ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 4–10 (እ.አ.አ)። 2 ነገሥት 2–7፤ “በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ [አለ]”


“ሐምሌ 4–10 (እ.አ.አ)፤ 2 መሳፍንት 2–7፥ ‘በእስራኤል ዘንድ ነቢይ [አለ]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 4–10 (እ.አ.አ)። 2 ነገሥት 2–7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ኤልሳዕ የእሳት ሰረገላዎችን ለአገልጋይ ሲያሳይ

ኤልሳዕ የእሳት ሰረገላዎችን ለአገልጋዩ ሲያሳይ ምስል፣ © Review & Herald Publishing/licensed from goodsalt.com

ሐምሌ 4–10 (እ.አ.አ)

2 ነግሥት 2–7

“በእስራኤል ዘንድ ነቢይ [አለ]”

ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ፣ መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ሐረጎችን ወይም ምንባቦችን ወደ እናንት ትኩረት ያመጣል። እነዚያ ምንባቦች ለእናንተ ለምን ትርጉም እንዳላቸው ለመፃፍ አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የነቢይ ዋናው ተልእኮ ስለ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር እና መመስከር ነው። ስለ ነቢዩ ኤልሳዕ ያለን መዝገብ ግን ብዙ ትምህርቱን ወይም ምስክርነቱን አያካትትም። መዝገቡ የሚያካትተው ልጅን ከሞት ማስነሳትን ጨምሮ ያሉ ኤልሳዕ የሰራቸውን ተአምራቶች(2 ነገሥት 4፥18–37ን ይመልከቱ)፣ እንዲሁም በጥቂት ምግብ እጅግ ብዙ ህዝብን የመገበበት (2 ነገሥት 4፥42–44ን ይመልከቱ)፣ እና ለምጻምን የፈወሰበትን (2 ነገሥት 5፥1–14 ይመልከቱ) ያካትታሉ። ስለዚህ ኤልሳዕ ስለ ክርስቶስ የመሰከረው ቃላት ባይኖሩንም፣ በኤልሳዕ አገልግሎት ሁሉ፣ የጌታን ሕይወት ሰጪ፣ ገንቢ እና የመፈወስ ኃይል የሚያሳዩ ኃይለኛ መገለጫዎች አሉን። እንደእነዚህ ዓይነቶቹ መገለጫዎች አንዳንዴ ከምናስተውለው በላይ በሕይወታችን ውስጥ በጣም ብዙ ናቸው። እነርሱን ለማየት፣ ኤልሳዕ በፈራው ወጣት አገልጋዩ ፈንታ ሲጸልይ የጠየቀውን ተአምር እኛም ልንሻ ያስፈልገናል፣ “አቤቱ፣ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ” (2 ነገሥት 6፥17)።

ስለ 2 ነገሥት ለበለጠ ማብራሪያ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ነገሥታት፣ መፅሐፈ” ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

2 ነገሥት 2–6

እግዚአብሔር በህይወቴ ውስጥ ተአምራትን ሊሰራ ይቻለዋል።

ተዓምራት ብዙውን ጊዜ የሟችነትን ችግሮች ለማሸነፍ ይረዱናል—በኤልሳዕ ዘመን፣ በረሃማ መሬት ንጹህ ውሃ ያስፈልጋት እና የጠፋ መጥረቢያ መልሶ ማግኘት አስፈልጎ ነበር (2 ነገሥት 2፥19–226፥4–7ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ተአምራት ልቦቻችንን ወደ ጌታም ያዞራሉ እና መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያስተምሩናል። እናንተ 2 ነገሥት 2–6 ስታነቡ፣ የምታገኟቸውን ተአምራቶች ለመዘርዘር አስቡ እናም ከእያንዳንዱ መንፈሳዊ ትምህርቶች የምትማሩትን አሰላስሉ። ስለ ጌታ እና በህይወታችሁ ማድረግ ስለሚችለው እነዚህ ተአምራት ምን ያስተምሯችኋል?

