ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሰኔ 6–12(እ.አ.አ)። ሩት፤ 1 ሳሙኤል 1–3፥ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና”


“ሰኔ 6–12 (እ.አ.አ)። ሩት፤ 1 ሳሙኤል 1–3፥ ‘ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 6–12 (እ.አ.አ)። ሩት፤ 1 ሳሙኤል 1–3፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ሩት እና ኑኃሚ

በምትሄጂበት በሳንዲ ፍሬክልተን ጋጎን

ሰኔ 6–12 (እ.አ.አ)

ሩት1 ሳሙኤል 1–3

“ልቤ በእግዚአብሔር ጸና”

የሩት፣ ሐና፣ እና የሌሎችም ህይወቶችን በዚህ ሳምንት ስታጠኑ፣ መንፈስ ቅዱስን በቅርበት አዳምጡ እና ማንኛውንም የምትቀበሉትን ስሜቶች መዝግቡ። ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አንዳንዴ ህይወታችን ከጅማሮው እስከ ፍጻሜው ግልጽ መንገድን ይከተላል ብለን እናስባለን። ሆኖም፣ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው አጭሩ እርቀት ቀጥተኛ መስመር ነውና። እና ግን ህይወት በአብዛኛው ባልጠበቅነው መንገዶች በሚወስዱን እና በመዘግየትና ልዋጭ መንገዶች የተሞላች ነች። ህይወታችንን ይሆናል ብለን ካሰብነው የተለየ ሆኖ ልናገኘው እንችል ይሆናል።

ሩት እና ሐና ይህን በእርግጥም ተረድተው ነበር። ሩት እስራኤላዊት አልነበረችም፣ ነገር ግን ያገባችው ሰው ነበረ፣ እና ባለቤትዋ ሲሞት፣ ምርጫ መወሰን ነበረባት። ወደቤተሰቧ እና የቀድሞ፣ የተለመደው ህይወት ትመለስ ይሆን፣ ወይም የእስራኤላዊ እምነትን እና ከምራቷ ጋር በአዲሱ ቤት ትቀጥል ይሆን? (ሩት 1፥4–18ን ይመልከቱ)። ሐና ለህይወቷ የነበራት እቅድ ልጆች ለመውለድ ነበር፣ እና ያንን ማድረግ አለመቻሏ “በልብዋ ትማረር” ነበር ( 1 ሳሙኤል 1፥1–10ን ይመልከቱ)። ስለ ሩት እና ሐና ስታነቡ፣ ህይወታቸውን በጌታ እጅ ለማድረግ እና ባልተጠበቁት መንገዶቻቸው ለመጓዝ የነበራቸውን እምነት አስቡ። ከዚያም ስለራሳችሁ ጉዞ አስቡ። ከሩት እና ሐና—እና ከሌሎችም—የተለየ ሆኖ ነው የሚታየው። ነገር ግን ከዚህ እና የዘለአለማዊ መድረሻችሁ ባሉት ፈተናዎች እና ግርምታዎች መካከል ሁሉ፣ እንደ ሐና “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና” ማለትን ልትማሩ ትችላላችሁ (1 ሳሙኤል 2፥1)።

ስለ ሩት እና 1 ሳሙኤል መጽሐፍቶች አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሩት” እና “ሳሙኤል፣ የብሉይ ኪዳን ነቢይ” የሚለውን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሩት

ክርስቶስ ሀዘንን ወደ ድል መቀየር ይችላል።

የሩት ባል ሲሞት፣ ሃዘኑ ያመጣባት መዘዞች ባሁን ጊዜ መበለት ከሚያጋጥማት እጅግ የከፉ ነበሩ። በዚያ ጊዜ በነበረው በእስራኤላዊ ባህል ፣ ባል ወይም ወንድ ልጆች የሌላት ሴት ለንብረት እና ምንም አይነት ገቢ ለማግኘት መብት አልነበራትም። የሩትን ታሪክ ስታነቡ፣ ሃዘንን ጌታ እንዴት ወደ ታላቅ በረከቶች እንደቀየረ አስተውሉ። ስለ ሩት ረድቷት ሊሆን ስለሚችል ነገር ምን ታስተውላላችሁ? ሩትን ከአጣዳፊ ሁኔታዋ በመዋጀት ላይ የቦዔዝ ድርሻ ምንድን ነበር? ( ሩት 4፥4–7ን ይመልከቱ)። በሩት እና በቦዔዝ ላይ የትኛውን የክርስቶስ መሰል ባህሪ ትመለከታላች?

