ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 25–31 (እ.አ.አ)። አስቴር፥ “የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ [ነው]”


“ሐምሌ 25–31 (እ.አ.አ)። አስቴር፥ ‘የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ [ነው]’” ኑ፥ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 25–31 (እ.አ.አ)። አስቴር፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
አስቴር ስትፀልይ

አስቴር፣ በጄምስ ጆህንሰን

ሐምሌ 25–31 (እ.አ.አ)

አስቴር

“የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ [ነው]”

አስቴርን ስታነቡ፣ ለእናንተ የተዘጋጀውን መነሳሳት ከመንፈስ ቅዱስ እሹ፣ እና የምትቀበሉትን ስሜቶች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በመፅሐፈ አስቴር ውስጥ ያሉ ብዙ ክስተቶች እንደ ዕድል ወይም የአጋጣሚ ሊመስሉ ይችላሉ። ወላጅ አልባ አይሁዳዊት ልጅ ህዝቧን ከመታረድ ለማዳን በትክክለኛው ጊዜ የፋርስ ንግሥት እንደሆነች እንዴት በሌላ መልኩ ልታብራሩ ትችላላችሁ? የአስቴር አጎት ልጅ መርዶክዮስ ንጉሱን ለመግደል የተጠነሰሰውን ሴራ ለመስማት የመቻሉ እድል ምን ያህል ነበር? እነዚህ አጋጣሚዎች ነበሩ፣ ወይስ የመለኮታዊ ዕቅድ አካል ነበሩ? ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ እንደጠቀሱት፥ “ተራ አጋጣሚ ሊመስል የሚችል ነገር፣ በእርግጥም፣ በወዳጅ የሰማይ አባት ቀድመው ታይተዋል። … ጌታ በህይወታችን በእያንዳንዱ ጥቃቅን ዝርዝሮች ውስጥ ነው” (“በመለኮታዊ ንድፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ) 56)። በእነዚህ “ጥቃቅን ዝርዝሮች” ውስጥ የጌታን ተጽዕኖ ሁልጊዜ ላናውቅ እንችላለን። ነገር ግን ከአስቴር ተሞክሮ የምንማረው እርሱ በመንገዳችን ሊመራን እንደሚችል እና እኛ የእርሱን አላማ ለሟሟላት በእጆቹ መሳሪያዎች ወደምንሆንበት “እንደዚህ ላለው ጊዜ” (አስቴር 4፥14) እንደሚያዘጋጀን ነው።

ስለመፅሀፈ አስቴር አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አስቴር፣ መጽሀፈ” የሚለውን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

አስቴር

ጌታ ሌሎችን ለመባርክ መሳሪያ ሊያደርገኝ ይችላል።

እህት አን ሲ. ፒንግሬ እንዲህ አስተምረዋል፥ “በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ መሆን ትልቅ መብት እና ቅዱስ ሀላፊነት ነው። የትም ብንኖር፣ ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ የጋብቻ ሁኔታችን ወይም ዕድሜያችን ምንም ይሁን ምን፣ ጌታ በዚህ የዘመን ፍጻሜ ውስጥ የእርሱን መንግሥት በመገንባቱ ውስጥ ልዩ የሆነውን ድርሻችንን እንድንወጣ እያንዳንዳችንን ይፈልገናል” (ለእናንተ ያለውን የጌታን ፍላጎት ማወቅ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2005 (እ.አ.አ)፣ 112)።

የአስቴርን ታሪክ ስታነቡ፣ ይህ ጽሁፍ እንዴት በእርሷ ተግባራዊ እንደሆነ አሰላስሉ። አይሁድን ለማዳን ጌታ ለእሷ የሚያስችሏትን መንገዶች እንዲገኙ እንዳደረገ ፈልጉ (ለምሳሌ፣ አስቴር 2፥21–233፥10–144፥14–16ን ተመልከቱ)። ከዛም ሌሎችን ለመባረክ በሚያስችላችሁ መንገዶች ሕይወታችሁን እርሱ እንዴት እንደመራው አሰላስሉ። “እንደዚህ ላለው ጊዜ” የመሯችሁ ሁኔታዎች ወይም ግንኙነቶች ምንድን ናቸው? (አስቴር 4፥14)። የፓትሪያርክ በረከት ካላችሁ፣ ጌታ ስለእናንተ እንድትሰሩ የሚጠብቀውን ስራ የበለጠ ለማወቅ እሱን ለማንበብ አስቡ።

አስቴር 35፥9–147

ኩራት እና ቁጣ ወደ ውድቀት ሊመራ ይችላል።

በመፅሐፈ አስቴር ውስጥ ከአስቴርና ከመርዶክዮስ ታማኝነት እንዲሁም ከሐማ ኩራት እና ቁጣ እንማራለን። እናንተ አስቴር 35፥9–14ን ስታነቡ፣ የሐማን ስሜቶች፣ ቃላቶች፣ እና ድርጊቶች አስተውሉ። ስለእርሱ እና ስለፍላጎቶቹ ምን ይገልጣሉ? እርሱን ምን ውጤቶች አጋጠሙት ? ( አስቴር 7ን ተመልከቱ)። ሰለ ሐማ ማንበብ ስሜቶቻችሁን እና ድርጊቶቻችሁን ምን እንደሚያነሳሳ እንድትመረምሩ ይገፋፋችሁ ይሆናል። ለውጥ ለምድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋልን? ለእርዳታ ወደሰማይ አባት እንዴት ነው ልትዞሩ የምትችሉት?

