ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 18–24 (እ.አ.አ)። ዕዝራ 1፤ 3–7፤ ነህምያ 2፤ 4–6፤ 8፤ “እኔም ትልቅ ሥራ እሠራለሁ”


“ሐምሌ 18–24 (እ.አ.አ)። ዕዝራ 1፤ 3–7፤ ነህምያ 2፤ 4–6፤ 8፤ ‘እኔም ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 18–24 (እ.አ.አ)። ዕዝራ 1፤ 3–7፤ ነህምያ 2፤ 4–6፤ 8፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

የዘሩባቤል ቤተመቅደስ

የዘሩባቤል ቤተመቅደስ ምስል፣ በሳም ሎውሎር

ሐምሌ 18–24 (እ.አ.አ)

ዕዝራ 13–7ነህምያ 24–68

“እኔም ትልቅ ሥራ እሠራለሁ”

ፕሬዘደንት ኤዝራ ቴፍት ቤንሰን እንዳሰተማሩት፣ “የእግዚአብሔር ቃል ቅዱሳንን ለማጠናከር እና ክፉን ለመቋቋም፣ መልካሞችን አጥብቀው ለመያዝ እና በዚህ ህይወት ውስጥ ደስታን እንዲያገኙ በመንፈስ የማስታጠቅ ኃይል አለው” (Teachings of Presidents of the Church: Ezra Taft Benson [የቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች ኤዝራ ቴፍት ቤንሰን] [2014 (እ.አ.አ)]፣ 118)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የአይሁድ ህዝብ ለ70 ዓመታት ያህል በባቢሎን ተማርኮ ነበር። ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን አጥተዋል፣ እና ብዙዎች ለእግዚአብሔር ሕግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ረስተው ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር እነርሱን አልረሳቸውም። በእርግጥም፣ በነቢዩ አማካኝነት እንዲህ አውጇል፣ “እጐበኛችኋለሁ፣ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ” (ኤርምያስ 29፥10)። በዚህ ትንቢት መሠረት፣ ጌታ ለአይሁዶች የሚመለሱበትን መንገድ አመቻቸላቸው እናም ለሕዝቡ “ታላቅ ሥራ” እንዲያከናውኑ አገልጋዮችን አስነሳ (ነህምያ 6፥3))። እነዚህ አገልጋዮች የሚያካትተውም የእግዚአብሔርን ቤት መልሶ መገንባትን ይቆጣጠር የነበረ ዘሩባቤል የተባለ አንድ ገዢን፤ የሕዝቦችን ልብ ወደ ጌታ ሕግ እንዲመለሰ ያደረገ ካህንና ጸሐፊ ዕዝራ፤ እና በኋላ ላይ የይሁዳ ገዢ የነበረው እና በኢየሩሳሌም ዙሪያ የመከላከያ ግድግዳዎችን መልሶ የመገንባቱን ሥራ የመራው ነህምያ ነበር። በእርግጥ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፣ ግን ደግሞ ባልተጠበቁ ምንጮች ድጋፍ አግኝተዋል። እኛም ታላቅ ሥራ እየሠራን ስለሆነ፣ የእነርሱ ልምዶች እንድናውቅ እና እንድንነሳሳ ለማድረግ ይችላሉ። እናም እንደ እነርሱ፣ የእኛ ሥራ ከጌታ ቤት፣ ከጌታ ሕግ እና በእርሱ ውስጥ ካገኘነው መንፈሳዊ ጥበቃ ጋር ብዙ የሚገናኝ ነው።

ስለዕዝራ እና ነህምያ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዕዝራ“ እና “ነህምያ” የሚሉትን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዕዝራ 1

ጌታ ዓላማዎቹን ለማሳካት ሰዎችን ያነሳሳል።

ፋርስ ባቢሎንን ድል ካደረገች በኋላ የፋርስ ንጉስ ቂሮስ ቤተመቅደሱን እንደገና ለመገንባት የአይሁድ ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲልክ በጌታ ተመስጦ ነበር። እናንተ ዕዝራ 1ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ቂሮስ በዚህ አስፈላጊ ሥራ ለአይሁዶች ድጋፍ ለመስጠት ምን ፈቃደኛ እንደነበረ አስተውሉ። የቤተክርስቲያኗ አባል ያልሆኑትን ጨምሮ ጌታ በዙሪያችሁ ባሉ ወንዶች እና ሴቶች በኩል ሲሰራ እንዴት ታዩታላችሁ? ይህ ስለጌታ እና ስለስራው ምን ጥቆማን ይሰጣችኋል?