ሩት1 ሳሙኤል 1

ሁኔታዬ ምንም ቢሆን እግዚአብሔር እንደሚመራኝ እና እንደሚረዳኝ አምናለሁ።

እራሳችሁን በሩት፣ በኑኃሚ፣ እና በሐና ታሪኮች ውስጥ ልትመለከቱ ትችላላችሁን? ምናልባትም እንደ ሩት እና ኑኃሚ፣ ታላቅ እጦት አጋጥሟችሁ ይሆናል (ሩት 1፥1–5ን ይመልከቱ)። ወይም፣ እንደ ሐና፣ ገና ያልተቀበላችሁትን በረከቶች እየጠበቃችሁ ይሆናል (1 ሳሙኤል 1፥ 1–10ን ይመልከቱ)። ከእነዚህ ታማኝ ሴቶች ምሳሌዎች ምን መልእክቶችን እንደምትማሩ አሰላስሉ። ሩት እና ሐና በእግዚአብሔር ያላቸውን እምነት እንዴት ነው ያሳዩት? እነርሱ ምን በረከቶችን ተቀበሉ? የእነርሱን ምሳሌዎች እንዴት ለመከተል ትችላላችሁ? ህይወት ከባድ ሆኖ በሚሰማ ጊዜ እንዴት ጌታን “ለማመን” (ሩት 2፥12) እንደቻላችሁ አስቡ።

ሪያና አይ. አቡርቶ፣ “በደመና እና በጸሃይ ብረሃን ጌታ ከእኔ ጋር ሁን!ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 57–60 ይመልከቱ።

ሐና እና ሳሙኤል

ለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፣ በኤልስፒት ያንግ

1 ሳሙኤል 2፥1–10

ልቤ በጌታ ሊደሰት ይችላል።

ሐና ወጣት ሳሙኤልን ወደ ቤተመቅደስ ስትወስደው፣ በ 1 ሳሙኤል 2፥1–10 የተመዘገቡ የሚያምሩ የጌታ የምስጋና ቃላትን ተናገረች። ጥቂት ቀደም ብሎ “በልብዋ ትመረር ነበር፣ … እና እጅግም አለቀሰች”(1 ሳሙኤል 1፥10) የሚለውን ስናስብ እነዚህ ቃላቶች ይበልጥ የሚነኩ ናቸው። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ለጌታ የሙገሳ እና የምስጋና ስሜታችሁን የሚጨምሩ ምን መልእክቶችን ታገኛላችሁ? ምናልባትም የሐና መዝሙር ለጌታ ምስጋና ለመግለጥ እንደ መዘመር፣ መሳል፣ ማገልገል፣ ወይም ለእርሱ ስሜታችሁን የሚገልጽ ማንኛውም ነገር ማድረግ አይነት የፈጠራ መንገድ እንድታገኙ ያነሳሷችኋል።

በእርግጥ፣ ሁሉም የልብ ጸሎቶች ልክ የሐና እንደተመለሰው አይመለሱ ይሆናል። ጸሎታችሁ ተስፋ እንዳደረጋችሁት መልስ የማይሰጣቸው በሚሆኑበት ጊዜ ሊረዳችሁ የሚችል ምን መልእክት “በማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ አመስጋኝ” ከሚለው ከፕሬዘዳንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ንግግር ውስጥ ታገኛላችሁ? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 70–77)።