በተጨማሪ ምሳሌ 16፥32አልማ 5:28ን ተመልከቱ።

አስቴር 3–45፥2–38፥11–12

መፆም በጌታ ጥገኝነቴን ያሳያል።

አስቴር እና የተቀሩት አይሁድ እንዲጾሙ ያደረጋቸውን ሁኔታዎች አስተውሉ (አስቴር 3፥134፥1–3፣ 10–17ን ተምልከቱ)። ፆም እንዴት ነበር ለእነርሱ በረከት የነበረው? (አስቴር 5፥2–38፥11–12ን ተመልከቱ)። ጌታ ለምንድነው እንድንፆም የሚጠይቀን? (የወንጌል ርዕሶች፣ “ፆም እና የፆም በኩራት፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ)። ጾምን በህይወታችሁ ውስጥ ትልቅ በረከት ለማድረግ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም ኢሳይያስ 58፥6–12ማቴዎስ 4፥1–417፥14–21፤ “Fasting: Young Single Adult Ward, Amanda” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

አስቴር 3፥1–114፥10–175፥1–4

ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ብዙ ጊዜ ብርታትን ይጠይቃል።

መርዶክዮስና አስቴር ለእምነታቸው ሲቆሙ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነበር። ምርጫዎቻችን ከባድ ያልሆኑ መዘዞች አሏቸው፣ ግን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ አሁንም ብርታትን ይጠይቃል። ከአስቴር 3፥1–44፥10–17 ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ብርቱ ስለመሆን ምን ትማራላችሁ? ብርታት ካሳዩ በኋላ መርዶክዮስና አስቴር የደረሰባቸውን የተለያዩ ውጤቶች አስተውሉ (አስቴር 3፥5–75፥1–4 ተምልከቱ)። የሚያስከትለው መዘዝ ምንም ይሁን ምን ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ልክ አስቴር እና መርዶክዮስ ያደረጓቸውን ምርጫዎች ለመምረጥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ምን ማወቅ ይኖርበታል?

በሚቀጥለው ጊዜ ትክክለኛውን ስለማድረግ ውጤቶች ስታስቡ፣ ለሁኔታችሁ በአስቴር 4፥16 ውስጥ የአስቴርን ብርቱ ቃላት ልትተገብሩ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ለራሳችሁ እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ፣ “ትክክለኛውን ስመርጥ፣ [ጓደኞችን ባጣም]፣ [ልጣቸው]።”

ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “ብርታት ይኑራችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 123–27።

ምስል
አስቴር እና ንጉሱ

አስቴር በንጉሱ ፊት፣ በሚኔርቫ ኬ. ቴይቸርት

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

አስቴር 1–10የአስቴርን ታሪክ ከከለሳችሁ በኋላ (“ንግስት አስቴር” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ወይም “For Such a Time as This፣” ቪድዮ ChurchofJesusChrist.org)፣ ቤተሰባችሁ የአንዳንድ ገፀ–ባህሪያትን ለማሳያ አሻንጉሊት በመስራት ይደሰቱ ይሆናል (የእዚህ ሳምንት እንቅስቃሴ ገጽኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ)። ከዚያም ታሪኩን ደግሞ ለመንገር ይጠቀሙበት። እንደ “ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ” (የልጆች መዝሙር፣ 158) ወይም “ትክክለኛውን አድርጉ” (መዝሙር፣ ቁጥር 237) የሚሉ ደፋር እና ሀቀኛ ስለመሆን መዝሙር ልትዘምሩም ትችላላችሁ። በመዝሙሩ ውስጥ የትኛው ቃል አስቴርን ያስታውሱናል?

አስቴር 2፥5–7በፈተና ወቅት የቤተሰብ አባላትን ስለ መርዳት ከመርዶክዮስ ምሳሌ ምን እንማራለን? ከቤተሰባችን ውስጥ ማን ድጋፋችንን ይፈልጋል? ለመርዳት እቅድ አውጡ።

አስቴር 4፥15–17የአስቴር ጀግንነት ቤተሰባችሁ በሚያጋጥሟቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለእውነት ለመቆም ድፍረትን እንዴት ማዳበር እንደሚችሉ እንዲወያዩ ሊያነሳሳቸው ይችላል። “ብጠፋም እጠፋለሁ” ስትል አስቴር ምን ማለቷ ነበር? ደፋር ለመሆን ሲያስፈልገን የእርሷ ቃላት እንዴት ለእኛ ሊተገበሩ ይችላሉ? “Courage” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለው ቪድዮ ጥቂት ምሳሌዎችን ይሰጣል።

አስቴር 9፥26–32የአይሁድ የፉሪም በዓል የአስቴርን ታሪክ ለማስታወስ ተመሰረተ። በዚህ ሳምንት በምግብ ሰዓት፣ ቅድመ አያቶቻችሁን ጨምሮ የቤተሰባችሁ አባላት እንደ አስቴር ለእውነት በመቆም ሌሎችን እንደባረኩ ታሪኮችን ለማጋራት አስቡ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 158።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የአዳኝን ህይወት ተከተሉ። “የጌታ ሌሎችን የማስተማርና ከፍ የማድረግ ሀይል የመጣው በሚኖርበት ህይወት ምክንያት እና ከእርሱ ማንነት ነው። በታታሪነት እንደ ክርስቶስ ለመኖር ስንጥር፣ በበለጠ ልክ እንደ እርሱ ለማስተማር እንችላለን” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር]፣ 13)።

ምስል
አስቴር

ንግስት አስቴር፣ በሚኔርቫ ኬ. ቴይቸርት፣ © William and Betty Stokes

አትም