በተጨማሪም 2 ኔፊ 26፥12–1327፥23ሞርሞን 9፥7–21ሞሮኒ 7፥35–37፤ ዶናልድ ኤል. ሆልስትሮም “የተአምራት ቀን አልፏልን?ሊያሆና፣ ህዳር 2017ቭ(እ.አ.አ)፣ 88–90 ይመልከቱ።

2 ነገሥት 4፥8–177፥1–16

የጌታ ቃላት በእርሱ ነቢያት አማካኝነት ይፈጸማሉ።

2 ነገሥት 4፥8–177፥1–16 ውስጥ እንደተጻፈው፣ ጌታ ስለሚመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ከሌሎቹ አንጻር የሚከሰቱ የማይመስሉ ነገሮችን ትንቢት እንዲናገር ኤልሳዕን አነሳስቶታል። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ​ዛሬ በነቢያት አማካኝነት ስላሚመጡት የጌታ ቃል ምላሻችሁ እንዴት እንደሆነ አስቡ። በህይወት ካሉ ነቢያት ምን ትምህርቶች፣ ትንቢቶች፣ ወይም ቃል ኪዳኖች ሰምታችኋል? በእነዚያ ቃላት ላይ በእምነት ለመተግበር ምን እያደረጋችሁ ነው?

በተጨማሪም 3 ኔፊ 29፥6ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥37–38ን ይመልከቱ።

2 ነገሥት 5

ትሁት እና ታዛዥ ከሆንኩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊፈውሰኝ ይችላል።

በአንድ ታሪክ ውስጥ አካላዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ነገሮች ጋር ሲያወዳድሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የግል ትርጉም ማግኘት አንዳንድ ጊዜ ቀላል ነው። ለምሳሌ፣ 2 ነገሥት 5ን ስታነቡ፣ የናዕማን የለምጻምነት በሽታን ከሚገጥማችሁ መንፈሳዊ ፈተና ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ። እንደ ናዕማንም፣ ጌታ እንዲረዳችሁ “ታላቅ ነገርስ እንኳን [ቢነግረን]” (ቁጥር 13) ብላችሁ ተስፋ አድርጋችኋል። የናዕማን ተሞክሮ ምን ያስተምራችኋል? በህይወታችሁ፣ ከ“መታጠብ፣ እና መንጻት” ቀላል ምክር ጋር የሚነፃፀር ምንድን ነው?

የናዕማን ተሞክሮ በእስራኤል አምላክ ላይ ያለውን እምነት እንዴት እንደነካ ልብ አስተውሉ (ቁጥር 15ን ይመልከቱ)። ምን ልምምዶች በእግዚአብሔር ያላችሁን እምነት እአጠናክረዋል?

በተጨማሪም ሉቃስ 4፥271 ጼጥሮስ 5፥5–7አልማ 37፥3–7; ኤተር 12፥27፤ ኤል. ዊትኒይ ክሌይተን፣ “ምንም ነገር ለእናነት ቢላችሁ፣ አድርጉት፣” ሊያሆና ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 97–99፤ “Naaman and Elisha” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

2:3

2 ነገሥት 6፥8–23

“ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉ።”

በቁጥር መበለጥ ተሰምቷችሁ እና ፈርታችሁ፣እንዲሁም ልክ እንደ ኤልሳዕ አገልጋይ እንዳደረገው “ምን እናደርጋለን?” ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁን? (2 ነገሥት 6፥8–23 ይመልከቱ)። ከኤልሳዕ ምላሽ ምን ያነሳሳችኋል? ስለ ፈተናዎች፣ ሀላፊነቶች ወይም ወንጌልን ለመኖር የምታደርጉትን ጥረት በተመለከተ ይህ ጽሁፍ ያላችሁን አስተሳሰብ እና ስሜት እንዴት ይለውጣል?

