ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ግንቦት 30–ሰኔ 5 (እ.አ.አ)። መሣፍንት 2–4፤ 6–8፤ 13–16፥ “እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው”


“ግንቦት 30–ሰኔ 5 (እ.አ.አ)። መሣፍንት 2–4፤ 6–8፤ 13–16፥ ‘እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 30–ሰኔ 5 (እ.አ.አ)። መሣፍንት 2–4፤ 6–8፤ 13–16፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ዲቦራ ከሰራዊቶች ጋር

ዲቦራ የእስራኤልን ሰራዊቶች ስትመራ የሚያሳይ ስዕል © Providence Collection/licensed from goodsalt.com

ግንቦት 30–ሰኔ 5 (እ.አ.አ)

መሣፍንት 2–46–813–16

“እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ አስነሣላቸው”

ቅዱሳት መጻህፍት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራሉ። በመጽሐፈ መሣፍንት ውስጥ የምታነቧቸው ታሪኮች እንዴት ወደ እርሱ እንድትቀርቡ እንደሚረዷችሁ አሰላስሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ስህተት መስራት፣ ስለዚያ መጥፎ ስሜት መሰማት፣ እና ከዚያም ንሰሃ መግባት እና መንገዶቻችንን ለመቀየር መወሰን ምን እንደሚመስል ሁላችንም እናውቃለን። ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች የቀድሞውን ውሳኔያችንን እንረሳለን፣ እናም፣ ፈተና ሲያጋጥመን፣ ስህተትን እንደገና ስንሰራ እራሳችንን እናገኝ ይሆናል። ይሄ አሳዛኝ ድግግሞሽ በመጽሐፈ መሣፍንትውስጥ የተብራራው የእስራኤላዊያን ተሞክሮዎች ነበር። ከምድሩ ለቀው እንዲወጡ ማድረግ ከነበረባቸው ከነዓናውያን እምነቶች እና የአምልኮ ተግባራት ተጽእኖ ምክንያት፣ እስራኤላውያን ከጌታ ጋር የነበራቸውን ቃል ኪዳን ሰበሩ እና እርሱን ከማምለክ እራሳቸውን አዞሩ። በውጤቱም፣ የእርሱን ጥበቃ አጡ እና ወደ ግዞት ወደቁ። እና ግን ይሄ በተከሰተ እያንዳንዱ ጊዜ፣ ጌታ ንሰሃ ለመግባት እድሉን ሰጣቸው እና አዳኝ፣ “መሳፍንት” የሚባል የወታደራዊ መሪ አስነሳ። በመጽሐፈ መሣፍንት ውስጥ የነበሩት መሣፍንት ሁሉ ቅዱስ አልነበሩም፣ ነገር ግን ጥቂቶቹ እስራኤልን ልጆች ለማዳን እና ከጌታ ጋር ወደነበራቸው የቃል ኪዳን ግንኙነት ለመመለስ ታላቅ እምነትን ተለማመዱ። እነዚህ ታሪኮች የሚያስታውሱን ቢኖር ከኢየሱስ ክርስቶስ ያራቀን ምንም ቢሆን፣ እርሱ የእስራኤል ቤዛ እንደሆነ እና ሁሌም ሊያድነንና ወደ እርሱ ሊቀበለን ፍቃደኛ እንደሆነ ነው።

ስለመጽሐፈ መሣፍንት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መጽሐፈ መሣፍንት” የሚለውን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

