ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 1–7 (እ.አ.አ)። ኢዮብ 1–3፤ 12–14፤ 19፤ 21–24፤ 38–40፤ 42፥ “እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ”


“ነሐሴ 1–7 (እ.አ.አ)። ኢዮብ 1–3፤ 12–14፤ 19፤ 21–24፤ 38–40፤ 42፥ ‘እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፤ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021(እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 1–7 (እ.አ.አ)። ኢዮብ 1–3፤ 12–14፤ 19፤ 21–24፤ 38–40፤ 42፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ሶስት ግለስቦች በምድር ላይ ያለን ሰው ሲያናግሩ

የኢዮብ ፍርዶች፣ በጆሴፍ ብሪኬይ

ነሐሴ 1–7 (እ.አ.አ)

ኢዮብ 1–312–141921–2438–4042

“እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ”

ስለ ኢዮብ በምታነቡበት ጊዜ፣ ለእናንተ ጠቃሚ የሆኑ አስፈላጊ እውነቶችን እንድታገኙ መንፈስ ይመራችኋል። የምታገኙትን ጻፉ፣ እና እነዚህ እውነቶች እንዴት በእናንተ ተግባራዊነት እንዳላቸው አሰላስሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

መጥፎ ነገሮች ለምን በጥሩ ሰዎች ላይ ይፈጸማሉ ብሎ ማሰቡ ተፈጥሮአዊ ነው—ወይም እንዲሁም፣ ለምን ጥሩ ነገሮች በመጥፎ ሰዎች ላይ ይሆናል። ጻድቅ የሆነው እግዚአብሔር ለምን ያንን ይፈቅዳል? እንደእነዚህ ያሉት ጥያቄዎች መጥፎ ነገሮች ከተከሰቱባቸው ጥሩ ሰዎች መካከል አንዱ በሆነው በኢዮብ ተሞክሮ በኩል ይዳሰሳሉ። በኢዮብ ፈተናዎች ምክንያት፣ ጓደኞቹ በእውነቱ ጥሩ ሰው ሰለመሆኑ ተጠራጠሩ። ኢዮብ የራሱን ጻድቅነት አረጋግጦ ነበር እና እግዚአብሔር በሆነው ሁሉ ጻድቅ ስለመሆኑ አሰበ። ነገር ግን ኢዮብ ቢሰቃይ እናቢደነቅም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጽኑ አቋሙን እና እምነቱን አጥብቆ ቀጠለ። በመፅሐፈ ኢዮብ ውስጥ እምነት ይጠየቃል እና ተፈትኗል ግን በፍፁም ሙሉ በሙሉ አልተተወም። ያም ሁሉም ጥያቄዎች ተመልሰዋል ማለት አይደለም። መፅሐፈ ኢዮብ ግን እስከሚመለሱ ድረስ ጥያቄዎችና እምነት አብረው ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስተምራል፣ እስከዚያው የሚከሰትም ምንም ይሁን ምን ስለ ጌታችን እንዲህ ማለት እንችላለን፣ “እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ” (ኢዮብ 13፥15)።

ስለ መጽሐፈ ኢዮብ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት “ኢዮብ” የሚለውን በቅዱሳት መጽሐፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ላይ ተመልከቱ።

Learn More image
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢዮብ 1–312–13

በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለኝ እምነት በሁሉም ሁኔታዎች ታማኝ እንድሆን ሊረዳኝ ይችላል።

የኢዮብ የመክፈቻ ምዕራፎች የሰይጣንን የጠላት ወይም ከሳሽ ሚና ለማጉላት የታሰበ ነው እንጂ እግዚአብሔር እና ሰይጣን በእውነቱ እንዴት እንደሚገናኙ ለመግለጽ አይደለም። ስለ ኢዮብ የሰይጣንን የይገባኛል ጥያቄዎች በምታነቡበት ጊዜ (ኢዮብ 1፥9–112፥4–5 ተመልከቱ)፣ ስለእናንተ ተመሳሳይ ነገር ሊናገር ይችል እንደሆነ ታስቡ ይሆናል። ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኜ የመቀጠሌ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ብላችሁ ራሳችሁን ትጠይቁ ይሆናል። ለኢዮብ የተሰጡትን ፈተናዎች እና የእርሱን ምላሾች አስቡ (ኢዮብ 1፥20–222፥9–10ን ተመልከቱ)። ለፈተናዎቻችሁ ምላሽ እንድትሰጡ የሚረዳችሁ ከእርሱ ምን ትማራላችሁ?

