ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ነገሥት 17–25፥ “በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ”


“ሐምሌ 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ነገሥት 17–25፥ ‘በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ነገሥት 17–25፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ሰዎች የሚቃጠለውን ከተማ ትተው ሲሄዱ

የእስረኞች ማምለጥ፣ በጄምስ ቲሶት እና ሌሎች

ሐምሌ 11–17 (እ.አ.አ)

2 ነገሥት 17–25

“በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ”

ኢዮስያስ ቃላቱን ከህጉ መጽሐፍ ሲሰማ፣ በእምነት ምላሽ ሰጠ። በ2 ነገሥት 17–25 ውስጥ ለምታነቡት በእምነት እንዴት ነው መመለስ የምትችሉት?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የነቢዩ ኤልሳዕ አገልግሎት አስደናቂ ቢሆንም፣ የሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት መንፈሳዊነት መቀነሱን ቀጠለ። ክፉ ነገሥታት የጣዖት አምልኮን፣ ጦርነትን እና ክህደትን ያበረታቱ ነበር። በስተመጨረሻ የአሦር መንግሥት አሥሩን የእስራኤል ነገዶች አሸነፈና በታተናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ብዙም የተሻለ አልነበረም፤ በዚያም የጣዖት አምልኮ ተስፋፍቶ ነበር። ነገር ግን በዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ዘገባዎች ለተወሰነ ጊዜ ሕዝባቸውን ወደ ጌታ የመለሱ ሁለት ጻድቃን ነገሥታትን ይጠቅሳሉ። አንደኛው ሕዝቅያስ ነበር። በእሱ የግዛት ዘመን አሶሮች፣ በሰሜን ከነበራቸው አዲስ ድል ጋር፣ ብዙ የደቡብን ምድሮች በድል አሸነፉ። ሕዝቅያስና ሕዝቡ ግን ኢየሩሳሌምን በተአምር መንገድ ባዳነው ጌታ ላይ እምነት አሳይተው ነበር። በኋላም፣ ከሌላ የክህደት ጊዜ ቀጥሎ፣ ኢዮስያስ ነገሠ። የህጉን መጽሐፍ እንደገና በማወቁ ተነሳስቶ፣ ኢዮስያስ የብዙ ወገኖቹን ሃይማኖታዊ ህይወት የሚያድሱ ማሻሻያዎችን አመጣ።

በይሁዳ ታሪክ ውስጥ በነበሩ ጨለማ ዓመታት ውስጥ ከእነዚህ ሁለት ብሩህ ቦታዎች ምን እንማራለን? ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ፣ በሕይወታችሁ ውስጥ የእምነት እና የእግዚአብሔር ቃል ኃይልን ማሰላሰል ትችላላችሁ። እንደ እስራኤል እና ይሁዳ፣ ሁላችንም ጥሩም መጥፎም ምርጫዎችን እናደርጋለን። እና በህይወታችን ውስጥ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉን ስናውቅ፣ ምናልባት የሕዝቅያስ እና የኢዮስያስ ምሳሌዎች “በአምላካችን በጌታ እንድንታመን” ያነሳሱናል (2 ነገሥት 18፥22)።

በተጨማሪም 2 ዜና 29–35፤ “በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች” ውስጥ ክፍል “ኢየሱስ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ይላል፣ ‘ወደቤት ኑ’” ይመልከቱ።

ምስል
Learn More image
ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

2 ነገሥት 18–19

በአስቸጋሪ ጊዜያት ለጌታ ታማኝ መሆን እችላለሁ።

ብዙዎቻችን እምነታችንን የሚፈታተኑ አጋጣሚዎች አጋጥመውናል። ለሕዝቅያስና ለሕዝቡ፣ ከእነዚህ ጊዜያት አንዱ የመጣው የአሶር ጦር ይሁዳን በመውረር፣ ብዙ ከተሞችን ካጠፋ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ነበር። እናንተ 2 ነገሥት 18–19ን ስታነቡ፣ በዚያ ጊዜ እናንተ በኢየሩሳሌም እንደምትኖሩ አድርጋችሁ አስቡት። ለምሳሌ ያህል በ2 ነገሥት 18፥28–37 እና 19፥10–13 ውስጥ እንደተዘገበው የአሶር ፌዞችን ብትሰሙ ምን ይሰማችሁ ነበር። በምላሹ ሕዝቅያስ ካደረገው ምን ትማራላችሁ? (2 ነገሥት 19፥1–7፣ 14–19ን ይመልከቱ)። ጌታ ሕዝቅያስን እንዴት ደገፈው? (2 ነገሥት 19፥35–37ን ይመልከቱ)። በአስቸጋሪ ጊዜያት እርሱ እንዴት እንደደገፋችሁ አስቡ።

2 ነገሥት 18፥5–7 ውስጥ የሕዝቅያስን ማብራሪያ ልታሰላስሉም ትችላላችሁ። እነዚህ ቁጥሮች ሕዝቅያስ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ታማኝ ሆኖ መኖር የቻለው ለምን እንደሆነ ምን ያመለክታሉ? ምሳሌውን እንዴት መከተል ትችላላችሁ?

