ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 22–28 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 102–103፤ 110፤ 116–119፤ 127–128፤ 135–139፤ 146–150፥ “እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን”


“ነሐሴ 22–28 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 102–103፤ 110፤ 116–119፤ 127–128፤ 135–139፤ 146–150፥ ‘እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 22–28 (እ.አ.አ)። መዝሙረ ዳዊት 102–103፤ 110፤ 116–119፤ 127–128፤ 135–139፤ 146–150፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስቶስ በቀይ ልብስ በተንበረከኩ ሰዎች ተከቦ

ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

ነሐሴ 22–28 (እ.አ.አ)

መዝሙረ ዳዊት 102–103110116–119127–128135–139146–150

“እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን”

መዝሙረ ዳዊት 119፥105 የእግዚአብሔር ቃል “ለመንገድህ ብርሃን” እንደሆነ ያስተምራል። መዝሙሮችን በምታነቡ ጊዜ፣ እናንተን የሚያነሳሱ እና ወደ ሰማይ አባት የምትመለሱበትን መንገድ ለመግለጽ የሚረዱ ሀረጎችን እና ሀሳቦችን መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ለመዝሙረ ዳዊት ባህላዊ የአይሁድ ስም ትርጉሙም “ውዳሴ” ማለት የሆነው የዕብራይስጥ ቃል ነው። ይህ ቃል ተሂሊም እንዲሁ “ሃሌ ሉያ” ከሚለው ቃል ጋር ይዛመዳል (ትርጉሙም “ያህዌህን አመስግኑ” ወይም “ጌታን አመስግኑ” ማለት ነው)። የመዝሙሮችን ዋና መልእክት ለማጠቃለል አንድ ቃል መምረጥ ቢኖርባችሁ “ውዳሴ” ጥሩ ምርጫ ይሆናል። አንዳንዶቹ መዝሙሮች “እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚለውን ቀጥተኛ ግብዣ ይዘዋል (በተለይም መዝሙረ ዳዊት 146–50 ተመልከቱ)፣ እና ሁሉም የአምልኮ እና የውዳሴ ስሜት ሊያነቃቁ ይችላሉ። መዝሙራት በጌታ ኃይል፣ በምህረቱ እና እርሱ ባደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች ላይ እንድናሰላስል ይጋብዙናል። ለእነዚህ ለየትኛውም ነገሮች እርሱን ልንከፍል አንችልም፣ ነገር ግን ስለእርሱ ማወደስ እንችላለን። ያ ውዳሴ ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ቅርጾች ሊኖሩት ይችላል—ያም መዘመርን፣ መጸለይን ወይም ምስክርነት መስጠትን ሊያካትት ይችላል። ብዙውን ጊዜ ወደ ጌታ እና የእርሱን ትምህርቶች ወደ መከተል ጥልቅ ቁርጠኝነት ይመራል። በሕይወታችሁ ውስጥ “ጌታን አመስግኑ” ማለት ማንኛውም ትርጉም ቢኖረውም፣ መዝሙሮችን በማንበብ እና በማሰላሰል የበለጠ መነሳሳትን ማግኘት ትችላላችሁ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 102–3116

ጌታ በመከራዎቼ ሊያጽናናኝ ይችላል።

መዝሙረ ዳዊት 102፥1–11 ብዙውን ጊዜ በችግር ጊዜ የሚመጡትን የጭንቀት እና የመገለል ስሜቶችን እንዴት እንደሚገልጽ አስተውሉ። ምናልባት እንደዚህ አይነት ስሜቶች አጋጥሟችሁ ይሆናል፣ እና እነዚህ መግለጫዎች ልምዶቻችሁን በተሻለ ለመረዳት ይረዳሉ። ወይም እነዚህ ጥቅሶች የሌሎች የሚሠቃዩ ሰዎች ስሜትን ለመረዳት ይረዱ ይሆናል።

