ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 29–መስከረም4 (እ.አ.አ)። ምሳሌ 1–4፤ 15–16፤ 22፤ 31፤ መክብብ 1–3፤ 11–12፦ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው”


“ነሐሴ 29–መስከረም4 (እ.አ.አ) ምሳሌ 1–4፤ 15–16፤ 22፤ 31፤ መክብብ 1–3፤ 11–12፦ ‘የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 29–መስከረም4 (እ.አ.አ) ምሳሌ 1–4፤ 15–16፤ 22፤ 31፤ መክብብ 1–3፤ 11–12፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦቸና ለቤተሰቦቸ፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳን መጽሐፍትን የሚያጠና ወንድ

ነሐሴ 29–መስከረም 4 (እ.አ.አ)

ምሳሌ 1–415–162231መክብብ 1–311–12

“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው”

የመጽሃፈ ምሳሌ እና የመጽሃፈ መክብብ ጥናትዎ “ጆሮ[ዎ] ጥበብን እንዲያደምጥ [ለማድረግ]፣ ልብ[ዎ]ም ወደ ማስተዋል [እንዲያዘነብል]” እንዴት ሊረዳዎት እንደሚችል ያስቡ (ምሳሌ 2፥2)።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በመጽሐፈ ምሳሌ የመጀመሪያ ምዕራፍ እነዚህን ቃላት እናገኛለን፦ “ልጄ ሆይ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናትህንም ህግ አትተው” (ምሳሌ 1፥8)። መጽሃፈ ምሳሌ ለአፍቃሪ ወላጆች እንደ የጥበብ አባባሎች ስብስብ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፣ ዋና መልዕክቱም የሰላም እና የብልፅግና በረከቶች ጥበብን ለሚሹ ሰዎች እንደሚመጣ ነው—በተለይ እግዚአብሔር እንደሚሰጠው ዓይነት ጥበብ። ነገር ግን ምሳሌ በመክብብ ነው የተከተለው፣ “ያን ያህል ቀላል አይደለም” የሚል ይመስላል። በመክብብ ውስጥ የተጠቀሰው ሰባኪው “ጥበብን [ያ]ውቅ ዘንድ ል[ቡ]ን ሰጠ” ነገር ግን “ትካዜ” እና “የሚጨምር ሀዘንን” አገኘ (መክብብ 1፥17–18)። በተለያዩ መንገዶች መጽሐፉ ይህን ጠየቀ፣ “ሁሉም ነገር ከንቱ፣ ጊዜያዊ እና እርግጠኛ ያልሆነ እንደሆነ በሚመስለው ዓለም ውስጥ ትክክለኛ ትርጉም ይኖር ይሆን?”

እና ይሁን እንጂ ሁለቱ መጽሐፎች ሕይወትን በተለያየ እይታ ቢመለከቱትም ሁሉቱም ተመሳሳይ እውነታዎችን ያስተምራሉ። መጽሃፈ መክብብ ይህን አወጀ፦ “የነገሩን ሁሉ ፍፃሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፣ ትዕዛዙንም ጠብቅ” (መክብብ 12፥13)። ይህ ምሳሌ ውስጥ በሙሉ የሚገኝ አንድ አይነት መርሆ ነው፦ “በፍፁም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን። … በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን” (ምሳሌ 3፥5፣7)። ሕይወት ምንንም ቢይዝ፣ ግራ የሚያጋባ እና የዘፈቀደ ቢመስልም እንኳን፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን ሁሌም የተሻለ ይሆናል።

ስለእነዚህ መጽሐፍት ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መጽሐፈ ምሳሌ” እና “መጽሐፈ መክብብ” የሚሉትን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ምሳሌ 1–415–16

“ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ።”

መጽሐፈ ምሳሌ በጥበብ ግንዛቤዎች የተሞላ ነው። “ጥበብ” እንዲሁም እንደ “እውቀት” እና “መረዳት” ያሉ ተዛማች ቃላትን በ ምዕራፎች 1–4 እና 15–16፣ ውስጥ ሲያገኙ ምልክት ማድረግን ያስቡ። እነዚህ ምዕራፎች ስለጥበብ በሚያስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራሉ? ባገኙት ነገር ላይ በመመስረት “እግዚአብሔር [የሚሰጠውን] ጥበብ” እንዴት ይገልፁታል? (ምሳሌ 2፥6)። “[በልብ] ጠቢብ” ለመሆን የእግዚአብሔርን እርዳታ እንዴት እየሻቱ እንደሆነ ያስቡ (ምሳሌ 16፥21)። ከእግዚአብሔር ጥበብ ምን በረከቶች ይመጣሉ?

