የካርታዎች ዝርዝር በካርታዎች ላይ አንድ ቦታን ለማግኘት ይረዳችኋል። እያንዳንዱ ቦታ የካርታ ቁጥር እና መጠቆሚያ በቁጥር እና በፊደል የተሰራ ነው። ለምሳሌ ረባት (አማን) ፩:መ፭ ተሰጥቷል፤ ይህም ካርታ ፩፣ አራት መአዘን መ፭ ማለት ነው። የቦታዎቹ ሌላ ስም በቅንፎች ውስጥ ተዘርዝረዋል፣ ለምሳሌ፣ ረባት (አማን)። ከስም በኋላ የሚገኝ የጥያቄ ምልክት በካርታው ላይ የሚታየው ቦታ ትክክል እንደሆነ የሚገመትበት እንጂ እርግጠኛ እንዳልሆነ ያመለክታል።