ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሰኔ 20–26 (እ.አ.አ)። 2 ሳሙኤል 5–7፤ 11–12፤ 1ኛ ነገስት 3፤ 8፤ 11፥ “መንግሥትህም … ለዘለአለም ይጠነክራል”


“ሰኔ 20–26 (እ.አ.አ)። 2 ሳሙኤል 5–7፤ 11–12፤ 1ኛ ነገስት 3፤ 8፤ 11፥ ‘መንግሥትህም ለዘለአለም ይጠነክራል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021(እ.እ.እ)]

“ሰኔ 20–26 (እ.አ.አ)። 2 ሳሙኤል 5–7፤ 11–12፤ 1ኛ ነገስት 3፤ 8፤ 11” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ንጉስ ዳዊት በዙፋኑ ተቀምጦ

ንጉስ ዳዊት በዙፋኑ፣ በጄሪ ማየልስ ሃርስተን

ሰኔ 20–26 (እ.አ.አ)

2 ሳሙኤል 5–711–121 ነገሥት 3811

“መንግሥትህም … ለዘለአለም ይጠነክራል”

“የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” (2 ጢሞቴዎስ 3፥16)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የንጉስ ዳዊት ንግስና የጀመረው በብዙ ተስፋ ነበር። ጎልያድን ለማሸነፍ የነበረው ያልታከተ እምነቱ አፈታሪክ ነበር። እንደ ንጉስ፣ ኢየሩሳሌምን እንደ ዋና ከተማ አስጠበቀ እና እስራኤልን አንድ አደረገ ( 2 ሳሙኤል 5ን ይመልከቱ)። መንግስቱም ከምንጊዜውም በላይ ጠንካራ ሆነ። ሆኖም ዳዊት በፈተና ተሸነፈ እና መንፈሳዊ ኃይሉን አጣ።

የዳዊት ልጅ ሰሎሞን የግዛት ዘመን እንዲሁ በብዙ ተስፋዎች የተጀመረ ነበር። እርሱ በመለኮታዊ የተቀበለው ጥበብ እና ማስተዋል አፈታሪኮች ነበሩ። እንደ ንጉሥ የእስራኤልን ድንበሮች አስፋፋ እና ለጌታ አስደናቂ ቤተመቅደስን ሠራ። መንግስቱም ከምንጊዜውም በላይ ጠንካራ ሆነ። ሆኖም ሰሎሞን ልቡን ወደ ሌሎች አማልክት እንዲዞር በሞኝነት ፈቀደ።

ከእነዚህ አሳዛኝ ታሪኮች ምን ትምህርት ለማግኘት እንችላለን? ምናልባትም አንድ ትምህርት ቢኖር ያለፉት ልምዶቻችን ምንም ይሁን ምን፣ መንፈሳዊ ጥንካሬያችን የሚወሰነው ዛሬ በምንወስዳቸው ምርጫዎች ላይ ነው። በተጨማሪም በእነዚህ ዘገባዎች ውስጥ የሚያድነን የራሳችን ጥንካሬ ወይም ድፍረት ወይም ጥበብ አለመሆኑን ማየት እንችላለን—ይህም የጌታ ነው። እነዚህ ታሪኮች የእስራኤል እውነተኛ ተስፋ—እናም የእኛ—በዳዊት፣ በሰሎሞን ወይም በሌላ በማንኛውም በሟች ንጉሥ ውስጥ ሳይሆን በሌላ “የዳዊት ልጅ” ውስጥ፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ (ማቴዎስ 1፥1)፣ “ወደ [እርሱ] ቢመለሱ፣ የሕዝቡን ኃጢያት ይቅር [በሚል]” (1 ነገሥት 8፥33–34) የዘለአለማዊ ንጉስ እንደነበር ያሳያሉ።

ስለ 2 ሳሙኤል እና 1 ነገሥት መጽሐፍቶች አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሳሙኤል፣ መጽሐፍቶች” እና “ነገሥታት፣ መጽሐፍቶች” የሚሉትን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

