ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 15–21 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 49–51፤ 61–66፤ 69–72፤ 77–78፤ 85–86፦ “ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ”


“ነሐሴ 15–21 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 49–51፤ 61–66፤ 69–72፤ 77–78፤ 85–86፡ ‘ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 15–21 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 49–51፤ 61–66፤ 69–72፤ 77–78፤ 85–86፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦቸና ለቤተሰቦቸ፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ፋኖስ ይዞ

የጠፋውን ለማዳን በማይክል ቲ. ማልም

ነሐሴ 15–21 (እ.አ.አ)

መዝሙረ ዳዊት 49–5161–6669–7277–7885–86

“ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ”

ይህ ረቂቅ በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ የተጠቀሱትን ጥቂቶቹን ትምህርታዊ ረዕሶች ይለያል። ስታጠኑ፣ አንዳንድ ቃላት፣ ምስሎች፣ ወይም ሃሳቦች ጎልተው ሊታዩአችሁ ይችላሉ። ጌታ ምን ሊያስተምራችሁ እየሞከረ እንደሆነ ይሰማችኋል?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የመዝሙር ጸሐፊዎች በግጥማቸው ጥልቅ ግላዊ ስሜቶቻቸውን አካፈሉ። ስለተስፋ መቁረጥ፣ ፍራቻ፣ እና ፀፀት ስሜት ፃፉ። አንዳንዴም፣ በእግዚአብሔር እንደተረሱ የተሰማቸው ይመስል ነበር፣ እና ጥቂቶቹ መዝሙራት ብዙ ብስጩነት ወይም ተስፋ መቁረጥን ይዘዋል። እንደዚህ አይነት ሰሜቶች መቼም ቢሰማችሁ፣ መዝሙራትን ማንበብ ብቸኛ እንዳልሆናችሁ እንድታውቁ ሊረዳችሁ ይችላል። ነገር ግን እንደዚያ አይነት ስሜቶች ሲኖሯችሁ ሊያበረታቷችህ የሚችሉ መዝሙራትም ታገኛላችሁ፣ ምክንያቱም መዝሙረኞቹ ስለ መልካምነቱ ጌታን አመስግነዋል፣ በኃይሉ ተደንቀዋል፣ እና በምህረቱ ተደስተዋል። አለምን ክፋት እና ኃጢያት እንደተጫናት፣ ነገር ግን ጌታ “መሀሪና ይቅር ባይ” (መዝሙረ ዳዊት 86፥5) እንደሆነ ያውቁ ነበር። በጌታ ላይ እምነት መኖር በጭንቀት፣ በኃጢያት፣ ወይም በፍራቻ በፍጹም ትግል አይኖርም ማለት እንዳልሆነ ገብቷቸው ነበር። ይህም ወደ ማን እንደምትዞሩ ታቃላችሁ ማለት ነው።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 4962፥5–12

ቤዛነት የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 49 ለ“ዝቅተኞችና ከፍተኞች፣ ባለጠጎችና ድሆች” (ቁጥር 2) መልእክት አለው። ይህ መልዕክት ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በመልክቱ ላይ መዝሙረ ዳዊት 62፥5–12 ምን እንደሚጨምር ይሰማችኋል?

እነዚህን መዝሙራት ማንበብ አንዳንድ ሰዎች ቤዛን ለማግኘት ከእግዚአብሔር ሌላ በሆኑ ነገሮች ላይ እምነት የሚያደርጉበትን መንገዶች እንድታሰላስሉ ይገፋፋችሁ ይሆናል (መዝሙረ ዳዊት 49፥6–7ን ተመልከቱ)። “እግዚአብሔር [ነፍሳችሁን] ከሲኦል እጅ ይቤዣታል” የሚለው ምስክርነታችሁ በህይወታችሁ ላይ እንዴት ነው ተጽእኖ የሚያደርገው? (ቁጥር 15)።