እናንተ መዝሙረ ዳዊት 102፥12–28103116ን ስታነቡ፣ በፈተናዎች ውስጥ “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት” እንደምትችሉ እምነት የሚሰጡ ሀረጎችን ፈልጉ (መዝሙረ ዳዊት 116፥13)። በእርሱ ላይ ተስፋ የሚሰጡ ሀረጎችን ምልክት ማድረግ፣ ማስታወስ ወይም ለሌሎች ማጋራት ትፈልጉ ይሆናል።

በተጨማሪም ኢሳይያስ 25፥82 ቆሮንቶስ 1፥3–7ዕብራውያን 2፥17–18አልማ 7፥11–13፤ ኢቫን ኤ. ሽሙትዝ “እግዚአብሔር ሁሉንም እንባዎች ያብሳል፣” ሊያሆና ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 116–18 ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ሲፈውስ

ፈውስ፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

መዝሙረ ዳዊት 110118

መዝሙር ወደ ጌታ ሊጠቁመኝ ይችላል።

መዝሙሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና አገልግሎት የሚጠቁሙ ምንባቦችን ይዟል። እነዚህም ምሳሌዎች ናቸው፥

እነዚህ ጥቅሶች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን እውነቶችን ያስተምሯችኋል? እነዚህን እውነቶች ማወቅ እንዴት ይባርካችኋል?

በዚህ ሳምንት መዝሙረ ዳዊትን በምታነቡበት ጊዜ፣ ስለ አዳኙ የሚያስተምሯችሁን ሌሎች ምንባቦችን ማስታወስን ቀጥሉ። እንዲሁም ስለእርሱ ለማሰብ የሚረዷችሁን አንዳንድ የምትወዷቸውን መዝሙሮች አንብባችሁ ወይም አድምጣችሁ ይሆናል።

መዝሙረ ዳዊት 119

የእግዚአብሔር ቃል በመንገዱ ላይ ይጠብቀኛል።

ይህ መዝሙር ህይወታችንን ወደ ሰማይ አባት ከመመለስ ጉዞ ጋር የሚያወዳድሩ ብዙ ሀረጎችን ይዟል። በምታነቡበት ጊዜ እንደ መሄድ፣ መንገድ፣ መንገዴ፣ እግሮች፣ እና መራቅ የመሳሰሉ ቃላትን ፈልጉ። የራሳችሁን የሕይወት ጉዞ—የት እንደነበራችሁ፣ አሁን ያላችሁበት እና የት አቅጣጫ እየሄዳችሁ እንደሆነ አስቡበት። ወደ ቤት ዳግም ለመመልስ ስላላችሁ ጉዞ በተመለከተ ከዚህ መዝሙር ምን ትማራላችሁ? በዚህ መዝሙር መሠረት በትክክለኛው ጎዳና ላይ ለመቆየት እንዲረዳችሁ እግዚአብሔር ምን አዘጋጀ?

በትክክለኛው የዕብራይስጥ ቋንቋ በመዝሙረ ዳዊት 119 ውስጥ ያሉት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ቁጥሮች የሚጀምሩት በዕብራይስጥ ፊደል ውስጥ ባለው የመጀመሪያ ፊደል ነው። የሚቀጥሉት ስምንት ቁጥሮች በሚቀጥለው ፊደል ይጀምራሉ፣ እና እስከ ፊደሉ መጨረሻ በኩል እንዲሁ ይቀጥላሉ።

በተጨማሪም ኢሳይያስ 42፥162 ኔፊ 31፥17–21አልማ 7፥19–20ተመልከቱ።

መዝሙረ ዳዊት 134፥36

ጌታ ከማንኛውም ጣዖት የበለጠ ኃይል አለው

በሐሰት አማልክት መታመን ሞኝነት ለምን እንደሆነ በመዝሙረ ዳዊት 135፥15–18 ውስጥ የተሰጡትን ምክንያቶች ልብ በሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከተገለጹት ጣዖታት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ነገር ላይ እምነት ለመጣል በምን ልትፈተኑ ትችሉ ይሆናል?

መዝሙረ ዳዊት 134–36 ውስጥ የተገለጹትን ጌታ ማድረግ የሚችላቸውን ኃይለኛ ነገሮች መዘርዘር ትችላላችሁ። ለእናንተ ምን ኃይለኛ ነገሮችን አድርጎላችኋል?

