ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መስከረም 19–25 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 40–49፦ “ሕዝቤን አጽናኑ”


“መስከረም 19–25። ኢሳይያስ 40–49፦ ‘ሕዝቤን አጽናኑ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 19–25። ኢሳይያስ 40–49፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ አይነስውርን ሰው ሲፈውስ

አይነስውር ሰው ሲፈወስ፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች

መስከረም 19–25 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ 40–49

“ሕዝቤን አጽናኑ”

ኢሳይያስ ብዙውን ጊዜ ምልክቶችን ያከካተተ ቋንቋን ተጠቅሟል። እነዚህ ምልክቶች ወደ አዕምሮዎ እና ልቦ ለሚያመጧቸው ሃሳቦች እና ስሜቶች ትኩረት ይስጡ። ይህ ምን እንዳስተማረ የበለጠ ለመገንዘብ ሊረዳዎት ይችላል።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

“አጽናኑ” የኢሳይያስ የመጀመሪያ ቃል ነው ምዕራፍ40። በነብዩ መልዕክት ውስጥ የተለየ ቃናን፣ የተለየ አፅንዖትን መጀመሪያ ምልክት ያደርጋል። የኢሳይያስ የቀድሞ ጽሁፎች እስራኤልን እና ይሁዳን በሃጢያታቸው አማካኝነት ስለሚመጣው መጥፋት እና ምርኮ አስጠነቀቁ፣ እነዚህ የኋላ ትንቢቶች አይሁዶችን ከ150 ዓመታት በኋላ ለማፅናናት የታቀዱ ናቸው—ኢየሩሳሌም ከጠፋች በኋላ ቤተመቅደሱ ረከሰ እና ህዝቦቹ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰዱ። ነገር ግን እነዚህ ትንቢቶች ለተሸነፉት፣ ተስፋ ለቆረጡት እስራኤላውን ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ዘልቆ ይደርሳሉ። አንዳንድ ጊዜ የተሸነፍን፣ ተስፋ የቆረጥን እንዲሁም የጠፋን መስሎ ለሚሰማን እኛን ይናገሩናል።

ለእነሱ እና ለእኛ የኢሳይያስ መልዕክት ቀላል ነው፦ “አትፍሩ” (ኢሳይያስ 43፥1)። ሁሉም አልጠፋም። እግዚአብሔር አልረሳዎትም፣ እና ከቁጥጥሮ ውጪ ለሚመስሉ ሁኔታዎች ኃይል አለው። እግዚአብሔር “ሰማያትን የፈጠረ፣ … ምድርን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን … የሚሰጥ” አይደለምን? (ኢሳይያስ 42፥5)። ከባቢሎን፣ ከሃጢያት፣ ምርኮ አድርጎ ከያዞት ከማንኛውም ነገር የበለጠ ኃያል አይደለምን? “ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ”፣ ብሎ ይለምናል (ኢሳይያስ 44፥22)። ሊፈውስ፣ ሊመልስ፣ ሊያጠነክር፣ ይቅር ሊል እና ሊያፅናና ይችላል—ለእርሶ የሚያስፈልግን ማንኛውንም ነገር ሁሉ፣ እርስዎን ለመቤዠት።

ኔፊ እና ያዕቆብ ኢሳይያስ 48–49 እንዴት ለህዝባቸው እንዳመሳሰሉት ለመማር 1ኛ ኔፊ22 እና 2ኛ ኔፊ6ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 40-49

ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያፅናናኝ እና ተስፋ ሊሰጠኝ ይችላል።

እስራላውያን በባቢሎን ውስጥ ምርኮኞች ሆነው እራሳቸውን ማግኘታቸው ተስፋ የሚያስቆርጥ እንዲሁም ልብ የሚሰብር መሆን አለበት። ብዙዎች እንደእግዚአብሔር የተመረጡ የቃልኪዳን ህዝቦች ቦታቸውን ለዘላለም ያጡ መስሏቸው የነበረ ሊሆን ይችላል። ኢሳይያስ 40–49ን ሲያነቡ መፅናናትን እና ተስፋን የሰጦትን ገፆች ይፈልጉ። በሚያገኙት በእያንዳንዱ ገፅ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር ለ እርሶ የሚለውን ነገር ያሰላስሉ ወይም ይመዝግቡ። ሊጀምሩ የሚችሉባቸው የተወሰኑ ጥቅሶች እነሆ፦

እነዚህን መልዕክቶች መበረታታትን ወይም ተስፋን ለሚፈልግ ሰው እንዴት ማካፈል ይችላሉ? ( ኢሳይያስ 40፥1–2)ይመልከቱ።

እንዲሁም ጀፍሪአር. ሆላንድ፣ “A Perfect Brightness of Hope፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 81–84 ይመልከቱ።