በተጨማሪም መዝሙረ ዳዊት 28፥6አልማ 34፥8–17 ተመልከቱ።

መዝሙረ ዳዊት 5185–86

በአዳኙ ምህረት ምክንያት፣ ከኃጢያቶቼ ይቅር ልባል እችላለሁ።

መዝሙረ ዳዊት 51 ውስጥ ያሉት የምህረት ተማጽኖ በዝሙት እና ግድያ ጥፋተኛ በነበረው በንጉስ ዳዊት የተሰጡ ነበሩ (2ኛ ሳሙኤል 11 ተመልከቱ)። ኃጢያቶቻችን አናሳ ቢሆኑም፣ በዚህ መዝሙር ውስጥ የተገለጹትን የምህረት አስፈላጊነት እኛንም ሊነካ ይችላል። ደግሞም ንስሀ መግባት ምን ማለት እንደሆነም ልንማር እንችላለን። ለምሳሌ፣ የመዝሙረ ዳዊት 51 ቃላት እና ሐረጎች ንሰሃ ለመግባት ስለሚያስፈልጉን ባህሪያት ምን ያስተምሯችኋል? በህይወታችሁ ውስጥ የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ሊኖረው ስለሚችል ተጽእኖ ምን ተማራችሁ?

እናንተ መዝሙረ ዳዊት 85–86 ስታነቡ፣ እነዚያኑ ጥያቄዎች ልትጠይቁ ትችላላችሁ። ጌታን የሚገልጹ ሐረጎችንም ልትፈልጉ ትችላላችሁ። እርሱ ይቅር እንደሚላችሁ እነዚህ ሐረጎች እንዴት ነው እምነታችሁን የሚያጠነክሩት? (ለምሳሌ፣ መዝሙረ ዳዊት 86፥5፣13፣ 15 ተመልከቱ)።

በተጨማሪም አልማ 36፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የተሻለ ማድረግ እና የተሻለ መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67–69፤ ካሮል ኤም. ስቲቨንስ፣ “ሊቁ ፈዋሽሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 9–12 ተመልከቱ።

መዝሙረ ዳዊት 51፥13–1566፥16–1771፥15–24

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ምስክርነት ሌሎች ወደ እርሱ እንዲመጡ ሊረዳ ይችላል።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ኃጢያት ክፍያው እንዴት ምስክርነትን እንዳገኛችሁ አሰላስሉ። ከዚያም፣ መዝሙረ ዳዊት 51፥13–1566፥16–1771፥15–24ን ስታነቡ፣ እንዴት ሌሎችን “ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ” ብላችሁ ለመጋበዝ እንደምትችሉ አስቡ (መዝሙረ ዳዊት 66፥5)። ይህ ለእናንተ “አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል” ማለት ምን ማለት ነው? (መዝሙረ ዳዊት 71፥24)። ለሌሎች እንዴት ነው “[ለነፍሳችሁ] ያደረገላትን ልንገራችሁ” የምትሏቸው? (መዝሙረ ዳዊት 66፥16)።

በተጨማሪም ሞዛያ 28፥1–4አልማ 26ን ተመልከቱ።

ምስል
ሁለት ወጣት ወንዶች እርስ በእርስ እየተነጋገሩ

ጌታ ለእኛ ስላደረገልን ያለንን ምስክርነት ለሌሎች ማካፈል እንችላለን።

መዝሙረ ዳዊት 6369; 77–78

በአጣዳፊ ችግሬ ጊዜ ጌታ ይረዳኛል።

ብዙ መዝሙራት፣ በግልጽ ቋንቋ፣ ከእግዚአብሔር የመራቅ ስሜት እና በአጣዳፊ የእርሱን እርዳታ መፈለግ ምን እንደሚመስል ያብራራሉ። እነዚያን ማብራሪያዎች በመዝሙረ ዳዊት 63፥1፣ 869፥1–8፣ 18–2177፥1–9 ውስጥ ለመፈለግ አስቡ። በመዝሙረ ዳዊት 636977–78 ውስጥ ለእነዚህ መዝሙረኞች ማረጋገጫ የሰጣቸው ምን እንደሆነ አገኛችሁን?