2 ሳሙኤል 5፥17–25

ጌታ ምሪትን ሊሰጠኝ ይችላል።

ዳዊት እስራኤላዊያንን አንድ ካደረገ በኋላ (2 ሳሙኤል 5፥1–5 ይመልከቱ)፣ ህዝቡን ከፊልስጤማዊያን መጠበቅ ነበረበት። እናንተ 2 ሳሙኤል 5፥17–25ን ስታነቡ፣ የዳዊት ምሳሌ በሚያጋጥማችሁ ችግሮች ውስጥ እንዴት ሊረዳችሁ እንደሚችል አስቡ (በተጨማሪም 1 ሳሙኤል 23፥2፣ 10–1130፥82 ሳሙኤል 2፥1 ይመልከቱ)። በህይወታችሁ የጌታን ምሪት እንዴት ነው የምትሹት? በምትቀበሉት መገለጥ ላይ በመተግበራችሁ እንዴት ተባርካችኋል?

በተጨማሪም 1 ዜና 12፤ ሪቻርድ ጂ. ስካት፣ “እንዴት ለግል ህይወታችሁ መገለጥን እና መንፈሳዊ መነሳሳትን ማግኘት እንደሚቻል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2012፣ 45–47 ይመልከቱ።

2 ሳሙኤል 7

ጌታ ለዳዊት ቃል የገባለት “ቤት” ምንድን ነው?

ዳዊት ቤት፣ ማለትም ቤተመቅደስ፣ ለጌታ ለመገንባት ሲያቀርብ ( 2 ሳሙኤል 7፥1–3ን ይመልከቱ)፣ በእርግጥም የዳዊት ልጅ እንደሚገነባው ጌታ ምላሽ ሰጠ (ቁጥሮች 12–15፤ በተጨማሪም 1 ዜና 17፥1–15ን ይመልከቱ)። ጌታ ደግሞ እርሱ በበኩሉ ለዳዊት “ቤት” ማለትም ትውልድ እንደሚሰራለት፣ እንዲሁም ዙፋኑ ለዘለአለም ይኖራል ብሏል (2 ሳሙኤል 7፥11፣ 16፥25–29)መዝሙር 89፥3–4፣ 35–37ን ይመልከቱ)። ይህ ቃል ኪዳን የዳዊት ዘር በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዘለአለማዊ ንጉሳችን ተፈጽሟል (ማቴዎስ 1፥1ሉቃስ 1፥32–33ዮሃነስ 18፥33–37ን ይመልከቱ)።

2 ሳሙኤል 1112፥1–14

ሁል ጊዜ ከኃጢያት መጠንቀቅ አለብኝ።

ዳዊት በፊት የነበረው ለጌታ ታማኝነት “በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ [ሲመላለስ]” እና “አንዲት ሴት ስትታጠብ [በማየቱ]” (2 ሳሙኤል 11፥2) የተፈተነበትን አልተከላከለውም። ከእርሱ ተሞክሮዎች ምን ትምህርቶች እንደምትማሩ አስቡ። እንደእነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ይህን መዝገብ እንድታጠኑ ሊረዱ ይችላሉ፥

  • ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ወደ ኃጢያት ጎዳና እንዲመራው ዳዊት ምን ምርጫዎችን አደረገ? በምትኩ ምን ዓይነት ትክክለኛ ምርጫዎችን ማድረግ ይችል ነበር?

  • ጠላት በራሳችሁ ሕይወት ውስጥ ወደ ኃጢአተኛ ጎዳናዎች ሊወስዳችሁ እንዴት እየሞከረ ሊሆን ይችላል? ወደ ደህንነት ለመመለስ አሁን ምን ምርጫዎችን ታደርጋላችሁ?

በተጨማሪም 2 ኔፊ 28፥20–24፤ “To Look Upon” (ቪድዮ) ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

1 ነገሥት 3፥1–15

የማስተዋል ስጦታ ትክክልና ስህተት የሆነውን ለመለየት እንድችል ይረዳኛል።

ጌታ እንዲህ ቢላችሁ፣ “ምን እንድሰ[ጣችሁ] ለም[ኑ]” (1 ነገሥት 3፥5)፣ ምን ትጠይቃላችሁ? ስለ ሰሎሞን ጥያቄ ምን ያስደንቃችኋል? “መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ፣ አስተዋይ ልቡ” (ቁጥር 9) ለምን አስፈላጊ ስጦታ እንደሆነ አሰላስሉ። ይህንን ስጦታ ለመሻት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም 2 ዜና 1ሞሮኒ 7፥12–19፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ለማስተዋል የፈጠነ፣” ኢንዛይን፣ ታህሳስ 2006 (እ.አ.አ)፣ 30–36 ይመልከቱ።

