ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሰኔ 13–19 (እ.አ.አ)። 1 ሳሙኤል 8–10፤ 13፤ 15–18፥ “ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና”


“ሰኔ 13–19 (እ.አ.አ)። 1 ሳሙኤል 8–10፤ 13፤ 15–18፤ ‘ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021(እ.አ.አ)]

“ሰኔ 13–19 (እ.አ.አ)። 1 ሳሙኤል 8–10፤ 13፤ 15–18፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦቸና ለቤተሰቦቸ፥ 2022 (እ.አ.አ)

ወጣት ዳዊት ወንጭፍ ይዞ

ዳዊት እና ጎልያድ፣ በስቲቭ ኔዘርኮት

ሰኔ 13–19 (እ.አ.አ)

1 ሳሙኤል 8–101315–18

“ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና”

በዚህ ዝርዝር ውስጥ የቀረቡት ሀሳቦች በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉትን አንዳንድ አስፈላጊ መርሆዎች ለመለየት ይረዳችኋል። ስታጠኑ ሌሎች መርሆዎችን ታገኙ ይሆናል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የእስራኤል ነገዶች በተስፋው ምድር ላይ ከተቀመጡበት ጊዜ አንስቶ ፍልስጤማውያን ለደህንነታቸው ቀጣይ ሥጋት ነበሩ። ባለፉት ለብዙ ጊዜያት ጌታ እስራኤልን ከጠላቶቻቸው አዳናቸው። ነገር ግን አሁን የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ አስገደዱ፣ “ንጉሥ ይሁንልን፥ … በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል” (1 ሳሙኤል 8፥19–20)። ጌታም ተጸጸተ፣ ሳኦልም ንጉሥ ሆኖ ተሾመ። ሆኖም አስፈሪው ግዙፍ ጎልያድ የእስራኤልን ጭፍሮች ለመዋጋት በመጣ ጊዜ፣ ሳኦልም ልክ እንደሌሎቹ ሰራዊቱ “እጅግ ፈራ” (1 ሳሙኤል 17፥11)። በዚያ ቀን እስራኤልን ያዳነው ንጉስ ሳኦል ሳይሆን፣ ምንም ትጥቅ ያልለበሰው ግን የማይደፈር እምነትን በጌታ የለበሰ ትሁት እረኛ ልጅ ዳዊት ነበር። ይህም ውጊያ ለእስራኤላዊያን እና መንፈሳዊ ውጊያ ላለበት ሁሉ የሚያሳየው “እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳልሆነ” እና “ሰልፉ የእግዚአብሔር [እንደሆነ]” ነው (1 ሳሙኤል 17፥47)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ሳሙኤል 8

ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሴ ነው።

እናንተ 1 ሳሙኤል 8ን ስታነቡ፣ እስራኤላዊያን ከእርሱ ሌላ ንጉስ በመፈለጋቸው ጌታ ምን እንደተሰማው አስተውሉ። ጌታን “በእናንተ ላይ እንዲነግሥ” መምረጥ ማለት ምን ማለት ነው? (1 ሳሙኤል 8፥7)። እንዲሁም ጌታን ከመከተል ይልቅ የዓለምን ዓመፀኛ አዝማሚያዎች ለመከተል የምትፈተኑባቸውን መንገዶች ልታስቡ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለአለም ንጉሣችሁ እንዲሆን እንደምትፈልጉ እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ነገሥት 8፥22–23ሞዛያ 29፥1–36፤ ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “አለምን ማሸነፍ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ.)፣ 58–62 ይመልከቱ።

1 ሳሙኤል 9፥15–1710፥1–1216፥1–13

እግዚአብሔር ሰዎች በመንግሥቱ እንዲያገለግሉ በትንቢት ይጠራቸዋል።

እግዚአብሔር ሳኦልን እና ዳዊትን በትንቢት እና በራእይ ነገሥታት አድርጎ መረጠ (1 ሳሙኤል 9፥15–1710፥1–1216፥1–13)። ዛሬም ወንዶች እና ሴቶችን በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንዲያገለግሉ የሚጠራው እንዲሁ ነው። “በትንቢት … በእግዚአብሔር መጠራት” ስለሚለው ከእነዚህ መዛግብት ምን ትማራላችሁ? (የእምነት አንቀጾች 1፥5)። ስልጣን በጌታ በተሰጣቸው አገልጋዮች በመጠራት እና በመለየት ምን በረከቶች ይመጣሉ?

ሳሙኤል ሳኦልን ሲቀባ

ሳሙኤል ሳኦልን ሲቀባ የሚያሳይ ስዕል © Lifeway Collection/licensed from goodsalt.com

1 ሳሙኤል 13፥5–1415

“መታዘዝ ከመስዋእትነት … ይበልጣል።”

ምንም እንኳን ሳኦል በአካል ረጅም ቢሆንም፣ በነገሠ ጊዜ “[በዓይኑ] ታናሽ” እንደነበር ተሰማው (1 ሳሙኤል 15፥17)። ሆኖም፣ በስኬት ሲባረክ፣ የበለጠ እራሱን በበላይ እና ጌታን ባነሰ መልክ መተማመን ጀመረ። በ1 ሳሙኤል 13፥5–1415 ውስጥ ምን ማረጋገጫ ታያላችሁ? ያኔ ከሳኦል ጋር ብትሆኑ ኖሮ “ዓመፁን” እና “እልከኝነቱን” እንዲያሸንፍ ሊረዳው የሚችል ነገሮች ምን ትሉት ነበር? (1 ሳሙኤል 15፥23)።

በተጨማሪም 2ኛ ኔፊ 9፥28–29ሔለማን 12፥4–5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥39–40፤ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን “የእግራችሁን መንገድ አስተውሉ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2014(እ.አ.አ)፣ 86–88።

1 ሳሙኤል 16፥7

“እግዚአብሔር ልብን ያያል”

ሰዎች “በውጫዊ ገጽታ” ላይ በሌሎች ላይ የሚፈርዱባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድናቸው? ጌታ እንደሚያደርገው “ልብን” መመልከት ምን ማለት ነው? (1 ሳሙኤል 16፥7)። ይህንን መርህ ሌሎችን በምታዩበት መንገድ እና እራሳችሁ ላይ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ። እንዲህ ማድረጋችሁ ከሌሎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ወይም ዝምድናዎች እንዴት ሊነካ ይችላል?

