የጥናት እርዳታዎች
11. ቅዱስ ምድር በአዲስ ኪዳን ዘመናት


11. ቅዱስ ምድር በአዲስ ኪዳን ዘመናት

ምስል
የመፅሐፍ ቅዱስ ካርታ ፲፩

ቁልፍ

የፖለቲካ ገደብ መስመር

ሲዶን

ሳቢላኒስ

ሰራፕታ

ሊባኖስ ተራራዎች

ደማስቆ

ሊታኒ

ሶርያ

አርሞንዔም ተራራ

ፋርፋ

ጢሮስ

ፎኒሲያ

ፊልጶስ ቂሣርያ

ሁሌኽ ሸልቆ

ገሊላ

ፕቶሌማስ (ዓኮን)

ኮራዚ

ቤተ ሳይዳ

ቅፍርናሆም

ቂሶን

ቃና

መጌዶል

የገሊላ ባህር (ኪኔሬት)

ቀርሜሎስ ተራራ

ናዝሬት

ጥብርያዶስ

ታቦር ተራራ

ያርሙክ

ናይን

አስር ከተማ

ቂሣርያ

የጊልቦዓ ተራራ

አስር ከተማ

ሰማርያ

ሳሌም?

ሰማርያ

ኤኢኖን?

የሼረን ሜዳ

ሲካር

ጌባል ተራራ

ያቦቅ

ኢዮጴ

ገሪዛን ተራራ

አርማትያስ?

ኤሎን

ቤቴል

የዮርዳኖስ ወንዝ

ጴሬአ

ፊልድልፍያ

ኢያሪኮ

ታላቅ ባህር (የሜድትሬኒያን ባህር)

አዛጦን

ሶሬቅ

ኤማሁስ

ቤተ ራባ

ኢየሩሳሌም

ደብረ ዘይት ተራራ

ቤተ ፋጌ

ቢታንያ

ኩራም

የሞአብ ሜዳ

የናባ ተራራ

አስከሎን

ኤላ

ቤተ ልሔም

ይሁዳ

ጋዛ

ኬብሮን

ማኬሩስ

ጌራራ

ኢዱሜአ

የሞት ባህር

አሮኖን

ቦሦር

ቤርሳቤህ

መሳዳ

የይሁዳ ምድረበዳ

ናባቴአ

ዘሬድ

ኪሎ ሜትር

0204060

ሀ ለ ሐ መ

1 2 3 4 5 6 7 8

1

1

2

2

3

4

5

6

7

8

9

10

11

12

13

14

15

16

17

  1. ጢሮስ እና ሲዶን ኢየሱስ ኮራዚና ቤተ ሳይዳን ከጢሮስ እና ሲዶን ጋር አነጻጸረ (ማቴ. ፲፩፥፳–፳፪)። የአህዛብ ሴትን ሴት ልጅን ፈወሰ (ማቴ. ፲፭፥፳፩–፳፰)።

  2. የመለወጫ ተራራ ኢየሱስ በጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ ፊት ተለወጠ፣ እና እነርሱም የመንግስት ቁልፎችን ተቀበሉ (ማቴ. ፲፯፥፩–፲፫)። (አንዳንዶች የመለወጫ ተራራ አርሞንዔም ተራራ ነው ብለው ያምናሉ፤ ሌሎችም የታቦር ተራራ ነው ብለው ያምናሉ)።

  3. ፊልጶስ ቂሣርያ ጴጥሮስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መሰከረ እናም የመንግስት ቁልፎችንም ቃል ተገባለት (ማቴ. ፲፮፥፲፫–፳)። ኢየሱስ የእራሱን ሞት እና ትንሳኤ አስቀድሞ ተናገረ (ማቴ. ፲፮፥፳፩–፳፰)።