1 ሳሙኤል 3

የጌታን ድምጽ ልሰማ እና ልታዘዝ እችላለሁ።

እንደ ሁላችን፣ ሳሙኤል እንዴት የጌታን ድምጽ መገንዘብ እንደሚችል መማር ነበረበት። እናንተ 1 ሳሙኤል 3ን ስታነቡ፣ ከዚህ ወጣት ልጅ የጌታን ድምጽ ስለመስማት እና መታዘዝ ምን ትማራላችሁ? ድምጹን በመስማት ምን ተሞክሮ ነበራችሁ? እንደ ኤሊ፣ ሌሎች ጌታ ሲናገራቸው ማስተዋል እንዲችሉ ለመርዳት ምን አጋጣሚዎች አሏችሁ? (1 ሳሙኤል 3ን ይመልከቱ)።

በተጨማሪ ዮሃንስ 14፥ 14–21፤ ዴቪድ ፒ. ሆመር፣ “ድምጹን መስማት፣” ሊያሆና, ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 41–43 ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሩት 1፥16–182፥5–8፣ 11–12በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ቤተሰባችሁ የደግነትን ምሳሌዎች ሊመለከቱ ይችላሉ። ለቤተሰባችን እና ለሌሎች ደግነትን እናም ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝነትን እንዴት ነው የምናሳየው? የ“ሩት እና ኑኃሚ” ምእራፍ (በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ) ከሩት ምሳሌ ቤተሰባችሁ እንዲማሩ ሊረዳቸው ይችላል።

1 ሳሙኤል 1፥15ምናልባት ሐና “እኔስ … በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ“ ያለችውን ምስላዊ እይታ የቤተሰብ አባላት እንዲታያቸው ከእቃ ውስጥ የሆነ ነገር ልታፈሱ ትችላላችሁ። ጸሎቶቻችን ምን መምሰል እንዳለባቸው ለማብራራት ይሄ ለምንድነው ጥሩ መንገድ የሆነው? የግል እና የቤተሰብ ጸሎታችንን እንዴት ልናሻሽል እንችላለን?

1 ሳሙኤል 2፥1–10የሐና ለጌታ የምስጋና ግጥም እናንተ ጌታን ለማመስገን የምትጠቀሙባቸውን መዝሙሮች እንድታስቡ ሊመራችሁ ይችላል። አብራችሁ ልትዘምሩ ትችላላችሁ። የቤተሰባችሁ አባላት ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ስሜት ለማሳየት ሌሎች መንገዶችን ሊያስቡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አዳኝን ለምን እንደሚወዱ የሚያሳዩ ምስሎችን ሊስሉ ይችላሉ።

1 ሳሙኤል 3፥1–11ጌታ ሳሙኤልን ሲጠራ ያለውን ታሪክ መጨዋወት አዝናኝ ሊሆን ይችላል ወይም ቤተሰባችሁ “ሳሙኤል እና ኤሊ” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ መመልከት ይችላሉ። የቤተሰብ አባላት ጌታ ሲናገራቸው የተሰማቸውን ጊዜ እና በቃላቱ ላይ እንዴት እንደተገበሩ መነጋገር ይችላሉ።

2:3

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ ተሰጠ መዝሙር፥ “በነብሴ የጸሐይ ብርሃን አለ ዛሬ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 227።

የግል ጥናትን ማሻሻል

መንፈስ ጥናታችሁን ይመራ ዘንድ ፍቀዱ። መማር ወዳለባችሁ ነገሮች መንፈስ ቅዱስ እንዲመራችሁ ፀልዩ። ያልጠበቃችሁትን ርእስ እንድታነቡ ወይም በተለየ መልኩ እንድታጠኑ ቢመራችሁ እንኳ ለሹክሹክታው ስሜታዊ ሁኑ።

ልጅ ሳሙኤል በድንኳን

ሳሙኤል ጌታን ሲሰማ የሚያጻይ ስዕል፣ በሳም ሎውሎር