10. ከነዓን በብሉይ ኪዳን ዘመናት
-
ዳን (ሌሳ) ኢዮርብዓም የሰሜን መንግስት እንዲያመልኩት የወርቅ ጥጃ ሰራላቸው (፩ ነገሥ. ፲፪፥፳፮–፴፫)። ዳን የጥንት እስራኤል የሰሜን ገደብ ነው።
-
ቀርሜሎስ ተራራ ኤልያስ ከበኣል ካህናት ጋር ተፎካከረ እናም ሰማያትን ለዝናብ ከፈተ (፩ ነገሥ. ፲፰፥፲፯–፵፮)።
-
መጊዶ ብዙ ጦርነት የተዋጉበት ቦታ (መሳ. ፬፥፲፫–፲፮፤ ፭፥፲፱፤ ፪ ነገሥ. ፳፫፥፳፱፤ ፪ ዜና ፴፭፥፳–፳፫)። ሰለሞን መጊዶ ለመገንባት ቀረጥ መደበ (፩ ነገሥ. ፱፥፲፭)። የይሁዳ ንጉስ ኢዮስያስ ከግብፅ ፈሮዖን ኒካዑ ጋር በተዋጋበት ጊዜ ቆስሎ ሞተ (፪ ነገሥ. ፳፫፥፳፱–፴)። በጌታ ዳግም ምፅዓት፣ እንደ አርማጌዶን ጦርነት ክፍል በኢይዝራኤል ሸለቆ ታላቅ ጦርነት ይኖራል (ኢዩ. ፫፥፲፬፤ ራዕ. ፲፮፥፲፮፤ ፲፱፥፲፩–፳፩)። አርማጌዶን የሚባለው ስም በግሪክ ቋንቋ የተተረጎመ የዕብራውያን ሀር መጊዶ፣ ወይም የመጊዶ ተራራ ስም ነው።
-
ኢይዝራኤል ከሁሉም በላይ የለማ የእስራኤል ሸለቆ ጋር አንድ አይነት ስም ያለው እና ከሁሉም ታላቅ ከተማ ስም። የሰሜን መንግስት ንጉሶች በእዚህ ቦታ ቤተመንግስት ሰሩ (፪ ሳሙ. ፪፥፰–፱፤ ፩ ነገሥ. ፳፩፥፩–፪)። ክፉ የነበረችው ንግስት ኤልዛቤል በእዚህ ቦታ ኖረች እናም ሞተች (፩ ነገሥ. ፳፩፤ ፪ ነገሥ. ፱፥፴)።
-
ቤትሳን እስራኤል ከነዓናውያንን በእዚህ ቦታ ተቋቋመች (ኢያ. ፲፯፥፲፪–፲፮)። የሳኦል ሰውነት በእዚህ ምሽግ ግድግዳ ላይ ታስሮ ነበር (፩ ሳሙ. ፴፩፥፲–፲፫)።
-
ዶታይን ዮሴፍ በወንድሞቹ ወደ ባሪያነት ተሸጠ (ዘፍጥ. ፴፯፥፲፯፣ ፳፰፤ ፵፭፥፬)። ኤልሳዕ በፈረሶች እና በሰረገላ የተሞላ ተራራ ራዕይ አየ (፪ ነገሥ. ፮፥፲፪–፲፯)።
-
ሰማርያ የሰሜን መንግስት ዋና ከተማ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፳፬–፳፱)። ንጉስ አሀብ የበኣል ቤተመቅደስ ሰራ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፴፪–፴፫)። ኤልያስ እና ኤልሳዕ አገለገሉ (፩ ነገሥ. ፲፰፥፪፤ ፪ ነገሥ. ፮፥፲፱–፳)። በ፯፻፳፩ ም.ዓ. አሶር የአስር ጎሳዎች መያዝን በመፈጸም አሸነፈቻት (፪ ነገሥ. ፲፰፥፱–፲)።
-
ሴኬም አብርሐም መሰዊያ ገነባ (ዘፍጥ. ፲፪፥፮–፯)። ያዕቆብ በእዚህ ቦታ አጠገብ ኖረ። ስምዖን እና ሌዊ የከተማዋን ወንዶች በሙሉ ገደሉ (ዘፍጥ. ፴፬፥፳፭)። ኢያሱ “በእዚህ ቀን” እግዚአብሔርን ለማገልገል “ምረጡ” ያለበት ማበረታቻ የነበረው በሴኬም ነበር (ኢያ. ፳፬፥፲፭)። ኢዮርብዓም የሰሜን መንግስት የመጀመሪያውን ከተማ በእዚህ ቦታ መሰረተ (፩ ነገሥ. ፲፪)።
-
ጌባል ተራራ እና ገሪዛን ተራራ ኢያሱ እስራኤልን በእነዚህ ሁለት ተራራዎች ላይ ከፋፈላቸው—የህጉ በረከቶች ከገሪዛ ተራራ ታወጀ፣ እርግማኑም ከጌልባ ተራራ መጣ (ኢያ. ፰፥፴፫)። ሳምራዊዎች በኋላም በገሪዛ ላይ ቤተመቅደስ ገነቡ (፪ ነገሥ. ፲፯፥፴፪–፴፫)።