እንዲሁም ኢሳይያስ 44፥24–28ን ይመልከቱ።

ዕዝራ 3፥8–136፥16–22

ቤተመቅደሶች ደስታን ሊያመጡልኝ ይችላሉ።

ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን በወረሩ ጊዜ ቤተመቅደሱን ዘርፈው በእሳት አቃጥለውታል (2ኛ ነገሥት 25፥1–102ኛ ዜና 36፥17–19ን ይመልከቱ)። ይህንን ከተመለከቱት አይሁድ መካከል ብትሆኑ ኖሮ ምን ይሰማን ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ? (መዝሙረ ዳዊት 137ን ተመልከቱ)። አይሁዶች፣ ከአስርተ ዓመታት በኋላ፣ ተመልሰው መቅደሱን እንደገና እንዲገነቡ በተፈቀደላቸው ጊዜ ምን እንደተሰማቸው ልብ በሉ (ዕዝራ 3፥8–136፥16–22ን ተመልከቱ)። ስለቤተመቅደስ ያላችሁን ስሜቶች አሰላስሉ። ቤተመቅደሶች ለምን የደስታ ምንጭ ናቸው? ለጌታ ድምጽ በይበልጥ ምላሽን መስጠት እንዴት ትችላላችሁ?

ለዘመኑ የቤተመቅደስ ግንባታ ደስታ ምሳሌ፣ የሚከተሉትን ቪድዮዎች ተመልከቱ፥ “Practice, Celebration, Dedication: Temple Blessings in El Salvador” እና “The Laie Hawaii Temple Youth Cultural Celebration” (ChurchofJesusChrist.org)።

5:51
3:13
ቤተሰብ በቤተመቅደስ ቅጥር ግቢ ላይ ሲራመዱ

ቤተመቅደሱ በህይወታችን ውስጥ የደስታ ምንጭ ሊሆን ይችላል።

ዕዝራ 4–6ነህምያ 246

ተቃውሞ ቢኖርም የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲቀጥል ማገዝ እችላለሁ።

የጌታ ሥራ ያለምንም ተቃዋሚ ይሄዳል፣ እናም ይህ በዘሩባቤል እና በነህምያ መሪነት ጥረቶች እውነት ነበር። በሁለቱም ሁኔታዎች፣ “የይሁዳ ጠላቶች” (ዕዝራ 4፥1) ሳምራውያን ነበሩ—ከአሕዛብ ጋር የተቀላቀሉ የእስራኤል ልጆች ዘሮች። ቤተመቅደሱን ስለመገንባታቸው ተቃዋሚነታቸው ማንበብ (ዕዝራ 4–6ን ተመልከቱ) ዛሬ የእግዚአብሔር ሥራዎች ያሉበትን ተቃዋሚዎች ለማሰላሰል እና ተቃውሞ ሲመጣ ምን ምላሽ መስጠት እንደምትችሉ ሊመራችሁ ይችላል።

በተመሳሳይ፣ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ግድግዳዎች ለመጠገን ስለሰራው ማንበብ ( ነህምያ 246ተመልከቱ) እግዚአብሔር እንድታደርጉ በሚፈልገው ሥራ ላይ እንድታሰላስሉ ያደርግ ይሆናል። ከነህምያ ምሳሌነት ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ዲይተር ኤፍ. ኡክቶድርፍ “ታላቅ ስራን እየሰራን ነው እናም ማቆም አንችልም፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 59–62 ተመልከቱ።