1 ነገሥት 8፥12–61

ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የእግዚአብሔር መኖር ሙሴ በሠራው ተንቀሳቃሽ ድንኳን ተወክሏል። ምንም እንኳን ዳዊት እግዚአብሔርን የበለጠ ቋሚ መኖሪያ ለመገንባት ፈልጎ የነበረ ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር በምትኩ ቤተመቅደስን እንዲሠራለት የዳዊት ልጅ የሆነውን ሰሎሞንን መርጧል። የሰሎሞንን ጸሎት እና ቤተመቅደሱን ሲያጠናቅቅ ለሕዝቡ የተናገራቸውን ቃላት በምታነቡበት ጊዜ፣ ስለ ጌታ እና ስለ ቤቱ ምን እንደተሰማው አስተውሉ። በጸሎቱ ሰሎሞን የጠየቃቸውን በረከቶች ልትዘረዝሩ ትችላላችሁ። ስለ እነዚህ በረከቶች ምን ታስተውላላችሁ? በእኛ ጊዜ እንዴት ነው በጌታ ቤት ውስጥ የተባረካችሁት?

በተጨማሪም 2 ዜና 6ን ይመልከቱ።

ምስል
የባራንኪላ ኮሎምቢያ ቤተመቅደስ

የባራንኪላ ኮሎምቢያ ቤተመቅደስ

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

2 ሳሙኤል 5፥19፣ 23መመሪያ እና አቅጣጫን ለማግኘት መቼ “እግዚአብሔርን ጠየቅን”? እንዴት ነው እርሱ የመለሰልን?

2 ሳሙኤል 7፥16ጌታ ዳዊትን “መንግሥትህም ለዘለአለም ይጸናል” ሲለው፣ እርሱ እያለ የነበረው ወደፊት በዳዊት የዘር ሐረግ ውስጥ ለዘለአለም የሚነግሠውን ንጉሥ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን እየጠቀሰ ነበር። ምናልባትም ኢየሱስ ክርስቶስ ዘለአለማዊ ንጉሳችሁ ስለሆነ ለምን አመስጋኞች እንደሆናችሁ በምትወያዩበት ጊዜ ቤተሰባችሁ በቤት ውስጥ የተሰሩ ዘውዶችን በስራት ሊደሰቱ ይችላሉ።

2 ሳሙኤል 11ስለ ዳዊት አሰቃቂ ኃጢያቶች ማንበብ የብልግና ሥዕሎች፣ ርኩስ ሀሳቦች እና የስነምግባር ብልሽት አደገኝነትን ለመወያየት ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። በውይይታችሁ እነዚህ ምንጮች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፥ ቤተክርስቲያኗ የብልግና ምስሎችን አስመልከቶ የሚወያይበት ምንጮችን በጥቅምት 2019 የወጣው ሊያሆና፣ (ChurchofJesusChrist.org/addressing–pornography)፣ እና “What Should I Do When I See Pornography?” and “Watch Your Step” የሚል ርዕስ ያላቸው ቪድዮዎች (ChurchofJesusChrist.org)። የቤተሰብ አባላት የብልግና ሥዕሎች ሲያጋጥሟቸው ምን እንደሚያደርጉ ዕቅድ ሊያወጡ ይችላሉ።

1 ነገሥት 11፥9–11ከጌታ ልባችንን ሊያዞሩ የሚችሉ “ሌሎችንም አማልክት” (ቁጥር 10) ምንድን ናቸው? ልባችን በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ይበልጥ ቅድስናን ስጠኝ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 131።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቤተሰባችሁን የሚባርክ መርሆዎ ላይ አተኩሩ። የእግዚአብሔርን ቃላት ስታጠኑ፣ ራሳችሁን እንዲህ ጠይቁ፣ “ለቤተሰቤ በተለየ ትርጉም የሚኖረውን በዚህ ምንድን ነው የማገኘው?” ( Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 17)።

ምስል
የሰሎሞን ቤተመቅደስ

የሰሎሞን ቤተመቅደስ የሚያሳይ ስዕል፣ በሳም ሎውሎር

አትም