-
ፓኒኤል ያዕቆብ ከጌታ መልእክተኛ ጋር በምሽት በሙሉ ታገለ (ዘፍጥ. ፴፪፥፳፬–፴፪)። ጌዴዎን የምድያማውያን ምሽግን ደመሰሰ (መሳ. ፰፥፭፣ ፰–፱)።
-
ኢዮጴ ዮናስ የነነዌ ሚስዮኑን ለማስወገድ ከእዚህ ቦታ ወደ ተርሴስ በመርከብ ተጓዘ (ዮና. ፩፥፩–፫)።
-
ሴሎ በመሳፍንት ዘመን፣ የእስራኤል ዋና ከተማ እና ታቦቱ ይገኝበት የነበረ ቦታ (፩ ሳሙ. ፬፥፫–፬)።
-
ቤቴል (ሎዛ) በእዚህ ቦታ አብርሐም ከሎጥ ጋር ተለያየ (ዘፍጥ. ፲፫፥፩–፲፩) እናም ራዕይ አየ (ዘፍጥ. ፲፫፤ አብር. ፪፥፲፱–፳)። ያዕቆብ ወደሰማይ የሚደርስ መሰላል ራዕይ አየ (ዘፍጥ. ፳፰፥፲–፳፪)። ለጊዜም ታቦት በእዚህ ቦታ ይገኝ ነበር (መሳ. ፳፥፳፮–፳፰)። ኢዮርብዓም የሰሜን መንግስት እንዲያመልኩት የወርቅ ጥጃ ሰራላቸው (፩ ነገሥ. ፲፪፥፳፮–፴፫)።
-
ገባዖን ኬጢያውያን ኢያሱን በማታለል ስምምነት እንዲገባ አደረገ (ኢያ. ፱)። ኢያሱ ጦርነትን እያሸነፈ እያለ ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ (ኢያ. ፲፥፪–፲፫)። ይህም የታቦት ለጊዜ የሚቀመጥበት ቦታ ነበር (፩ ዜና ፲፮፥፴፱)።
-
ጋዛ፣ አዛጦን፣ አስቀሎና፣ አቃሮን፣ ጌት (የፍልስጥኤማውያን አምስት ከተማዎች) በብዙ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከእነዚህ ከተማዎች እስራኤልን ያጠቁ ነበር።
-
ቤተ ልሔም ራሔል በእዚህ ቅርብ ነበር የተቀበረችው (ዘፍጥ. ፴፭፥፲፱)። ሩት እና ቦዓዝ በእዚህ ኖሩ (ሩት ፩፥፩–፪፤ ፪፥፩፣ ፬)። ይህም የዳዊት ከተማ ነበር (ሉቃ. ፪፥፬)።
-
ኬብሮን አብርሐም (ዘፍጥ. ፲፫፥፲፰)፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ (ዘፍጥ. ፴፭፥፳፯)፣ ዳዊት (፪ ሳሙ. ፪፥፩–፬)፣ እና አቤሴሎም (፪ ሳሙ. ፲፭፥፲) በእዚህ ኖሩ። ይህ በንጉስ ዳዊት ስር የይሁዳ የመጀመሪያ ዋና ከተማ ነበር (፪ ሳሙ. ፪፥፲፩)። አብርሐም፣ ሳራ፣ ይስሐቅ፣ ርብቃ፣ ያዕቆብ፣ እና ልያ በእርሻ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ውስጥ ተቀብረዋል ተብሎ ይታመናል (ዘፍጥ. ፳፫፥፲፯–፳፤ ፵፱፥፴፩፣ ፴፫)።
-
ዓይንጋዲ ዳዊት ከሳዖል ተደበቀ እናም የሳዖልን ህይወት አተረፈ (፩ ሳሙ. ፳፫፥፳፱–፳፬፥፳፪)።
-
ቤርሳቤህ አብርሐም በእዚህ ቦታ የውሀ ጉድጓድ ቆፈረ እናም ከአቢሜሌክ ጋር ቃል ኪዳን ገባ (ዘፍጥ. ፳፩፥፴፩)። ይስሐቅ ጌታን አየ (ዘፍጥ. ፳፮፥፲፯፣ ፳፫–፳፬)፣ እናም ያዕቆብ በእዚህ ቦታ ይኖር ነበር (ዘፍጥ. ፴፭፥፲፤ ፵፮፥፩)።
-
ሰዶም እና ገሞራ ሎጥ በሰዶም ለመኖር መረጠ (ዘፍጥ. ፲፫፥፲፩–፲፪፤ ፲፬፥፲፪)። እግዚአብሔር ሰዶም እና ገሞራን በኃጢያተኛነት ምክንያት ደመሰሰ (ዘፍጥ. ፲፱፥፳፬–፳፮)። በኋላም ኢየሱስ እነዚህን ከተማዎች እንደ ኃጢያተኛነት ምሳሌዎች ተጠቀመባቸው (ማቴ. ፲፥፲፭)።