መዝሙረ ዳዊት 146–50

“እግዚአብሔርን አመስግኑ።”

እነዚህን የመጨረሻ የውዳሴ መዝሙሮች በምታነቡበት ጊዜ ጌታን ለማመስገን ስላላችሁ ምክንያቶች አስቡ። እርሱን ማመስገን ለምን አስፈላጊ ነው? እርሱን የምታመሰግኑበት ምን መንገዶች አላችሁ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 119፥105ምናልባት ቤተሰባችሁ ጨለማ መንገድ ላይ ለማብራት ብርሃን በመጠቀም አብረው በመፍጠር መጓዝ ይችላሉ። ስትጓዙ፣ “በሕይወታችን ውስጥ ምን እንደዚህ ጨለማ አለ?” ወይም “የእግዚአብሔር ቃል እንደ ብርሃን የሆነው እንዴት ነው?” አይነት ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ። እንደ “በብርሃኑ እንድጓዝ እርዱኝ” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 177) ያሉ ስለ እግዚአብሔር ብርሃን መዝሙሮችን መዘመር፣ በመዝሙረ ዳዊት 119፥105 ውስጥ የሚገኙትን መርሆዎች እንድትተገብሩ ሊረዳችሁ ይችላል።

መዝሙረ ዳዊት 127–28ጌታን “[ቤታችንን] እንድንሰራ” ይረዳል ማለት ምን ማለት ነው? (መዝሙረ ዳዊት 127፥1)። ፃድቅ ቤት ለመፍጠር በምናደርገው ጥረት እርሱን በተሻለ እንዴት ማሳተፍ እንችላለን? ቤተሰባችሁን ይህንን ጥያቄ እንዲመልሱ ለመርዳት በወረቀት ላይ አንድ ቤት በመሳል ወረቀቱን እንዲገጣጥሙት መቆራረጥ ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ቁራጭ ጀርባ ላይ የቤተሰብ አባላት ጌታን የቤታችሁ አካል ለማድረግ የሚያስችሏቸውን መንገዶች መፃፍ ወይም መሳል ይችላሉ። ከዚያ የወረቀት ቁርጥራጭ እንቆቅልሹን ማጋጠም ትችላላችሁ። በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ በጌታ መንገዶች እንድንመላለስ የሚያነሳሳን ሌላ ምን እናገኛለን?

መዝሙረ ዳዊት 139ቁጥሮች 1–4 ድረስ ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት እግዚአብሔርን በግል ለማወቅ እንዴት እንደቻሉ ለማውራት ይችላሉ (በተጨማሪ ቁጥሮች 14–15፣ 23–24 ተመልከቱ)።

መዝሙረ ዳዊት 146–50የፀሐፊውን ስሜት ለማስተላለፍ በመሞከር፣ ከመዝሙረ ዳዊት 146–50 ውስጥ የተወሰኑ የመዝሙር ጥቅሶችን ጮክ ብለው እንዲያነቡ የቤተሰብ አባላትን መጋበዝ ትችላላችሁ። ልቦቻችንን ለጌታ እንዴት መክፈት እንችላለን? የቤተሰብ አባላት የራሳቸውን የውዳሴ መዝሙሮች በመፃፍ እና እርስ በእርሳቸው በማካፈል ይደሰቱ ይሆናል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “በብርሃኑ እንድጓዝ እርዳኝ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 177።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የድምፅ ቀረጻዎችን ተጠቀሙ። ለቤተሰባችሁ ስታስተምሩ፣ በChurchofJesusChrist.org ወይም በወንጌል መፅሐፍ ቤት መተግበሪያ ውስጥ የሚገኘውን የቅዱሳት መጻህፍት የድምጽ ቅጂ ለማዳመጥ አስቡ። መዝሙሮችን ማዳመጥ በተለይ ጮክ ብለው የተነበቡትን ማዳመጥ በጣም ኃያል ነው።

ምስል
በጫካ ውስጥ መንገድ

“እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ” (መዝሙረ ዳዊት 119፥35)።

አትም