ምንም እንኳን ኢዮብ ታማኝ ሆኖ ለመኖር ቢሞክርም፣ የእርሱ ፈተናዎች እና መከራዎች ቀጥለው ነበር (በምዕራፍ 3 ላይ ያለቀሰውን ልብ በሉ)። በእውነቱ፣ የእርሱ መከራ የተጠናከረ ይመስላል፣ እናም ጓደኞቹ እግዚአብሔር እየቀጣው እንደነበር ሀሳብ ሰጡ (ኢዮብ 4–5811ን ተመልከቱ)። በምዕራፍ 12–13 ውስጥ ኢዮብ የሰጠውን ምላሽ በከፊል ስታነቡ፣ ኢዮብ መከራውና መልስ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎቹ ቢኖሩም መተማመንን ለመቀጠል ያስችለው ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ምን እንዳወቀ አስቡ። ፈተናዎቻችሁን እንድትጋፈጡ የሚረዳችሁ ስለእግዚአብሔር ምን ታውቃላችሁ? እነዚህን እውነቶች እንዴት ወደማወቅ መጣችሁ፣ እና እምነታችሁን እንዴት አጠናክረውታል?

ኢዮብ 19

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዬ ነው።

አንዳንድ ጊዜ በጣም አስፈላጊው እውነቶች በእኛ ጥልቅ ጭንቀት ውስጥ ነው ለእኛ የሚገለጡት። በኢዮብ 19፥1–22 ውስጥ ኢዮብ የገለጸውን ፈተናዎች እና በኢዮብ 19፥23–27 ውስጥ ባወጀው እውነት ላይ አሰላስሉ። ከዚያም ቤዛችሁ ህያው እንደሆነ እንዴት እንደምታውቁ አስቡ። ይህ እውቀት ከባድ ፈተናዎች ሲያጋጥማችሁ ምን ልዩነትን ያመጣል?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–12122ን ተመልከቱ።

ሰው ወደላይ እየተመለከተ

ኢዮብ፣ በጌሪ ኤል. ካፕ

ኢዮብ 21–24

“ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።”

በኢዮብና በጓደኞቹ መካከል በኢዮብ ሥቃይ በስተጀርባ ያሉ ምክንያቶችን በተመለከተ ክርክር የበለጠ ስታነቡ በክርክሩ እምብርት ላይ እንዴት ለጥያቄው መልስ እንደሚሰጡ ታስቡ ይሆናል፥ ለምንድነው ጻድቃን አንዳንድ ጊዜ የሚሰቃዩት እና ኃጢአተኞች አንዳንድ ጊዜ የማይቀጡት? እናንተ ኢዮብ 21–24ን ስታነቡ ያንን አስቡ። መልስ ለማግኘት የሚረዷችሁ ስለ ሰማይ አባት እና ስለ እቅዱ ምን ታውቃላችሁ? ለምሳሌ 2 ኔፊ 2፥11–13ሞዛያ 23፥21–2324፥10–16አብረሃም 3፥22–26፤ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “በሁሉም ነገሮች ተቃርኖ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 114–17 ተመልከቱ።

በተጨማሪም ኤል. ቶድ በጅ፣ “ቀጣይ እና ጽኑ እምነት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 47–49 ተመልከቱ።