እንዲሁም አነዚህን ይመልከቱ ምሳሌ 8–9ማቴዎስ 7፥24–2725፥1–13

ምሳሌ 1፥72፥516፥631፥30መክብብ 12፥13

“እግዚአብሔርን መፍራት” ምንድን ነው?

ሽማግሌ ዴቪድኤ. ቤድናር እንዲህ ገለፁ፦ “ድንጋጤን እና ጭንቀትን ከሚፈጥረው ከዓለማዊ ፍርሃት ይልቅ፣ እግዚብሔርን መፍራት የሰላም፣ የማረጋገጫ እና የመተማመን ምንጭ ነው። … አክብሮትን፣ ክብርን እና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን እድናቆት፤ ትዕዛዛቱን ማክበርን እንዲሁም ለመጨረሻው ፍርድ እና በእርሱ እጅ ለሚሰጠው ፍትህ የመጓጓትን ጥልቅ ስሜት ይይዛል። … እግዚብሔርን መፍራት እርሱን ማፍቀር እና ማመን ነው” (“Therefore They Hushed Their Fears፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 48–49)።

እንዲሁም ምሳሌ 8፥13ይመልከቱ።

ምሳሌ4

“የእግርህን መንገድ አቅና።”

ምሳሌ4 ጥበብን እና ጽድቅን እንደ “መንገድ” ወይም “ጎዳና” ይገልፃል (እንዲሁም ምሳሌ 3፥5–6ይመልከቱ)። ይህን ምዕራፍ ሲያነቡ “የእግር[ዎ] መንገድ” (ቁጥር26) እና እርምጃዎ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያቀርቦት እዲያሰላስሉ የሚረዳዎትን ምንባቦች ሊያገኙ ይችላሉ። ለምሳሌ ቁጥሮች 11–12 እና 18–19 ትክክለኛውን መንገድ መከተል ስለበረከቶች ምን ያስተምራሉ? ቁጥሮች26 እና27 ለእርሶ ምን ማለት ናቸው?

እንዲሁም 2ኛ ኔፊ 31፥18–21ይመልከቱ።

ምሳሌ 15፥1–2፣ 4፣ 18፣2816፥24–32

“የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች።”

ምዕራፎች15 እና16 ውስጥ የተወሰኑት ምሳሌዎች ከሌሎች ጋር በተለይም ከሚወዱት ጋር የሚነጋገሩበትን መንገድ ለማሻሻል ሊያነሳሳዎት ይችላል። ለምሳሌ ከ “ሻካራ ቃል” ይልቅ “የለዘበን መልስ” የተጠቀሙበትን ለየት ያሉ ጊዜዎች ያስቡ (ምሳሌ 15፥1)። በ ምሳሌ 16፥24–32 ውስጥ ያለው ምክር የሚጠቀሙትን ቃላት እንዲያስቡ እንዴት ነው የሚረዳዎት?

ይህን ግንዛቤ ከሽማግሌ ደብሊው.ክሬግ ዝዊክ ያስቡ፦ “‘የለዘብ መልስ’ ምክንያታዊ መልስን—ከትሁት ልብ ስርዓት ያለው ቃላትን ይይዛል። ይህ ማለት በቀጥታ መናገር አንችልም ወይም የትምህርት እውነታን እናስቀራለን ማለት አይደለም። በመረጃ ጠንካራ የሚሆኑ ቃላት በመንፈስ የለዘቡ መሆን ይችላሉ” (“What Are You Thinking?ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣42)።

ምስል
አንድ ሴት የባሕር ወፎችን እየመገበች

ልባም ሴትን ማን ማግኘት ይችላል?II፣ በሉዊስ ፓከር

ምሳሌ 31፥10–31

“እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።”

ምሳሌ 31፥10–31 ስለ “ልባም ሴት” ወይም ታላቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ፣ ችሎታ እና ተፅዕኖ ያላት ሴትን ይገልፃል። እነዚህ እያንዳንዱ ጥቅሶች ስለእርሷ የሚሉትን በራስዎ ቃላት ለማጠቃለል መሞከር ይችላሉ። እርስዎ ሊተገብሯቸው የሚችሉት የተወሰኑ ባህሪዎቿ ምንድን ናቸው?