መሣፍንት 2፥1–194፥1–16

እኔ በተሳሳትኩ ጊዜ ጌታ መዳንን ያቀርባል።

መጽሐፈ መሣፍንት እንደ ማስጠንቀቂያ ሊያገለግለን ይችላል፦ የጌታን ሃይል በህይወታችን ውስጥ ከተለማመድን በኋላ፣ መውደቅ ሁልጊዜም ሊኖር ይቻላል። መጽሐፉ ለሚወድቁትም ብርታትን ሊሰጥ ይችላል፣ ጌታ መመለሻ መንገዱን ያዘጋጃልና። ለምሳሌ፣ እናንተ መሣፍንት 2፥1–19ን ስታነቡ፣ እስራኤላውያንን ከጌታ ወደ መራቅ የመራቸውን ድርጊቶች እና እንዴት ጌታ እንዳዳናቸው ተመልከቱ። እነዚህ ጥቅሶች ስለጌታ ምን ያስተምሯችኋል? በእምነታችሁ ይበልጥ ጸንታችሁ ለመቆየት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በመሣፍንት ውስጥ በሙሉ የአመጻ፣ ሀዘን፣ እና መዳን ድግግሞሽን ታገኛላችሁ (በተለይ ምእራፎች 346፣ እና13 ይመልከቱ)። መጽሐፈ መሣፍንትን ስታነቡ፣ እስራኤልን ለማዳን መሣፍንቱ ያደረጉትን እና እንዴት አዳኝ መዳን ሲያስፈልጋችሁ እንዴት እንደሚረዳችሁ አሰላስሉ።

እስራኤልን ለማዳን ከረዱት አንድ ልትታወስ የሚገባት ምሳሌ ዲቦራ ነች። ስለ እርሷ በመሣፍንት 4፥1–16 ውስጥ አንብቡ፣ እናም በአከባቢዋ የነበሩ ሰዎች ላይ የነበራትን ተጽእኖ አጥኑ። ከዲቦራ ቃላት ወይም ድርጊቶች የትኞቹ በጌታ እምነት እንደነበራት ያሳዩአችኋል? በቁጥር 14 ውስጥ “እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል” ስትል ዲቦራ በጥያቄዋ ምን ማለቷ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

በተጨማሪም አልማ 7፥13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥87–88 ይመልከቱ።

መሣፍንት 2፥13

ባዓል እና አስታሮት እነማን ነበሩ?

ባዓል የከነዓናውያን አውሎ ነፋስ አምላክ ነበር፣ አስታሮት ደግሞ የከነዓናውያን የመራባት አምላክ ነበረች። የእነዚህ ሁለት አማልክት ማምለክ የመሬትና የሰዎች ለምነት ለከነዓናውያን ምን ያህል አስፈላጊ እንደነበረ ያሳያል። አንዳንድ ጊዜ የፆታ ብልግና እና የልጆች መስዋእትነት ጨምሮም፣ ሕዝቡ እነዚህንና ሌሎች የሐሰት አማልክትን ያመለኩበት መንገዶች በተለይ ለጌታ ቅር ያሰኝ ነበር።

መሣፍንት 6–8

በመንገዶቹ ላይ ስተማመን ጌታ ተዓምራት ሊሰራ ይችላል።

በሕይወታችን ውስጥ የጌታን ተአምራት ለመቀበል የእርሱ መንገዶች ያልተለመዱ ቢመስሉም እንኳ በእሱ መንገዶች መታመን አለብን። በመሣፍንት 6–8 ውስጥ የሚገኘው የጌዴዎን ታሪክ የእዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። የጌዴዎን ሠራዊት የምድያም ሰዎችን ሲያሸንፍ ጌታ እንዴት ያልተጠበቀ ተአምር ሠራ? ጌታ ምን ሊያስተምራችሁ እየሞከረ እንደሆነ ይሰማችኋል? እግዚአብሔር በእናንተ ወይንም በሌሎች አማካኝነት ስራውን ሲሰራ ያያችሁት መቼ ነው?

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “With God Nothing Shall Be Impossible [ከእግዚአብሔር ጋር ምንም የማይቻል የለም]፣” ኤንዛይን፣ ግንቦት 1988 (እ.አ.አ)፣ 33–35።

መሣፍንት 13–16

ጥንካሬ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ጋር በበተቡ ቃል ኪዳኖች በማመን ነው።

በተለይ ናዝራዊን የሚመለከቱትን ጨምሮ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች በመጣሱ፣ ሶምሶን አካላዊ ጥንካሬውንም ሆነ መንፈሳዊ ጥንካሬውን አጥቷል (ስለ ናዛራውያን መረጃ፣ ዘሁልቁ 6፥1–6መጽሐፈ መሣፍንት 13፥7ተመልከቱ)። በመሳፍንት 13–16 ውስጥ የሶምሶንን ታሪክ በምታነቡበት ጊዜ፣ የገባችሁትን እያንዳንዱን ቃል ኪዳን አሰላስሉ። እነዚያን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ በብርታት የተባረካችሁት እንዴት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ለገባችሁት ቃል ኪዳኖች ታማኝ በመሆን ለመኖር ከሚያነሳሳችሁ የሶምሶን ታሪክ ምን ትማራላችሁ?