  4. የገሊላ ክልል ኢየሱስ አብዛኛውን ህይወቱን እና አገልግሎቱን በገሊላ አሳለፈ (ማቴ. ፬፥፳፫–፳፭)። በእዚህም የተራራ ስብከትን ሰጠ (ማቴ. ፭–፯)፤ ለምጻሞችን ፈወሰ (ማቴ. ፰፥፩–፬)፤ እናም አስራ ሁለት ሐዋሪያትን መረጠ፣ ወይም ሾመ፣ እናም ላከ፣ ከእነርሱም መካከል የአስቆሮቱ ይሁዳ ከገሊላ የመጣ አልነበረም (ማር. ፫፥፲፫–፲፱)። በገሊላ ውስጥ ከሞት የተነሳው ክርስቶስ በሐዋሪያት ታየ (ማቴ. ፳፰፥፲፮–፳)።

  5. የገሊላ ባህር በኋላም የጥብርያዶስ ባህር ተብሎ የተጠራው፥ ኢየሱስ ከጴጥሮስ ጀልባ አስተማረ (ሉቃ. ፭፥፩–፫) እናም ጴጥሮስን፣ እንድርያስን፣ ያዕቆብን የሰው አጥማጆች እንዲሆኑ ጠራቸው (ማቴ. ፬፥፲፰–፳፪ሉቃ. ፭፥፩–፲፩)። አውሎ ንፋስንም ጸጥ አስደረገ (ሉቃ. ፰፥፳፪–፳፭)፣ ምሳሌዎችን ከጀልባ አስተማረ (ማቴ. ፲፫)፣ በባህር ላይ ተራመደ (ማቴ. ፲፬፥፳፪–፴፪)፣ እናም ከትንሳኤም በኋላ በደቀመዛሙርቱ ታየ (ዮሐ. ፳፩)።

  6. ቤተ ሳይዳ ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ እና ፊልጶስ በቤተ ሳይዳ ውስጥ ተወልደው ነበር (ዮሐ. ፩፥፵፬)። በቤተ ሳይዳ አጠገብ ኢየሱስ ከሐዋሪያት ጋር በሚስጥር ሄደ። ህዝብም ተከተሉት፣ እና ፭ ሺህን መገበ (ሉቃ. ፱፥፲–፲፯ዮሐ. ፮፥፩–፲፬)። በእዚህም ቦታ ኢየሱስ አይነ ስውር ሰውን ፈወሰ (ማር. ፰፥፳፪–፳፮)።

  7. ቅፍርናሆም ይህም የጴጥሮስ ቤት ነበር (ማቴ. ፰፥፭፣ ፲፬)። ማቴዎስ የኢየሱስ “የእርሱ ከተማ” ብሎ በጠራው በቅፍርናሆም፣ ኢየሱስ ሽባ የሆነውን ሰው ፈወሰ (ማቴ. ፱፥፩–፯ማር. ፪፥፩–፲፪)፣ የአስር አለቃን አዳነ፣ የጴጥሮስ ሚስት እናትን ፈወሰ (ማቴ. ፰፥፭–፲፭)፣ ማቴዎስ ከሐዋሪያቱ መካከል አንዱ እንዲሆን ጠራው (ማቴ. ፱፥፱)፣ አይነ ስውር አይኖችን ከፈተ፣ ዲያቦስን አስወጣ (ማቴ. ፱፥፳፯–፴፫)፣ እጁ የሰለለች ሰውን በሰንበት ፈወሰ (ማቴ. ፲፪፥፱–፲፫)፣ የህይወት እንጀራ ስብከትን ሰጠ (ዮሐ. ፮፥፳፪–፷፭)፣ እና ጴጥሮስን ከአሳ አፍ ገንዘብ እንዲያመጣ በመንገር፣ ቀረጥን ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነ (ማቴ. ፲፯፥፳፬–፳፯)።

  8. መጌዶል ይህም የመጌዶል ማርያም ቤት ነበር (ማር. ፲፮፥፱)። ኢየሱስ ፬ ሺህ ህዝቦችን ከመገበ በኋላ ወደ እዚህ መጣ (ማቴ. ፲፭፥፴፪–፴፱)፣ እናም ፈሪሳዊ እና ሰዱቃውያን ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁ (ማቴ. ፲፮፥፩–፬)።