ኢዮብ 384042

የእግዚአብሔር አመለካከት ከእኔ ይበልጣል።

በጓደኞቹ ክስ ተስፋ በመቁረጥ (ኢዮብ 16፥1–519፥1–3ን ተመልከቱ)፣ ኢዮብ ስለ ሥቃዩ ማብራሪያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር ደጋግሞ ጮኸ (ኢዮብ 19፥6–723፥1–931ን ተመልከቱ)። ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል እንዳስተዋሉት፣ ኢዮብ ያደርገው እንደሚመስለው “ሁሉን በሚያውቅ የእግዚአብሔር የጊዜ አጠባበቅ ትዕግሥት በማይኖረን ጊዜ፣ በእውነት እኛ ጥሩውን እንደምናውቅ እናስባለን ማለት ነው። እንግዳ ነ፣ አይደለምን—እኛ የእጅ ሰዓቶችን የምንለብስ የጠፈር ሰዓቶችን እና የቀን መቁጠሪያዎችን የሚቆጣጠረውን ለመምከር እንፈልጋለን” (“በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ተስፋ፣” ኤንዛይን ህዳር 1998 (እ.አ.አ)፣ 63)። ለኢዮብ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ምላሽ በምዕራፎች 38 እና40 ላይ ስታነቡ እነዚህን ቃላት ልብ በሉ። ለኢዮብ ምን እውነታዎችን እያስተማረው ነበር? በዚህ ምድራዊ ኑሮ ውስጥ ከችግሮች እና ጥያቄዎች ጋር ስንታገል እነዚህ እውነታዎችን ማወቃችን ለምን አስፈላጊ ናቸው? በኢዮብ 42፥1–6 ውስጥ የኢዮብ ምላሽ ያስገረማችሁ ምንድነው?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢዮብ 1፥20–22በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተገለጸው ኢዮብ የተሰማውን ስሜት ለመረዳት በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ “ኢዮብን” ማንበብ ወይም ኢዮብ 1፥13–22ን በጭውውት ማሳየት ትችላላችሁ። ከኢዮብ ምሳሌ ምን እንማራለን?

ኢዮብ 14፥14በዚህ ቁጥር ለኢዮብ ጥያቄ እንዴት ነው ምላሽ የምንሰጠው? አልማ 11፥42–44 እንዴት ሊረዳን ይችላል? (በተጨማሪም “He Lives—Celebrate Easter Because Jesus Christ Lives” የሚለውን ቪድዮ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።)

ኢዮብ 16፥1–5እኛ ኢዮብ መጽናኛ ሲፈልግ ሲፈርዱበት እና ሲተቹት እንደነበሩት እንደ ኢዮብ ጓደኞች ነን? (ኢዮብ 16፥1–4፤ በተጨማሪ ዮሐንስ 7፥24 ተመልከቱ)። የእኛ ቃላት ሌሎችን በመከራቸው እንዴት ሊያጠነክሩ ይችላሉ? (ኢዮብ 16፥5 ተመልከቱ)።

ኢዮብ 19፥23–27እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት ቤዛችን ሕያው መሆኑን እንዴት እንደሚያውቁ ሊያካፍሉ ይችላሉ። የምሥክርነት ቃላቶቻችሁን (ወይም ልጆች የሳሏቸውን የአዳኝ ምስል) በመጽሐፍ ውስጥ፣ ለምሳሌ በቤተሰብ መዝገብ ውስጥ፣ ለማስቀመጥ አብራችሁ ልትሰሩ ትችላላችሁ (ቁጥር 23ን ተመልከቱ)። እንደ “አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 34–136) አይነት ስለአዳኝ የሚመሰክሩ መዝሙርን ለመዘመር እና በእርሱ እምነታችሁን የሚያጠነክሩ ሀረጎችን አለመካፈል ትችላላችሁ።

ኢዮብ 23፥8–11“እንደ ወርቅ” ከፈተናዎቻችን “መውጣት” ማለት ምን ማለት ነው? (በተጨማሪ “The Refiner’s Fire,” ChurchofJesusChrist.org የሚለውን ቪድዮተመልከቱ)። ይህን ያደረገ የምናቀው ማን ነው? ልጆች በቁጥር 10 ላይ ከተጻፉት ቃላት አንድ ነገር በማድረግ ሊደሰቱ ይችላሉ። እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ፈተናዎች እንዴት እንዳሸነፈ መወያየት ትችላላችሁ (ሉቃስ 22፥41–44ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19ን ተመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “አዳኜ እንዳለ አውቃለሁ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 135።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በአዕምሮ ተመልከቱ። እራሳችንን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለማስቀመጥ ስንሞክር ትርጉም ያላቸው ግንዛቤዎች ሊመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ እራሳችሁን በኢዮብ ሁኔታ ውስጥ በማስገባት ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማሰላሰል ሊረዳችሁ ይችላል።

ግለስቦች በመድር ላይ ያለውን ሰው ሲያናግሩ

ኢዮብ እና ጓደኞቹ፣ በልያ ረፒን