ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሰኔ 27–ሐምሌ 3 (እ.አ.አ)። 1 ነገሥት 17–19፥ “እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ”


vሰኔ 27–ሐምሌ 3 (እ.አ.አ)። 1 ነገሥት 17–19፤ ‘እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 27–ሐምሌ 3 (እ.አ.አ)። 1 ነገሥት 17–19” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ኤልያስ ከሚነድ መሰዊያ ጎን ቆሞ

ኤልያስ ከበኣል ካህን ጋር ሲሟገት በጄሪ ሃርስተን

ሰኔ 27–ሐምሌ 3 (እ.አ.አ)

1 ነገሥት 17–19

“እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ”

ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ፣ የመንፈስ ቅዱስን “አነስተኛ ለስላሳ ድምጽ” እንድትሰሙ ልባችሁን እና አእምሮአችሁን የሚያዘጋጀውን እምነትን እየተለማመዳችሁ ናችሁ (1 ነገሥት 19፥12)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የእስራኤል ቤት ግራ በመጋባት ላይ ነበረች። በዳዊት እና ሰለሞን ስር የተሳኩት አንድነት እና ብልጽግና ካለፉ ቆይተዋል፣ እና ህዝቡ ከጌታ ጋር የነበራቸው የቃል ኪዳን ግንኙነት ለብዙ ሰዎች የቆየ ትውስታ ሆኖ ነበር። የእስራኤል መንግስት ተከፋፍሎ ነበር፣ አስሩ ነገዶች የሰሜኑን የእስራኤል መንግስት እና ሁለቱ ነገዶች የደቡቡን የይሁዳ መንግስት መሰረቱ። ሁለቱም መንግስታት በመንፈሳዊ ያልተረጋጉ ነበሩ፣ ከጌታ ጋር ያላቸውን ቃል ኪዳን በሚጥሱ እና ሌሎችም እንደዚያው እንዲያደርጉ ተጽእኖ በሚያሳድሩ ነገስታት ይመሩ ነበር (1 ነገሥት 11–16ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ንጉስ አሃብ የሃሰት አምላክ በኣልን እስራኤል እንድታመልክ በሚያበረታታበት በሰሜኑ መንግስት ውስጥ ክህደቱ በተለየ መልኩ የባሰ ነበር።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነበር ነቢዩ ኤልያስ እንዲሰብክ የተጠራው። በክፉ አካባቢ እንኳን በጌታ ያለ የግል እምነት በቅዱሳን መካከል እንደሚበለጽግ የእርሱ አገልግሎት መዝገብ በግልጽ ያሳያል። አንዳንዴ ለዚህ አይነት እምነት ጌታ ስሜት በሚያሳድርው፣ ከሰማይ እንደሚወርድ እሳት አይነት ባልተደበቁ ተአምራቶች ምላሹን ይሰጣል። ነገር ግን እርሱ ጸጥ ባሉ፣ የታማኝ መበለትን እና የወንድ ልጇን የግል ፍላጎቶችን እንደማሟላት ባሉ የግል ተአምራቶችም ይሰራል። እና በአብዛኛው የእርሱ ተአምራቶች በጣም ግላዊ ስለሆኑ ለእናንት ብቻ ነው የሚታወቁት—ለምሳሌ፣ ጌታ እራሱን እና ፍላጎቱን “በዝግተኛ ትንሽ ድምጽ” (1 ነገሥት 19፥12) በሚገልፅበት ጊዜ።

ስለ ኤልያሳ ለበለጠ ማብራሪያ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ኤልይሳ” የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ነገሥት 17፥1–16

መስዋዕት ለማድረግ መጋበዝ እምነቴን ለመለማመድ እድል ነው።

መጀመሪያ ለምን ኤልያስ የሰራፕታ መበለቷ እራሷን እና የተራበውን ልጅዋን ከማብላቷ በፊት ምግብ እና ውሃ እንድትሰጠው መጠየቁ ለመረዳት የሚከብድ ይመስላል። ነገር ግን የኤልያስ ጥያቄ ለዚህ ትንሽ ቤተሰብ እንደበረከት ሊታይ ይችላል። የጌታ በረከት ያስፈልጋቸው ነበር፣ እና መስዋዕት በአብዛኛው በረከቶችን ያመጣል—የጠንካራ እምነት በረከትንም ጨምሮ።

ይህን ታሪክ ስታነቡ፣ ራሳችሁን በዚህች ድንቅ መበለት ቦታ አድርጉ። ስለ እርሷ ምን ያስደንቃችኋል? እምነታችሁን ለመለማመድ ያላችሁን እድሎች አስቡ—ለመስዋዕት ያላችሁን እድሎች ጨምሮ። እንዴት ነው ይበልጥ እንደዚህች መበለት ልትሆኑ የምትችሉት?