  9. ቃና ኢየሱስ ውሀን ወደ ወይን ቀየረ (ዮሐ. ፪፥፩–፲፩) እና በቅፍርናሆም የነበረን የልዑል ሰው ልጅን ፈወሰ (ዮሐ. ፬፥፵፮–፶፬)። ቃና የናትናኤል ቤት ነበር (ዮሐ. ፳፩፥፪)።

  10. ናዝሬት ለማርያም እና ለዮሴፍ የተሰጠው ብስራት የነበረው በእዚህ ቦታ ነበር (ማቴ. ፩፥፲፰–፳፭ሉቃ. ፩፥፳፮–፴፰፪፥፬–፭)። ከግብፅ ከተመለሱ በኋላ፣ ኢየሱስ ልጅነቱን እና ወጣትነቱን በዚህ ቦታ አሳለፈ (ማቴ. ፪፥፲፱–፳፫ሉቃ. ፪፥፶፩–፶፪)፣ መሲህ እንደሆነ አስታወቀ፣ እናም በእርሱ ሰዎች ተወገደ (ሉቃ. ፬፥፲፬–፴፪)።

  11. ኢያሪኮ ኢየሱስ ለአይነ ስውር ሰው እይታን ሰጠ (ሉቃ. ፲፰፥፴፭–፵፫)። ከቀራጮች መካካል ዋና ከሆነው ከዘካርያስ ጋር በላ (ሉቃ. ፲፱፥፩–፲)።

  12. ቤተ ራባ መጥምቁ ዮሐንስ “በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” እንደሆነ መሰከረ (ዮሐ. ፩፥፲፱–፳፰)። ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀ እናም ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ እንደሆነ መሰከረ (ዮሐ. ፩፥፳፰–፴፬)።

  13. የይሁዳ ምድረበዳ መጥምቁ ዮሐንስ በምድረበዳ ሰበከ (ማቴ. ፫፥፩–፬)፣ በእዚህም ኢየሱስ ለአርባ ቀናት ጾመ እናም ተፈተነ (ማቴ. ፬፥፩–፲፩)።

  14. ኤማሁስ ከሞት የተነሳው ክርስቶስ በኤማሁስ መንገድ ላይ ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር ሄደ (ሉቃ. ፳፬፥፲፫–፴፪)።

  15. ቤተ ፋጌ ሁለት ደቀመዛሙርት ለኢየሱስ ውርንጫይቱን አመጡለት በዚህም ላይ ወደ ኢየሩሳሌም በድል ገባ (ማቴ. ፳፩፥፩–፲፩)።

  16. ቢታንያ ይህ የማርያም፣ የማርታ፣ እና የአልዓዛር ቤት ነበር (ዮሐ. ፲፩፥፩)። ማርያም የኢየሱስን ቃላት ሰማች፣ እናም ኢየሱስ ማርታን “መልካሙን እድልን” ስለመምረጥ ተናገረ (ሉቃ. ፲፥፴፰–፵፪)፤ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው (ዮሐ. ፲፩፥፩–፵፬)፤ እናም ማርያም የኢየሱስን እግር ቀባች (ማቴ. ፳፮፥፮–፲፫ዮሐ. ፲፪፥፩–፰)።

  17. ቤተ ልሔም ኢየሱስ ተወልዶ በግርግም ውስጥ ተኛ (ሉቃ. ፪፥፩–፯)፤ መላእክት ለእረኞች የኢየሱስ መወለድን አወጁ (ሉቃ. ፪፥፰–፳)፤ ሰብአ ሰገል በኢየሱስ ኮኮብ ተመርተው ነበር (ማቴ. ፪፥፩–፲፪)፤ እናም ሂሮድስ ልጆችን ገደለ (ማቴ. ፪፥፲፮–፲፰)።

አትም