1 ሳሙኤል 17

በጌታ እገዛ ማንኛውንም ተግዳሮት ማሸነፍ እችላለሁ።

እናንተ 1 ሳሙኤል 17ን ስታነቡ፣ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተለያዩ ሰዎችን ቃላት አሰላስሉ (ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ)። እነዚህ ጥቅሶች ስለእግዚአብሔር ምን ያስተምሯችኋል? የዳዊት ቃላት ድፍረቱን እና በጌታ ላይ ያለውን እምነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?

የሚገጥሟችሁን የግል ውጊያዎች አሰላስሉ። በ1 ሳሙኤል 17 ውስጥ ጌታ ሊረዳችሁ የሚችል እምነትታችሁን የሚያጠናክር ነገር ምን ይገኛል?

በተጨማሪም ጎርደን ቢ. ሂንክሊ፣ “በህይወታችን ውስጥ ያሉ ጎልያዶችን ማሸነፍ፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት1983 (እ.አ.አ)፣ 46፣ 51–52 ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ሳሙኤል 9፥15–2116፥7እነዚህን ጥቅሶች ከሽማግሌ ዲተር ኤፍ ኡክዶርፍ የሚከተሉትን ቃላት በማንበብ ጌታ ለምን ሳኦልን እና ዳዊትን እንደመረጠ ለመወያየት ሊያነሳሳ ይችላል፣ “እራሳችንን በሟች አይኖቻችን ብቻ ከተመለከትን፣ እራሳችንን እንደ ጥሩ አድርገን አናይም ይሆናል። ነገር ግን የሰማይ አባታችን በእውነት እኛ ማን እንደሆንን እና ማን መሆን እንደምንችል ያያል” (“በሚያስደንቅ መልኩ ይሰራል!Liahona፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 23)። ምናልባት የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው በልባቸው ውስጥ ስላሉት መልካም ባሕሪዎች ተራ በተራ ማውራት ይችሉ ይሆናል (1 ሳሙኤል 16፥7 ይመልከቱ)።

1 ሳሙኤል 10፥6–12እግዚአብሔር ሳኦልን እንደባረከው ሥራ ወይም ጥሪን ለመፈፀም አንድን ሰው በመንፈሳዊ ኃይል ሲባርከው መቼ አይተናል? በአገልግሎቱ ውስጥ “እግዚአብሔር ሌላ ልብ [ሲሰጠን]” ወይም “የእግዚአብሔርም መንፈስ [በእኛ ላይ በወረደበት]” ጊዜ ምን ልምዶችን ልናካፍል እንችላለን? (ቁጥሮች 9–10)።

1 ሳሙኤል 17፥20–54ቤተሰቦችዎ የዳዊትን እና የጎልያድን ታሪክ አብረው ሊያነቡ ይችላሉ (በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ “ዳዊትና ጎልያድ” ሊረዳ ይችላል) ወይም “The Lord Will Deliver Me” የሚልን ቪድዮ ይመልከቱ (ChurchofJesusChrist.org)። ይህ ለእኛ እንደ “ጎልያዶች” ሊሰሙን ስለሚችሉት ተግዳሮቶች ለመወያየት ሊያመራ ይችላል። ከእነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ የተወሰኑትን ኢላማ ወይም የጎልያድ ስዕል ላይ መጻፍ እና ተራ በተራ እቃዎችን (እንደ የወረቀት ኳሶች) በእዚያ ላይ መወርወር ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ጎልያድ ስለነበረው የጦር መሣሪያ ማንበቡ አስደሳች ሊሆን ይችላል (ቁጥሮች 4–7)። ዳዊት የነበረው ምንድን ነበር? ( ቁጥሮች 38–40፣ 45–47 ይመልከቱ)። ጎልያዶቻችንን እንድናሸነፍ የሚረዳንን ጌታ ምን ሰጥቶናል?

2:3

1 ሳሙኤል 18፥1–4ዳዊት እና ዮናታን እንዴት እርስ ለእርሳቸው መልካም ጓደኞች ነበሩ? መልካም ጓደኞች እኛን እንዴት ባርከዋል? መልካም ጓደኞች ለመሆን ምን ማድረግ እንችላለን፣ ለቤተሰባችን አባላት ጨምሮም?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ጀግና እሆናለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 162።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ምስክርነታችሁን በብዛት አካፍሉ። “የእናንተ ስለእውነት ያላችሁ ንጹህ ምስክርነት [ቤተሰባችሁን] በሃይለኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል። ምስክርነት ቀጥታ እና ከልብ ሲሆን ነው በጣም ሃይል ያለው። ርቱዕ አነጋገር ወይም ረዥም መሆን የለበትም” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር]፣ 11)።

ዳዊት

የዳዊት ምስል፣ በዳይሊን ማርሽ