በተጨማሪም ማቴዎስ 6፣25–33ሉቃስ 4፣24–26፤ ሊን ጂ. ሮቢንስ፣ “አስራት—ለተቸገሩትም እንኳ ትዕዛዝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2005 (እ.አ.አ)፣ 34–36 ይመልከቱ።

1 ነገሥት 18

“እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ።”

ጌታ“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” (ዘጸአት 20፥3) በማለት ያዘዘ ቢሆንም፣ እስራኤላዊያን በዓልን ለማምለክ ጥሩ ምክንያቶች አለን ብለው ያስቡት ይሆናል። በዓል የማእበል እና ዝናብ አምላክ ተብሎ ነበር የሚታወቀው፣ እና ከሶስት አመታት ድርቅ በኋላ፣ ማእበል በጥድፊያ አስፈልጓቸው ነበር። እና በዓልን ማምለክ ማህበራዊ ተቀባይነት ነበረው እና በንጉሱ እና ንግስቲቱ የተደገፈ ነበር። እናንተ 1 ነገሥት 18ን ስታነቡ፣ እስራኤላዊያን የነበሩበትን ሁኔታ ጋር ሊነጻጸር የሚችሉ በህይወታችሁ ማንኛውም ሁኔታዎችን አስቡ። አማራጮቹ ምክኒያታዊ እና አጓጊ ስለሆኑ ጌታን በመከተል ዙሪያ እራሳችሁን ባለመወሰን ውስጥ የምታገኙበት ጊዜ አለ? ( 1 ነገሥት 18፥21ን ይመልከቱ)። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ባሉት ክስተቶች፣ ጌታ ስለራሱ እና በዓል ህዝቡን ምን ለማስተማር እየሞከረ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ? ምን ተሞክሮዎች ተመሳሳይ እውነታዎችን አስተምረዋችኋል?

ኤልያስ በጌታ ላይ የነበረውን እምነት የሚያሳዩትን በዚህ መዕራፍ ውስጥ የተናገራቸውን እና ያደረጋቸውን ነገሮች ማስተዋል ያስደስታል። ስለ እምነት ከኤልያስ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ኢያሱ 24፥152 ኔፊ 2፥26–28፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሶን፣ “ምርጫ እና ቁርጠኝነት” [ለወጣት ጎልማሶች የአለም አቀፋዊ ጉባኤ፣ ጥር 12፣ 2020 (እ.አ.አ)]፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ

ኤልያስ በአለት ላይ ቆሞ

የ1 ነገሥት 19፥11–12 ምሳሌያዊ መግለጫ። ነቢዩ፣ © Robert Booth Charles/Bridgeman Images

1 ነገሥት 19፥1–18

ጌታ በብዛት በጸጥተኛና ቀላል መንገዶች ይናገራል።

ንግስት ኤልዛቤል በቀርሜሎስ ተራራ በካህናቷ ላይ የሆነውን በሰማች ጊዜ፣ አልተለወጠችም—ተቆጥታም ነበር። ለህይወቱ ፈርቶ፣ ኤልያስ ወደ ምድረበዳው ሸሸ እና በዋሻ ውስጥ ተሸሸገ። እዚያ፣ በብቸኝነት እና ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ እየታገል፣ በቀርሜሎስ ተራራ ከሆነው የተለየ ከጌታ ጋር ተሞክሮ ነበረው። በ1 ነገሥት 19፥1–18 ያለው የኤልያስ ተሞክሮ በችግራችሁ ጊዜ ጌታ እንዴት እንደሚገናኝ ምን ያስተምራችኋል? የእርሱን ድምጽ በህይወታችሁ ተሞክሮ ያገኛችሁበትን ጊዜ አሰላስሉ። የእርሱን መመሪያ ለመቀበል ምን ለማድረግ ያስፈልጋችኋል?።

በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን ቃላት እና ሐረጎች አሰላስሉ፥ ሔለማን 5፥303 ኔፊ 11፥3–7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–238፥2–39፥8–911፥12–1436፥2

በተጨማሪም መዝሙረ ዳዊት 46፥101 ኔፊ 17፥45፤ ራሴል ኤም. ኔልሰን፣ “ስሙት፣” ሊያሆና May 2020 (እ.አ.አ.)፣ 88– 92 ይመልከቱ።

1 ነገሥት 19፥19–21

ጌታን ማገልገል ከአለማዊ ሃሳቦች ይልቅ ቅድሚያውን ይወስዳል።

ኤልሳዕ 12 ጥማድ በሮች ባለቤት መሆኑ ሀብታም ሰው መሆኑን ያሳያል። በ1 ነገሥት 19፥19–21 ውስጥ ስለተመዘገቡት ድርጊቶች ያስገረማችሁ ምንድን ነው? የኤልሳዕን ምሳሌ እንዴት መከተል ትችላላችሁ?

እንዲሁም ማቴዎስ 4፥18–22ን ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ነገሥት 17፥1–16“Elijah and the Widow of Zarephath [ኤልያስ እና የሰራፕታ መበለት]” የሚለው ቪድዮ (ChurchofJesusChrist.org) እና ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ያለው ምስል በ1 ነገሥት 17፥1–16 ያለውን መዝገብ ቤተሰባችሁ ምስላዊ እይታ እንዲኖራቸው ሊረዳ ይችላል። ጥቅሶቹን ካነበባችሁ እና እነዚህን መረጃዎች ካያችሁ በኋላ፣ መበለቷ የነበራትን የሚያነሳሱ ባህሪዎች እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊዘረዝሩ ይችላሉ። እምነታችንን ለማሳየት ምን እንድናደርግ ነው ጌታ የሚጠይቀን?

2:3

1 ነገሥት 18“ኤልያስ እና የበኣል ነቢያት” (በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ) ቤተሰባችሁ በ1 ነገሥት 18 ውስጥ ያለውን ታሪክ እንዲማሩ ሊረዷቸው ይችላሉ። ለጌታ ሙሉ ለሙሉ ራሳችንን እንዳንሰጥ እየከለከሉን ያሉ ነገሮች አሉን? እርሱን ለመምረጥ ያለንን ፍላጎት እንዴት ልናሳይ እንችላለን? (ቁጥር 21ን ይመልከቱ)።

1 ነገሥት 19፥11–12“ዝግተኛ ትንሽ ድምጽ”ን የመስማት አስፈላጊነትን ቤተሰባቹ እንዲረዱ ምን ሊያግዛቸው ይችላል? እናንተ 1 ነገሥት 19፥11–12 እንደቤተሰብ አብራችሁ ልታነቡ ወይም እንደ “መንፈስ ቅዱስ” (የልጆች መዝሙር፣ 105) አይነት ስለመንፈስ ቅዱስ መዝሙሮችን በዝግተኛ እና ትንሽ ድምጽ ለመዘመር ትችላላችሁ። ዝግተኛ፣ ትንሹን ድምጽ እንዳንሰማ ለመከልከል ሰይጣን እንዴት እንደሚጥር ለማሳየት የሚረብሹ ድምጾችን ትጨምሩም ይሆናል። የቤተሰብ አባላት የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳቶች ለመስማት ምን እንደሚያደርጉ ሊያካፍሉ ይችሉ ይሆናል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “መንፈስ ቅዱስ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 105።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። መንፈስ እንደተናገራችሁ ሲሰማችሁ፣ እየተናገራችሁ ያለውን ስሜታችሁን ለመጻፍ አስቡ። እነዚህን ስሜቶች ወደ ቃላት ለመቀየር የሚጠይቀውን ሃሳብ እንድታሰላስሉ እና ሃብታችሁ እንዲሆኑ ሊረዳችሁ ይችላል።

ሴት እና ልጅ

የሰራፕታ መበለት፣ በሮዝ ዳቶክ ዳል