መክብብ 1–312

ምድራዊ ሕይወት ጊዜያዊ ነው።

መክብብ 1–2 እንደሚጠቅሰው በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉ ብዙ ነገሮች “ከንቱ” (ወይም ጊዜያዊ እና ብዙ ጊዜ የማይጠቅሙ) እንደሆኑ ማስታወስ ለእርሶ ለምን ይጠቅማል? በ ምዕራፍ12 ውስጥ ለሕይወት ዘላለማዊ ዋጋዎችን የሚሰጥ ምን ያገኛሉ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ምሳሌቤተሰቦ የግል “መጽሐፈ ምሳሌ”—ማለትም ከቅዱሳን መጻህፍት እና ከኋለኛው ቀን ነብያት የጥበብ ምክሮች ስብስብ በመፍጠር ሊደሰቱ ይችላሉ።

ምሳሌ 1፥72፥516፥6መክብብ 12፥13–14የቤተሰብ አባላት ምሳሌ 1፥72፥516፥6መክብብ 12፥13ን እንዲገነዘቡ ለመርዳት መፍራት የሚለውን ቃል በ አክብሮት፣ ፍቅር፣ ወይም ታዛዥነት መተካት ሊረዳ ይችላል ( እንዲሁም ዕብራውያን 12፥28ይመልከቱ)። ይህ ስለእነዚህ ጥቅሶች በምናስብበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራል? እግዚአብሔርን እንደምንፈራ የምናሳየው እንዴት ነው?

ምሳሌ 3፥5–7የቤተሰብ አባላት እነዚህ ጥቅሶች የሚያስተምሩትን በምናባቸው እንዲመለከቱ ለመርዳት እንደ ግድግዳ ጠንካራ እና ቋሚ የሆነን ነገር እንዲደገፉ መጋበዝ ይችላሉ። ከዚያም ጠንካራ ያልሆነን ነገር ለምሰሌ የቁም መጥረጊያን ለመደገፉ መሞከር ይችላሉ። ለምንድን ነው “በራ[ሳችን] ማስተዋል [መ]ደገፍ” የሌለብን? ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልባችን እንደምናምን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ምሳሌ 15፥1–2፣1816፥24፣32ቃላቶቻችን በቤታችን ውስጥ ባለው መንፈስ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው? በእርግጥም የቤተሰብ አባላት ከ “ሻካራ ቃል” ይልቅ “የለዘበ መልስ” መስጠትን ሊለማመዱ እና የተማሩትን በእርስ በእርስ ግንኙነታቸው ውስጥ ለመጠቀም ሊሞክሩ ይችላሉ። እንደ “Kindness Begins with Me” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣145) ዓይነት መዝሙር ይህን መርሆ ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ፍቅር ባለበት፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 138–39።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የቅዱሳን መጽሐፍት ቃላት ለሁሉም ሰው ይሰራሉ። የአንዳንድ ቅዱስ ጽሁፍ ምንባቦች ወንዶችን ወይም ሴቶችን ብቻ ይጠቅሳሉ (እንደ ምሳሌ 3፥1331፥10)። ይሁን እንጂ በአብዛኛው፣ በእነዚህ ምንባቦች ውስጥ ያሉት መርሆዎች ለእያንዳንዱ ተግባራዊ ይሆናሉ።

ምስል
ኢየሱስ ሁለት በጎችን በጫካ ውስጥ እየመራ

“በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል” (ምሳሌ 3፥6) ይመራኛል፣ በዮንግሱንግ ኪም፣ havenlight.com

አትም