“ነሐሴ 8–14 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 1–2፤ 8፤ 19–33፤ 40፤ 46፥ ‘እግዚአብሔር እረኛዬ ነው,’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“ነሐሴ 8–14 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 1–2፤ 8፤ 19–33፤ 40፤ 46፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ በዮንግሱንግ ኪም፣ havenlight.com
ነሐሴ 8–14 (እ.አ.አ)
መዝሙረ ዳዊት 1–2፤ 8፤ 19–33፤ 40፤ 46
“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው”
በመዝሙራት ምርጫ ወይም በዚህ ረቂቅ ውስጥ በተዘረዘሩት መርሆዎች ብቻ የመገደብ ስሜት አይሰማችሁ። ወደ ጌታ ለመቅረብ እንዲሰማችሁ ወደሚረዷችሁ እውነቶች መንፈስ ቅዱስ ይምራችሁ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
መዝሙረ ዳዊትን ማን እንደጻፈ በእርግጠኝነት አናውቅም። ጥቂቶቹ ንጉሥ ዳዊት እንደጻፋቸው ይታመናሉ፣ ግን አብዛኞቹ ፀሐፊዎች ስማቸው አልተገለጠም። ሆኖም መዝሙሮችን ካነበብን በኋላ፣ ስማቸውን ባናውቅም እንኳ የመዝሙረኞችን ልብ እንደምናውቅ ሆኖ ይሰማን ይሆናል። እኛ የምናውቀው መዝሙሮች በእስራኤላውያን መካከል ትልቅ የአምልኮ ክፍል እንደነበሩ፣ እና አዳኝ ብዙ ጊዜ እንደጠቀሳቸው ነው። በመዝሙሮች ውስጥ፣ ወደ እግዚአብሔር የጥንት ሰዎች ነፍስ ውስጥ የሚያሳይ መስኮትን እናገኛለን። ስለ እግዚአብሔር ምን እንደተሰማቸው፣ ምን እንዳስጨነቃቸው እና እንዴት ሰላም እንዳገኙ እናያለን። ዛሬ አማኞች እንደመሆናችን፣ በመላው ዓለም፣ አሁንም እነዚህን ቃላት ለእግዚአብሔር አምልኮአችን እንጠቀማለን። የመዝሙረ ዳዊት ጸሐፊዎች ወደ እኛ ነፍስ ውስጥ የሚያሳይ መስኮት የነበራቸው ይመስላል እናም ስለ እግዚአብሔር ያለንን ስሜት፣ ስለምንጨነቅበት እና ሰላምን እንዴት እንደምናገኝ የሚገልጹበት መንገድ ያገኙ ይመስላል።
ስለ መዝሙረ ዳዊት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መዝሙረ ዳዊት“ የሚለውን ተመልከቱ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
መዝሙረ ዳዊት 1፤ 23፤ 26–28፤ 46
መዝሙር ጌታን እንድናምን ያስተምረናል።
ጸሐፊዎቹ ፍርሃትን፣ ሀዘንን ወይም ጭንቀትን ምን ያህል ጊዜ እንደሚገልጹ መዝሙርን ስታነቡ ልብ ትሉ ይሆናል። ለእምነት ሰዎችም እንኳ፣ እንዲህ ያሉት ስሜቶች የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን መዝሙሮችን የሚያነቃቃ የሚያደርጋቸው ቢኖር የሚሰጡዋቸው መፍትሄዎች ናቸው፣ እንዲሁም በጌታ ላይ ሙሉ መታመንን ጨምሮ። እናንተ መዝሙረ ዳዊት 1፤ 23፤ 26–28፤ 46ን ስታነቡ፣ እነዚህን የሚያነሳሱ መልእክቶች አስቡ። የሚከተሉትን አስተውሉ፣ እና ግኝታችሁን ጻፉ፥
-
ጌታን ለመታመን ግብዣ፤
-
ጌታን የሚገልጹ ቃላት፤
-
እርሱ የሚሰጣቸውን ሰላም፣ ጥንካሬ፣ እና ሌሎች በረከቶች የሚገልጹ ቃላት፤
-