ዕዝራ 7ነህምያ 8

ቅዱሳት መጻህፍትን ሳጠና እባረካለሁ።

ቤተመቅደሱ እንደገና ከተገነባ በኋላም ቢሆን፣ የኢየሩሳሌም ሰዎች በመንፈስ ታገሉ፣ ምክንያቱም ለትውልዶች “የሙሴ ህግ መጽሐፍ” ውስን መዳረሻ ስለነበራቸው (ነህምያ 8፥1)። ጸሐፊው ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከፋርስ ንጉሥ ፈቃድ ተቀብሎ “ሕጉን ወደ ጉባኤው አመጣው” (ነህምያ 8፥2)። በዕዝራ 7፥10 ውስጥ እንደተብራራው የዕዝራን ምሳሌ እንዴት መከተል ትችላላችሁ? ዕዝራ ሕግን ለሕዝቡ ስለማንበቡ ታሪክ የሚናገረውን ነህምያ 8 በምታነቡበት ጊዜ፣ በሕይወታችሁ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል ኃይል ምን ሀሳቦች አላችሁ?

ደግሞም [Teachings: Ezra Taft Benson] ትምህርቶች፥ ኤዝራ ቴፍት ቤንሰን፣ 115–24ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዕዝራ 3፥8–136፥16–22አይሁድ ቤተመቅደሱ እንደገና ሲገነቡ እና ከዚያም ሲቀደስ ያላቸውን ደስታ እንዴት አሳዩ? እኛ ለቤተመቅደስ ያለንን ደስታ ለመግለጽ ምን እያደረግን ነን? ምናልባት ቤተሰቦቻችሁ የቤተመቅደሶችን ሥዕሎች ተመልክተው ቤተመቅደሶች ደስታን እንዴት እንደሚያመጡ ማውራት ይችሉ ይሆናል (temples.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)።

ዕዝራ 7፥6፣ 9–10፣ 27–28በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በብዛት፣ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ እንደነበረ ጽፏል። ይህ ሐረግ ምን ማለቱ ይሆን? የጌታ እጅ በእኛ ላይ እንዴት ተሰምቶናል? ምናልባትም የቤተሰብ አባላት ከህይወታቸው ምሳሌዎችን መጋራት ይችሉ ይሆናል።

ነህምያ 246“ታላቅ ሥራ” (ነህምያ 6፥3) ሲሰሩ ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው የሚያገረው የነህምያ ታሪክ የቤተሰብ አባላትን ሊያነቃቃ ይችላል። በጋራ ቁልፍ ምንባቦችን ሲታነቡ (እንደ ነህምያ 2፥17–204፥13–186፥1–3 ያሉ) የቤተሰብ አባላት በቤታችሁ ዙሪያ ካሉት ነገሮች ግድግዳ መገንባት ይችላሉ። ከነህምያ ምሳሌነት ተቃርኖን ስለመጋፈጥ ምን እንማራለን? ጌታ ምን ታላቅ ስራ እንድንሰራ ይፈልጋል? በዚህ ሥራ ላይ የሚደርሰውን ተቃውሞ ለማሸነፍ ጌታ እንዴት አጠናክሮናል?

ነህምያ 8፥1–12ነህምያ 8 ውስጥ ዕዝራ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ለሚጓጉ ሰዎች የሙሴን ሕግ አነበበ። ከቁጥሮች 1–12 ያሉትን በማንበብ ቤተሰባችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸውን አድናቆት እንዲያሳድጉ ሊያግዝ ይችላል። ሰዎቹ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ምን ተሰማቸው? እርስ በእርሳችን “ንባቡን ለመረዳት” እንዴት ልንረዳዳ እንችላለን? (ቁጥር 8)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 95።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

እንደቤተሰብ ቅዱሳት መጻሐህፍትን አካፍሉ። በቤተሰባችሁ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ወቅት፣ የቤተሰብ አባላት በተለይም ለእነሱ ትርጉም ያላቸውን የግል ጥናቶቻቸው ውስጥ ምንባቦችን እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው።

ዕዝራ ለሰዎች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ

ዕዝራ በኢየሩሳሌም ለሰዎች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ ምስል፣ በኤች. ዊላርድ ኦርትሊፕ © Providence Collection/licensed from goodsalt.com