በተጨማሪም 3 ኔፊ 3–4፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “በክርስቶስ እምነት ጽኑ እና የማይነቃነቅ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 30–33 ይመልክቱ።

2 ነገሥት 19፥20–37

ሁሉም ነገሮች በጌታ እጆች ናቸው።

የአሶር ንጉሥ ሱራፌልም ሠራዊቱ ኢየሩሳሌምን ያሸንፋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት ነበረው። አሶር እስራኤልን ጨምሮ ብዙ ህዝቦችን አሸንፋለች—ኢየሩሳሌም ለምን የተለየ ትሆናለች? (2 ነገሥት 1718፥33–3419፥11–13ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ጌታ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ለሱራፌል መልእክት ነበረው እናም በ2 ነገሥት 19፥20–34 ውስጥ ተመዝግቧል። ይህን መልዕክት እንዴት ታጠቃልሉታላችሁ? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በጌታ እና በእቅዱ ላይ እንድትታመኑ የሚያደርጋችሁ ምን እውነቶችን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ሔለማን 12፥4–23ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥16፣ ይመልከቱ።

2 ነገሥት 21–23

ቅዱሳት መጻህፍት ልቤን ወደ ጌታ ሊያዞሩ ይችላሉ።

አንድ መንፈሳዊ ነገር እንደጎደላችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ምናልባት ከእግዚአብሔር ጋር ያለላችሁ ግንኙነት በጣም ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል ተስምቷችሁ ይሆናል። ወደ እርሱ ለመመለስ ምን ረዳችሁ? በንጉሥ ምናሴ መሪነት የይሁዳ መንግሥት ከጌታ እንዴት እንደወደቀች (2 ነገሥት 21ን ይመልከቱ) እና ንጉስ ኢዮስያስ ራሳቸውን ወደ እርሱ እንዲመልሱ እንዴት እንደረዳቸው (2 ነገሥት 22–23ን ይመልከቱ) ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች ልብ በሉ። ኢዮስያስን እና ሕዝቡን ምን አነሳሳቸው? ይህ ታሪክም “ … በፍጹም [ልብና] በፍጹም [ነፍስ]” “እግዚአብሔርን ተከትሎ [ለመሄድ] ዘንድ” (2 ነገሥት 23፥3)ቁርጥነታችሁን ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

እነዚህን ምእራፎች ስታነቡ፣ በተጨማሪም ምዕራፍ 6ን በ Teachings of Presidents of the Church: Spencer W. Kimball [ቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርት፥ ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል] [2006 (እ.አ.አ) 59–68] ውስጥ ማጥናት አስቡ፣ በዚህም ፕሬዝዳንት ኪምባል የንጉስ ኢዮስያስ ታሪክ “በቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ውስጥ ካሉ ምርጥ ታሪኮች አንዱ ነው” የሚል ሀሳብ አቅርበዋል (ገጽ 62)። ፕሬዚዳንት ኪምባል ለምን እንደዚያ ሊሰማቸው ቻለ? በፕሬዚዳንት ኪምባል ቃላት ውስጥ በተለይም ስለ ንጉስ ኢዮስያስ በሰጡት አስተያየት እናንተ በህይወታችሁ እንድትተገብሩ 2 ነገሥት 22–23 ውስጥ የሚያግዛችሁ ነገር ምንድን ነው?

በተጨማሪም አልማ 31፥5፤ ታኪሻ ዋዳ፣ “የክርስቶስ ቃላትን መመገብ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 38–40፣ “Josiah and the Book of the Law” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
ቤተሰቦች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

ቅዱሳት መጻሕፍት ልባችንን ወደ ጌታ ሊያዞሩ ይችላሉ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

2 ነገሥት 19፥14–19አስቸጋሪ ችግሮች ወይም ጥያቄዎች ሲያጋጥሙን ሊረዳን ከሚችለው የሕዝቅያስ ምሳሌ ምን እንማራለን? ጌታ ለእርዳታ ጸሎታችንን እንዴት ምላሽ ሰጥቷል? ምናልባት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወደ ጌታ እንዲመለሱ የሚያስታውሳቸውን ለማሳየት በቤት ውስጥ አንድ ነገር ለመስራት ይችሉ ይሆናል።

2 ነገሥት 22፥3–72 ነገሥት 22፥3–7 ውስጥ የተገለጹት ሠራተኞች “የታመኑ በመሆናቸው” ቤተመቅደሱን እንደገና ለመገንባት በሚውለው ገንዘብ ታምነዋል (ቁጥር 7)። እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት በአደራ የተሰጧቸውን ነገሮች ስም እንዲጠሩ መጠየቅ ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደ ተጠቀሱት ሰራተኞቹ እምነት የሚጣልብን ለመሆን እንዴት እንችላለን?

2 ነገሥት 22፥8–11፣ 1923፥1–3ኢዮስያስ እና ሕዝቡ ለአምላክ ቃል ምላሽ በሰጡበት መንገድ ምን ያስደንቀናል? በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል እንዴት ነው ምላሽ የምንሰጠው? የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስን የመከተል ፍላጎታቸውን የጨመሩ የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባቦችን ወይም ታሪኮችን የቤተሰባችሁ አባላት ማጋራት ይችላሉ።

2 ነገሥት 23፥25በዚህ ጥቅስ ውስጥ ስለ ኢዮስያስ ገለፃ እኛ ምን የተለየ ነገር እናያለን? ቤተሰባችሁ በዚህ ሳምንት ወደ ጌታ በፍጹም ልባቸው ለመዞር ማድረግ የሚችሉትን ነገሮች በወረቀት ላይ ሊስሉ ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ቅዱሳት መጽሃፍትን ስፈትሽ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 277።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። እያነበባችሁ እያላችሁ መንፈስ አንዳንድ ቃላትን እና ሃረጎችን ወደ ትኩረታችሁ ሊያመጣ ይችላል። ሊያነሳሱ እና ሊያበረታቷችሁ ይችሉ ይሆናል፤ ልክ ለእናንተ ቀጥታ የተጻፉም ሊመስሉ ይችላሉ።

ምስል
አንድ ሰው ለንጉሱ ጥቅል ሲያመጣ

አንድ ሰው ለንጉሱ ጥቅል ሲያመጣ የሚያሳይ ስዕል፣ በሮበርት ቲ. ባሬት

አትም