እርሱን የሚያምኑትን የሚገልጹ ቃላት፤
መዝሙሮች አእምሯችንን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እና አገልግሎት ይጠቁማሉ።
በርካታ መዝሙሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ያመለክታሉ። በአዲስ ኪዳን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖችም እነዚህን ግንኙነቶች ተመልክተዋል—ለምሳሌ፣ በመዝሙረ ዳዊት 2 ውስጥ ኢየሱስ በንጉሥ ሄሮድስ እና በጴንጤናዊው ጰላጦስ ፊት ለፍርድ እንደቀረበ መጠቀሱን ተገንዝበዋል (የሐዋርያት ሥራ 4፥24–30ን ተመልከቱ)። እነዚህን ለማንበብ አስቡ፦ መዝሙረ ዳዊት 2 እና 22፣ በተጨማሪ ማቴዎስ 27፥35–46፤ ሉቃስ 23፥34–35፤ እና ዮሐነስ 19፥23–24። በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ ባሉ ቃላት እና በአዳኝ ሕይወት መካከል ግንኙነቶችን ፈልጉ እና በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንቶች ውስጥ መዝሙረ ዳዊትን ስታጠኑ ተመሳሳይ ግንኙነቶችን መፈለጋችሁን ቀጥሉ።
መዝሙሮችን በደንብ የሚያውቁ እና ከአዳኝ ሕይወት ጋር ግንኙነቶችን የተመለከቱ በኢየሱስ ዘመን እንደነበሩ አይሁዳዊ አድርጋችሁ እራሳችሁን አስቡ። ይህ እውቀት ለእናንተ ምን ያህል በረከት ሆኖ ነበር?
በተጨማሪም መዝሙረ ዳዊት 31፥5፤ 34፥20፤ 41፥9፤ ሉቃስ 24፥44፤ ዕብራዊያን 2፥9–12ን ተመልከቱ።
መዝሙረ ዳዊት 8፤ 19፤ 33
“የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።”
መዝሙረ ዳዊት 8፤ 19፤ እና 33 ን ማንበብ የጌታን ብዙ ድንቅ ፍጥረቶች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ያን ስታደርጉ ለሃሳባችሁ እና ስሜቶቻችሁ ትኩረት ስጡ። እንዴት የጌታ ፍጥረቶች ለእናንተ “የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ”? (መዝሙረ ዳዊት 19፥1)።
የጌታ ቃል “ልብን ደስ የሚያሰኝ” ኃይለኛ ነው።
በመዝሙራት ውስጥ እንደ ምስክር፣ ሕጎች፣ ትእዛዝ፣ እና ፍርዶች ያሉ ቃላት የጌታን ቃል ሊያመለክቱ ይችላሉ። እናንተ መዝሙረ ዳዊት 19፥7–11ን ስታነቡ ያንን በአእምሮአችሁ ያዙ። እነዚህ ጥቅሶችለእናንተ ስለጌታ ቃል ምን ይጠቁማሉ? መዝሙረ ዳዊት 29 ስለ እርሱ ድምጽ ምን ያስተምራችኋል? በእናንተ ተሞክሮ፣ የጌታ ቃል ወይም ድምጽ ከእነዚህ መግለጫዎች ጋር እንዴት ነው የሚዛመደው?
ወደ ጌታ ፊት ለመግባት በመንፈሳዊ የጠራን እና ንጹህ መሆን አለብን።
በጌታ ፊት መግባት ንጽህናን ይጠይቃል።
በኢየሩሳሌም ያለው ቤተመቅደስ የተገነባው በተራራ ላይ ስለሆነ “የእግዚአብሔር ተራራ” (መዝሙረ ዳዊት 24፥3) የሚለው ሐረግ ቤተ መቅደሱን ወይም የእግዚአብሔርን መኖር ሊያመለክት ይችላል። ያም እናንተ በመዝሙረ ዳዊት 24 ያላችሁ መረዳት ላይ ምን ይጨምራል? “እጆቹ የነጹ፣ ልቡም ንጹሕ” የሆነ ማለት ለእናንተ ምንድን ነው? (መዝሙር 24፥4)።
መዝሙረ ዳዊት 26 እና 27 ስለ ጌታ ቤት ምን ያስተምሯችኋል?