በተጨነቃችሁ ጊዜ፣ “የእግዚአብሔርን ሥራ ማስታወስ” እና የእርሱን “የቀደመውን ተአምራትን” ማስታወስ እንዴት ነው የሚረዳችሁ? (መዝሙረ ዳዊት 77፥11)። ጥቂቶቹ ተአምራቶች በመዝሙረ ዳዊት 78 ውስጥ ተብራርተዋል። ሰለ እነርሱ ስታነቡ፣ “ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ” ምን እንደሚረዳ አሰላስሉ (ቁጥር 7)። ከቤተሰባችሁ ታሪክ ተሞክሮዎች ውስጥ ምን ያነሳሳችኋል?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 51፥17የልብ መሰበር ማለት ምን እንደሆነ ለቤተሰባችሁ እንዴት እንደምታስተምሩ አስቡ። ለምሳሌ፣ የቤተስብ አባላት ጠንካራ ሽፋን ያለውን እንደ እንቁላል ወይም ለውዝ የሚሆን ነገርተራ በተራ ሰብሮ መክፈት ትችላላችሁ። ልቦቻችን አንዳንዴ እንደዚያ ሽፋን የሆኑት እንዴት ነው? ልቦቻችንን ለጌታ እንዴት መክፈት እንችላለን? አብሮ መዝሙረ ዳዊት 51ን ማንበብ ጥቂት ሀሳቦችን ሊያመጣ ይችላል።

መዝሙረ ዳዊት 61፥2–3ይእቤተሰብ አባላት በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን ምልክቶች በመሳል እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደ ከፍተኛ “አለት፣” “መጠለያችን፣” እና “ጽኑ ግንብ” እንደሆነ በማብራራት ሊደሰቱ ይችላሉ።

መዝሙረ ዳዊት 71፥1778፥5–7ጌታ ምንድነው “ለልጆቻችሁ እንድስታስታውቁ” የሚፈልገው? (መዝሙረ ዳዊት 78፥5)። ምናልባት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል “ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ” ስለሚረዳቸው እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፣ ተሞክሮ፣ ወይም የግል ምስክርነት አይነት የሆኑ የጌታን “ተአምራት ስራ” ምሳሌ፣ ማካፈል ይችሉ ይሆናል (መዝሙር 71፥1778፥7)።

መዝሙረ ዳዊት 72መዝሙረ ዳዊት 72 የተጻፈው በዳዊት ስለ ልጁ ሰለሞን ነበር፣ ነገር ግን አብዛኛው ስለኢየሱስ ክርስቶስ አተገባበር ሊኖረው ይችላል። ቤተሰባችሁ መዝሙርን ሲያነቡ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያስታውሳቸው ጥቅሶችን ሲያገኙ የአዳኝን ምስል ከፍ አድርገው መያዝ ይችላሉ። “ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይሙላ” የሚለው እንዲሟላ እንዴት ልንረዳ እንችላለን? (መዝሙረ ዳዊት 72፥19፤ በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 65፥2) ይመልከቱ።

መዝሙረ ዳዊት 85፥11ይህ ጥቅስ ዳግም ስለተመለሰው ወንጌል—መፅሐፈ ሞርሞን ከ“ምድር [የወጣ]” እና እንዴት የሰማይ መልዕክተኞች ከ“ሰማይ” እንደመጡ ውይይትን ሊያነሳሳ ይችላል (በተጨማሪም ሙሴ 7፥62ን ተመልከቱ) ተመልከቱ። “Preparation of Joseph Smith: Tutored by Heaven” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለው ቪድዮ እነዚህን ክስተቶች ያሳያል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “I Need Thee Every Hour፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 98።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የተለያዩ መንገዶችን ተጠቀሙ። “ወንጌል በማስተማር ጥረቶቻችሁ ውስጥ ልዩነትን ለመጨመር መንገዶችን ፈልጉ። ያንን ማድረግ ለተሞክሮው ሀብትን እና ውበትን ይጨምራሉ። … መዝሙር፣ ታሪኮች፣ ምስሎች፣ እና ሌሎችም የጥበብ አይነቶችን መጠቀም መንፈስ ቅዱስን ሊጋብዝ እንደሚችል አስቡ” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር]፣ 22)።

ምስል
በኢየሱስ ፊት የተንበረከከ ሰው

ቶማስ፣ አትጠራጠር በጄ.ከርክ ሪቻርድስ

አትም