ሶምሶን ምሰሶዎችን ሲገፋ

ሶምሶን ምሰሶዎችን ሲጥል፣ በጄምስ ቲሶት እና በሌሎች

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

መሣፍንት 2፥10ኢያሱ ከሞተ በኋላ የሚቀጥለው የእስራኤል ትውልድ “እግዚአብሔርን አላወቁም” ነበር። ከቤተሰባችሁ ጋር ጌታን እንዴት እንደሚያውቁ እና ለእነርሱ “ያደረገውን ሥራ” ተነጋገሩ። ይህ እውቀት ለወደፊት ትውልዶች እንደሚጠበቅ እንዴት ነው ልታረጋግጡ የምትችሉት?

መሣፍንት 3፥7–10እነዚህ ጥቅሶች በመፅሐፈ መሳፍንት ውስጥ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተውን ንድፍ ያጠቃልላሉ። የቤተሰባችሁ አባላት እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ፣ እስራኤል ከጌታ ለመራቅ የሰራችውን እና ጌታ እነሱን ለማዳን ያደረገውን መለየት ትችላላችሁ። ጌታን እንድንረሳ ምን ሊያደርገን ይችላል? እርሱ እንዴት ሊያድነን ይችላል? በተከታታይነት ለእሱ ታማኝ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

መሣፍንት 6፥13–16፣ 25–30ምንም እንኳን ድርጊቶቹ ተወዳጅ ባይሆኑም ጌዴዎን ጌታን በመታዘዝ ታላቅ ድፍረትን አሳይቷል። ጌታ ሌሎች የማይስማሙበትን ነገር ምን እንድናደርግ ጠይቆናል? በቁጥሮች 13–16 ውስጥ ጌታ ለጌዴዎን በሰጠው ቃላት ምን ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ያነሳሳናል?

መሣፍንት 7በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ከተገለጸው የጌዴዎን ሠራዊት ተሞክሮ ለመማር እንዲችሉ ቤተሰባችሁ ለመርዳት ጭውውቶችን ወይም ሌላ የፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ልትጠቀሙ ትችላላችሁ? በዚህ ምእራፍ (ለምሳሌ፣ ቁጥሮች 2 እና 15ን ይመልከቱ) የጌታ ቃላት እንዴት ነው በህይወታችን ተግባራዊ የሚሆኑት?

መሣፍንት 13፥5ቃል ኪዳኖቻችን ብርታት እንደሚሰጡን ሁሉ፣ የሶምሶን ከጌታ ጋር የገባው ቃል ኪዳኖች ብርታት ሰጡት። ቤተሰባችሁ በጥቂት አካላዊ እንቅስቃሴዎች መካፈል እና እነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዴት እንድንጠነክር እንደሚረዱን በመወያየት ይደሰቱ ይሆናል። በመንፈሳዊነት እንድንጠነክር ምን ሊረዳን ይችላል? ለአንዳንድ ሀሳቦች የቤተሰብ አባላት ሞዛያ 18፥8–10ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79ን ማንበብ ይችላሉ። ቃል ኪዳናችንን መጠበቅ እንዴት መንፈሳዊ ጥንካሬን ይሰጠናል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “የእስራኤል አዳኝ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 6።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በተማራችሁት ተግብሩ። ስታጠኑ፣ እየተማራችሁት ያለውን እንዴት ልትተገብሩ እንደምትችሉ እራሳችሁን ጠይቁ እና ለማድረግ ወስኑ። መንፈስ ቅዱስ ይምራችሁ። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 35ን ይመልከቱ።)

ጌዴዎን እና ሰራዊት

የጌዴዎን ሰራዊት፣ በዳንኤል ኤ. ልዊስ