮)። በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰባት ከተማዎች አንዱም ነው (ሌሎቹም ኤፌሶን፣ ሰምርኔስ፣ ጴርጋሞን፣ ትያጥሮን፣ ሰርዴስ፣ እና ፊልድልፍያ ናቸው፣ ራዕ. ፩፥፲፩ ተመልከቱ)። ቈላስይስ ከሎዶቅያ በ ፲፰ ኪሎ ሜትር ወደ ምስራቅ ይገኛል። ጳውሎስ በእዚህ ለሚኖሩት ቅዱሳን ጻፈ።

  15. አንጾኪያ (በጲስድያ ውስጥ) በመጀመሪያው ሚስዮናቸው፣ ጳውሎስና በርናባስ አይሁዶችን ክርስቶስ ከዳዊት ዘር እንደመጣ አስተማሩ። ጳውሎስ ወንጌሉን ለእስራኤል አቀረበ፣ ከእዚያም ለአህዛብ አቀረበ። ጳውሎስ እና በርናባስ ተሰደዱ (የሐዋ. ፲፫፥፲፬–፶)።

  16. ሚሊጢን በሶስተኛው ሚስዮኑ ላይ እያለ፣ ጳውሎስ የቤተክርስቲያኗን ካህናት “ጨካኞች ተኩላዎች” በመንጋዎች መካከል እንደሚገቡ አስጠናቀቀ (የሐዋ. ፳፥፳፱–፴፩)።

  17. ፍጥሞ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የነበሩትን ራዕዮች በተቀበለበት ጊዜ ዮሐንስ በእዚህ ደሴት ላይ እስረኛ ነበር (ራዕ. ፩፥፱)።

  18. ኤፌሶን አጵሎስ በእዚህ ቦታ በሀይል ሰበከ (የሐዋ. ፲፰፥፳፬–፳፰)። ጳውሎስ፣ በሶስተኛው ሚስዮን፣ በኤፌሶን ውስጥ ለሁለት አመት አስተማረ፣ ብዙ ሰዎችን ቀየረ (የሐዋ. ፲፱፥፲፣ ፲፰)። በእዚህም መንፈስ ቅዱስ ስጦታን እጆችን በመጫን ሰጠ (የሐዋ. ፲፱፥፩–፯) እናም ክፉ መንፈሶችን ከማስወጣት በተጨማሪ ብዙ ታዕምራቶችን ሰራ (የሐዋ. ፲፱፥፰–፳፩)። አርጤምስ በጳውሎስ ላይ ብጥብጥ አመጣ (የሐዋ. ፲፱፥፳፪–፵፩)። የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ክፍልም በኤፌሶን ስላለው ቤተክርስቲያን ነው (ራዕ. ፩፥፲፩)።

  19. ጢሮአዳ ጳውሎስ በእዚህ ቦታ በሁለተኛው ሚስዮን በሚጓዙበት ጊዜ፣ እርዳታ የሚጠይቅ ሰው በመቄዶንያ ውስጥ በራዕይ አየ (የሐዋ. ፲፮፥፱–፲፪)። ለሶስተኛው ሚስዮን በእዚህ ቦታ እያለ፣ ጳውሎስ አውጤኪስን ከሞት አስነሳ (የሐዋ. ፳፥፮–፲፪)።

  20. ፊልጶስ ጳውሎስ፣ ሲላስ፣ እና ጢሞቴዎስ ሉድ የምትባል ሴትን ቀየሩ፣ ክፉ መንፈስን አስወጡ፣ እናም ተደበደቡ (የሐዋ. ፲፮፥፲፩–፳፫)። ከእስር ቤት ለማምለጥ መለኮታዊ እርዳታ ተቀበሉ (የሐዋ. ፲፮፥፳፫–፳፮)።

  21. አቴና ጳውሎስ፣ ወደ አቴና በሄደው በሁለተኛው ሚስዮኑ፣ በማርስ ኮረብታ (አርዮስፋጎስ) ላይ “ስለማይታወቅ አምላክ” ሰበከ (የሐዋ. ፲፯፥፳፪–፴፬)።

  22. ቆሮንቶስ ጳውሎስ ለሁለተኛ ሚስዮኑ ወደ ቆሮንቶስ ሄደ፣ በእዚህም ከአቂላ ና ከጵርስቅላ ጋር ኖረ። በእዚህም ሰበከ እናም ብዙ ሰዎችን አጠመቀ (የሐዋ. ፲፰፥፩–፲፰)። ከቆሮንቶስ፣ ጳውሎስ ወደ ሮሜ መልእክትን ጻፈ።

  23. ተሰሎንቄ ጳውሎስ በሁለተኛው የሚስዮን ጉዞው በእዚህ ቦታ ሰበከ። የሚስዮን ቡድኑ አይሁዶች ደህንነታቸውን ካስፈራሯቸው በኋላ ወደ ቤርያ ሄዱ (የሐዋ. ፲፯፥፩–፲)።

  24. ቤርያ ጳውሎስ፣ ሲላስ፣ እና ጢሞቴዎስ በጳውሎስ ሁለተኛ ጉዞ የሚያስተምሯቸው ልዑል ነፍሶችን አገኙ (የሐዋ. ፲፯፥፲–፲፫)።

  25. መቄዶንያ ጳውሎስ በሁለተኛው እና በሶስተኛው ጉዞው በእዚህ ቦታ አስተማረ (የሐዋ. ፲፮፥፱–፵፲፱፥፳፩)። ጳውሎስ ለእርሱ እና በኢየሩሳሌም ላሉት ደሀ ቅዱሳን ለሰጡት ለመቄዶንያ ቅዱሳንን ደግነታቸውን አመሰገናቸው (ሮሜ ፲፭፥፳፮፪ ቆሮ. ፰፥፩–፭፲፩፥፱)።

  26. መላጥያ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሲሄድ በእዚህ ደሴት ላይ መርከቡ ተሰበረ (የሐዋ. ፳፮፥፴፪፳፯፥፩፣ ፵፩–፵፬)። በእባብ ቢነከስም አልተጎዳም እናም በመላጥያ የታመሙትን ሁሉ ፈወሰ (የሐዋ. ፳፰፥፩–፱)።

  27. ሮሜ ጳውሎስ በቤት ውስጥ ታስሮ እያለ ለሁለት አመት በእዚህ ቦታ ሰበከ (የሐዋ. ፳፰፥፲፮–፴፩)። በሮሜ ውስጥ ታስሮ እያለ መልእክቶች፣ ወይም ደብዳቤዎች፣ ለኤፌሶን፣ ለፊልጵስዩስ፣ እና ቈላስይስ እናም ለጢሞቴዎስና ለፊልሞና ጻፈ። ጴጥሮስ የመጀመሪያ መልእክቱን ኔሮ ክርስቲያኖችን በ፷፬ ዓ.ም. ካሳደደ በኋላ ምናልባት ሮሜ ከሆነው “ከባቢሎን” ጻፈ። ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በእዚህ ቦታ ሰማዕት እንደሆኑ ይታመናል።