ስታሰላስሉ፣ የፕሬዘዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግን ቃላት አስቡ፥ “ልክ እንደ ኤልሳዕ አገልጋይ፣ ተቃርነው ከምታዩአቸው ይልቅ የእናንተ ይበልጣል። አብረዋችሁ ያሉት አንዳንዶቹም በምድራዊ አይናችሁ አይታዩም። ጌታ ከፍ ያደርጋችኋል እናም አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ከእናንተ ጋር እንዲቆሙ በመጥራት ያደርገዋል” (“ተጓዡ ሆይ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 58)።

በተጨማሪም መዝሙር 121ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥88ን ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

2 ነገሥት 2፥1–14ኤልሳዕ የኤልያስን መጎናጸፊያ (ወይም የትንቢታዊ ጥሪ ምልክት) “እንደወሰደ” የተመለከቱትን ሰዎች አስቡ። ይህ ለኤልሳዕ አገልግሎት የሰጡት ምላሽ ላይ እንዴት ተጽእኖ አድርጎ ይሆን? (በተጨማሪም 1 ነገሥት 19፥19ን ይመልከቱ።) ምናልባት የቤተሰብ አባላት ጌታ በተራቸው በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንዲያገለግሉ የተጠሩትን ሲደግፍ እና ሲያጠናክሩ የተመለከቱባቸውን መንገዶች “መጐናጸፊያ” ለብሰው መመስከር ይችሉ ይሆናል።

2 ነገሥት 42 ነገሥት 4 ውስጥ ካሉት ተአምራቶች አንዱን እንዲያነቡ ልትጋብዟቸው ( ቁጥሮች 1–7፣ 14–17፣ 32–35፣ 38–41፣ 42–44ን ይመልከቱ) እና የትኛውን ተአምር እርሱ ወይም እርሷ እየገለጸ/ጸች እንደሆነ የቤተሰብ አባላት በመጻፍ እንዲገምቱ ለማድረግ ትችላላችሁ። ስለጌታ እና ስለ ተአምራቶቹ ከእዚህ ምእራፍ ምን እንማራለን? በህይወታችን ምን ተአምራትን—ትልቅ ወይም ትንሽ—አይተናል?

2 ነገሥት 5፥1–15እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ እና ናዕማን እንዲያደርግ የተጠየቀውን ቀላል ነገር ስታሰላስሉ፣ ነቢያችን እንድናደርግ የጠየቁንን ቀላል ነገሮች አስቡ። የእርሳቸውን ምክር እንዴት በተሻለ ቤተሰባችን መከተል ይችላል?

ቤተሰባችሁ ይህንን ቪድዮ ሊመለከቱ ይችላሉ “Naaman and Elisha” (ChurchofJesusChrist.org) ወይም ይህንን አንብቡ “ኤልሳዕናዕማን ሲፈውስ” (የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ)።

2:3

2 ነገሥት 5፥20–27ግያዝ “ታማኝነት እና ሐቀኝነት” በለወጣቶች ጥንካሬ ውስጥ በማንበብ እንዴት ይጠቅመው ነበር? (ገጽ 19)። አለመታመን እንዴት ነው የሚጎዳን? ታማኝ ስንሆን የምንባረከው እንዴት ነው?

2 ነገሥት 6፥13–17በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጸውን የኤልሳዕ እና የአገልጋዩ ተሞክሮ በመሳል የቤተሰብ አባላት ይደሰቱ ይሆናል። እነዚህ ጥቅሶች ብቸኝነት ወይም ውጥረት ሲሰማን እንዴት ሊረዱን ይችላሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር: “Dearest Children, God Is Near You፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር. 96።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ጥያቄዎችን መጠየቅ አበረታቱ። ከልጆች የሚመጡ ጥያቄዎች እነርሱ ለመማር ዝግጁ መሆናቸውን ያመላክታሉ። ለእነርሱ ጥያቄዎች መልሱን የማታውቁ ከሆነ፣ አብራችኋቸው መልሱን ፈልጉ። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 25–26ን ይመልከቱ።)

ናዕማን በወንዝ ውስጥ ሲታጠብ

ናዕማን ከለምጹ ሲፈወስ የሚያሳይ፣ በፖል ማን