“በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ማንበብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ማንበብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ማንበብ
ከመፅሐፈ ኢዮብ በፊት በሚመጡት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ በአብዛኛው ታሪኮችን እናገኛለን—ታሪካዊ ክስተቶችን በመንፈሳዊ እይታ የሚገልጹ የትረካ ዘገባዎች። ኖህ መርከብ ሠራ፣ ሙሴ እስራኤልን አዳነ፣ ሐና ወንድ ልጅ እንዲኖራት ጸለየች። የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች በማይረሳ መንገድ ጥልቅ ስሜቶችን ወይም ግዙፍ ትንቢቶችን ለመግለጽ ወደ ግጥማዊ ቋንቋ ስለዞሩ ከኢዮብ ጀምሮ የተለየ የአጻጻፍ ዘይቤ እናገኛለን።
በታሪካዊ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍቶች ውስጥ በሙሉ፣ ጥቂት ግጥማዊ የአጻጻፍ ምሳሌዎችን ጣል ጣል ብለው አይተናል። እና ከመፅሐፈ ኢዮብ በኋላ፣ ያንን በብዛት እንመለከታለን። የኢዮብ፣ መዝሙሮች እና ምሳሌ መጽሐፍት ሙሉ በሙሉ ግጥሞች ናቸው፣ እንዲሁም የኢሳይያስ፣ ኤርምያስ እና አሞጽ ነቢያት ፅሁፎች ክፍልም እንዲሁ ናቸው። ግጥም ማንበብ ታሪክን ከማንበብ የተለየ ስለሆነ፣ እነዚህን መረዳቱ ብዙውን ጊዜ የተለየ አካሄድ ይጠይቃል። የብሉይ ኪዳን ግጥሞች ንባባችሁን የበለጠ ትርጉም ያለው ለማድረግ እንድትችሉ ጥቂት ሃሳቦችን እነሆ።
የዕብራይስጥ ግጥምን ማወቅ
መጀመሪያ፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚየዕብራይስጥ ግጥም፣ እንደ ሌሎች የግጥም አይነቶች፣ ቤት የሚመታ እንዳልሆነ ማወቁ ሊረዳችሁ ይችላል። ምንም እንኳን ምት፣ የቃላት አጻጻፍ እና ድምፆች መደጋገም የጥንት የዕብራይስጥ ግጥም የተለመዱ ባህሪዎች ቢሆኑም፣ በተለምዶ በትርጉም ውስጥ ጠፍተዋል። ወደፊት የምታስተውሉት አንድ ገጽታ ግን አንዳንድ ጊዜ “ትይዩነት” ተብሎ የሚጠራው የሀሳቦች መደጋገም ነው። የዚህ የኢሳይያስ ጥቅስ ቀላል ምሳሌን ይዟል፦
-
ፅዮን ሆይ፣ ሀይልሽን ልበሺ፤
-
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ቆንጆ ልብስሽን ልበሺ (ኢሳይያስ 52፥1)።
29ኛው መዝሙር ብዙ ትይዩ መስመሮች አሉት—አንድ ምሳሌ ይኸው፦
-
የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤
-
የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው (ምሳሌ 29፥4)።
ሁለተኛው መስመር ከመጀመሪያው ጋር ትይዩ መሆኑን ማወቁ ምንባቡን ለመረዳት ቀላል የሚያደርግበት አንድ ምሳሌ ይሄ ነው፦
-
በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥራት፥
-
በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት ሰጠኋችሁ (አሞጽ 4፥6)።
በእነዚህ ምሳሌዎች ውስጥ፣ አንድ ሃሳብ በትንሽ ልዩነት ተደጋግሟል። ልዩነቶቹን የበለጠ በተሟላ ሁኔታ ለመግለጽ ወይም ለማዳበር በሚጠቀሙበት ጊዜ ይህ ዘዴ የተደጋገመውን ሀሳብ አፅንዖት መስጠት ይችላል።
በሌላ ሁኔታዎች፣ ሁለቱ ትይዩ ሃረጎች የተጠናከረ ሃሳቦችን ለማስተላለፍ ተመሳሳይ ቋንቋን ይጠቀማሉ፣ ልክ እንደዚህ ምሳሌ፦
-
የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፤
-
ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች (ምሳሌ 15፥1)።