በተጨማሪም መዝሙረ ዳዊት 15፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “እጆቹ የነጹ እና ልቡም ንጹሕ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ)፣ 80–83 ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
መዝሙረ ዳዊት 22።አንድ የቤተሰብ አባል ይህንን መዝሙር ሲያነብ፣ ሌሎች በማቴዎስ 27፥35–46 ውስጥ የሚገኝ ተመሳሳይነትን መፈለግ ይችላሉ። ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለእኛ ስለከፈለው መስዋዕትነት ስሜቶቻቸውን ሊያካፍሉ ይችላሉ።
-
መዝሙረ ዳዊት 23።መዝሙረ ዳዊት 23፣ እንደ “ጌታ እረኛዬ ነው” እና “ጌታ መስኬን ያዘጋጃል” (መዝሙሮች፣ ቁጥሮች 108፣ 109) ላሉ ለብዙ መዝሙሮች መነሳሻ ነበር። ምናልባት ቤተሰባችሁ ከእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ አንዱን መዘመር እና በመዝሙሩ ውስጥ ግጥሞቹን ሊያነሳሱ የሚችሉ ቃላትን መለየት ይፈልጉ ይሆናል። ወይም በመዝሙሩ ውስጥ ያገኙትን አንድ ነገር ስዕሎችን በመሳል እና የቤተሰብ አባላት ከስዕሎቹ ጋር የሚሄዱትን ጥቅሶች ወይም ግጥሞች እንዲገምቱ በማድረግ ሊደሰቱ ይችላሉ። አዳኝ እንደ እረኛ የሆነልን እንዴት ነው?
-
መዝሙረ ዳዊት 24፥3–5።ንፁህ እጆች እና ንፁህ ልብ መኖሩ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ለመስጠት፣ የቤተሰብ አባላት እጃቸውን ሲታጠቡ መዝሙረ ዳዊት 24፥3–5ን ማንበብ ትችላላችሁ። በዚህ መዝሙር ውስጥ እጆች ምን ሊወክሉ ይችላሉ? ልብ ምንን ሊወክል ይችላል? እጃችንን እና ልባችንን በመንፈሳዊ ለማንጻት ምን ማድረግ አለብን?
-
መዝሙረ ዳዊት 30፥5፣ 11።መዝሙረ ዳዊት 30፥5 “ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል” የሚለውን ቃል ኪዳን ይዟል። ጌታ ሀዘናችንን ወደ ደስታ የቀየረው እንዴት ነው? ቁጥር 11 የሚያብራራውን ቤተሰባችሁ በጭውውት መልክ ማሳየት ይችላሉ።
-
መዝሙረ ዳዊት 33።በዚህ መዝሙር ውስጥ ሁሉም ቃል ምን ያህል ጊዜ ጥቅም ላይ እንደዋለ አስተውሉ። በተለይ በቁጥሮች 13–15 ተደጋግሞ ከተጠቀሰው ከዚህ ቃል ስለጌታ ምን እንማራለን?
-
መዝሙረ ዳዊት 46፥10።የቤተሰብ አባላት “እረፉ” እንደሚለው ለማድረግ በአንድነት አንድ ነገርን ልታደርጉ ትችላላችሁ። ማረፍ እግዚአብሔርን ማወቅ እንድንችል እንዴት ሊረዳን ይችላል? እንድናርፍ እና እግዚአብሔርን ወደማወቅ ለመምጣት ምን ዕድሎች አሉን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣” መዝሙር፣ ቁጥር 108።
የግል ጥናትን ማሻሻል
አዲስ ነገር ፈጣሪ ሁኑ። እንደ መዝሙረ ዳዊት ያሉ ቅዱሳት መጻህፍት ሰዎች ጌታን ለማሞገስ አዲስ ፈጠራ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ያነሳሳሉ። በሙዚቃ፣ ግጥም፣ በሚታይ ጥበብ፣ ወይም በሌላ መንገድ መሰጠታችሁን መግለጽ የምትፈልጉ ከሆነ፣ በእነዚያ ስሜቶች ላይ ተግብሩ። በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሌሎች እምነታቸውን እንዲገነቡ ለመርዳት የፈጠራችሁትን ለማካፈል አስቡ።
መልካሙ እረኛ፣ በኬን ስፔንሰር