እነዚህ ተይዩነቶች በድንገት የተከሰቱ አይደሉም። ፀሃፊዎቹ ሆን ብለው ያደረጉት ነው። መንፈሳዊ ስሜቶችን ወይም እውነቶችን ለእነሱ ኃይለኛ እና ቆንጆ በሚመስላቸው መንገድ እንዲገልጹ አስችሏቸዋል። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ጽህፈቶች ውስጥ ትይዩነቶችን ስታስተውሉ፣ እንዴት የጸሃፊዎቹን መልእክት ለመረዳት እንደሚረዳችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ “ጥንካሬን” “በሚያምር ልብስ” እና “ጽዮን”ን ከ“ኢየሩሳሌም” ጋር በማዛመድ ምን ለማለት ሞክሮ ሊሆን ይችላል? (ኢሳይያስ 52፥1)። “የለዘበች መልስ” ለሚለው ሐረግ “ሸካራ ቃል” ተቃራኒው መሆኑን ካወቅን ምን መልእክት ከዚህ ለመውሰድ እንችላለን? (ምሳሌ 15፥1)።
የዕብራይስጥ ግጥም እንደ አዲስ ጓደኛ
የግጥም ንባብን ከአዲስ ሰው ከመገናኘት ጋር ማነጻጸር ለእናንተ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ የብሉይ ኪዳን ግጥም ማንበብን ከሩቅ አገር የመጣን እና እኛ የምናውቀውን ተመሳሳይ ቋንቋ የማይናገር የውጭ አገር ባህል ካለው ሰው ጋር ከመገናኘት ጋር ልታነጻጽሩት ትችላላችሁ፣ በአጋጣሚም ይህ ሰው ከሁለት ሺህ አመት በላይ እድሜያ ያለው ነውእና ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ የሚሆነውን ሰው። ይህ ሰው ምናልባት መጀመሪያ ላይ ያልገባንን ነገር ይናገር ይሆናል፣ ግን እርሱ ወይም እርሷ ለእኛ የሚነገር ምንም ጠቃሚ ነገር የለውም/የላትም ማለት አይደለም። በተወሰነ ትዕግስት እና በተወሰነ ርህራሄ፣ አዲሱ ትውውቃችን በመጨረሻ ወዳጅ ጓደኛ ሊሆን ይችላል። ነገሮችን ከእሱ ወይም ከእሷ አንጻር ለመመልከት በመሞከር አብረን የተወሰነ ጊዜ ማሳለፍ ነው የሚያስፈልገን። ምናልባት በልባችን ውስጥ በትክክል እርስ በርሳችን በደንብ የምንግባባ ሆነን ልናገኝ እንችል ይሆናል።
ስለዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢሳይያስ ምንባብ ስታነቡ፣ አዲስ ላገኛችሁት ሰው እንደ መጀመሪያ ትውውቅ ቁጠሩት። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “ምንድነው መጀመሪያ የተሰማኝ ስሜት?” እያንዳንዱ ቃል ባይገባችሁም እንኳን ምንባብ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋል? ከዚያም እንደገና አንብቡት፣ ከተቻለ ብዙ ጊዜያት። አንዳንድ ሰዎች ምንባቦችን ጮክ ብለው በማንበብ ተጨማሪ ትርጉም ያገኛሉ። የተወሰኑ ኢሳይያስ የመረጣቸውን ቃላትን አስተውሉ፣ በተለይም በአእምሮአችሁ ውስጥ ስዕል የሚስሉ ቃላትን። እነዚህ ምስሎች ምን እንዲሰማችሁ ያደርጋሉ? ኢሳይያስ ምን እንደተሰማው ምስሉ ምን ይጠቁማል? የእነዚህን የብሉይ ኪዳን ገጣሚዎች ቃላትን በበለጠ ባጠናችሁ ቁጥር፣ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ መልእክት ለመግለጽ ሆን ብለው ቃላቶቻቸውን እና ዘዴዎቻቸውን የመረጡ ሆነው ታገኟቸዋላችሁ።
ግጥሞች ስሜታችን እና ልምዶቻችንን እንድንረዳ ስለሚረዱን ግሩም ጓደኞች ሊሆኑ ይችላሉ። የብሉይ ኪዳን ግጥሞች በተለይም ውድ ናቸው፣ ምክንያቱም በጣም አስፈላጊ ስሜቶቻችንን እና ልምዶቻችንን ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ላይ የተዛመዱትን እንድንገነዘብ ይረዱናል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ስታጠኑ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመራን በጣም ጠቃሚ እንደሆነ አስታውሱ። በእርሱ ላይ እምነታችሁን የሚገነቡ ምልክቶችን፣ ምስሎችን እና እውነቶችን ፈልጉ። ስታጠኑ የመንፈስ ቅዱስ ግፊቶችን አዳምጡ።