ምስል
ወንዝ በጫካ ውስጥ

እግዚአብሔርን በመታዘዝ “ሰላም … እንደ ወንዝ” ሊኖረን ይችላል (ኢሳይያስ 48፥18)።

ኢሳይያስ 40፥3–8፣ 15–2342፥15–1647፥7–11

የእግዚአብሔር ኃይል ከዓለማዊ ኃይል የላቀ ነው።

ኢሳይያስ ከከበባቸው ከተቃዋሚ ዓለማዊ ኃይል ጋር ሲነፃፀር አቻ ስለሌለው የእግዚአብሔር ኃይል በተደጋጋሚ ለህዝቦቹ አስገነዘበ። ኢሳይያስ 40፥3–8፣ 15–2342፥15–16፤ እና 47፥7–11 ን ሲያነቡ ይህንን መልዕክት ይፈልጉ ( ምዕራፍ47 ለእስራኤል ማራኪዎች ለባቢሎን የተፃፈ መሆኑን ያስተውሉ)። እነዚህ ምንባቦች ስለዓለማዊ ነገሮች ምን ያስተምሮታል? ስለእግዚአብሔር ምን ያስተምሮታል? ይህ መልዕክት ለአይሁዶች በምርኮ ውስጥ ለምን ጠቃሚ እንደነበር ያሰላስሉ። ለእርሶ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

እንዲሁም “Abide with Me!” ይመልከቱ። መዝሙር፣ ቁጥር 166 ይመልከቱ።

ኢሳይያስ 41፥8–1342፥1–743፥9–1244፥21–2845፥1–448፥1049፥1–9

“አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ።”

በመላ ኢሳይያስ 40–49 ውስጥ እግዚአብሔር ስለእርሱ “አገልጋይ” እና ስለእርሱ “ምስክር” ይናገራል። በአንዳንድ ምንባቦች ውስጥ እነዚህ ቃላት ኢየሱስ ክርስቶስን የሚገልፁ ይመስላሉ ( ኢሳይያስ 42፥1–7ይመልከቱ)፣ ሌሎች የእስራኤል ቤትን የሚገልፁ ( ኢሳይያስ 45፥4ይመልከቱ) እና ሌሎች አይሁዶች ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ እና ቤተመቅደስን መልሰው እንዲገነቡ የፈቀደውን ንጉሥ ቂሮስን የሚገልፁ ይመስላሉ ( 44:26–45፥4ይመልከቱ)። በእያንዳንዱ ሁኔታ እንደአገልጋይ እና የጌታ ምስክር ምንባቦቹ እንዴት ለእርሶ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ሊያስቡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ያሰላስሉ፦

ኢሳይያስ 41፥8–1342፥644፥21 እግዚአብሔር ምን እንዲያደርጉ ጠርቶዎታል? እርሱን ለማገልገል ያለዎትን መደበኛ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች እንዲሁም ሌሎች የቃልኪዳን ሃላፊነቶችን ያስቡ። ሲያገለግሉ እርሱ የሚረዳዎት እና “[እጆትን የሚይዘው]” (ኢሳይያስ 42፥6)እንዴት ነው? የእርሱ አገልጋይ እንዲሆኑ “በመከራ እቶን [የፈተኖት]” እንዴት ነው? (እንዲሁም ኢሳይያስ 48፥10ይመልከቱ)።

ኢሳይያስ 43፥9–12 የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር የሆኑት በምን መልኩ ነው? በሕይወቶ ውስጥ እርሱ አዳኝ እንደሆነ ያሳዮት ልምዶች ምንድን ናቸው?

ኢሳይያስ 49፥1–9 ጥረቶ እና አገልግሎቶ “ምንም ጥቅም የሌለው እና ከንቱ” ሲመስል በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምን የሚረዱ መልዕክቶችን ያገኛሉ? (ቁጥር4).

እንዲሁም ሞዛያ 18፥9፤ ሄንሪቢ. አይሪንግ፣ “A Child and a Disciple፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2003 (እ.አ.አ)፣ 29–32 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 40፥3–4“የእግዚአብሔርን መንገድ … ማዘጋጀት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማሰስ ቤተሰቦ የጎበጠን ነገር ማቃናት፣ የተዝረከረከን ወለል ማፅዳት ወይም ድንጋያማ መንገድን ማፅዳት ይችላሉ። የመጥምቁ ዮሐንስን እና የጆሴፍ ስሚዝን ፎቶዎች ማሳየትም ይችላሉ ( የወንጌል የስነጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥሮች 3587ይመልከቱ። ለጌታ መምጣት መንገዱን እንዴት ነው ለማዘጋጀት የረዱት? ( ሉቃስ 3፥2–18ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3ይመልከቱ)። መንገዱን ለእርሱ ለማዘጋጀት መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? (ለምሳሌ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥10ይመልከቱ)።

ኢሳይያስ 40፥2843፥14–1544፥6በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምን ዓይነት የኢየሱስ ክርስቶስ ስሞችን ወይም ማዕረጎችን እናገኛለን። እያንዳንዱ ስም ስለእርሱ ምን ያስተምረናል?

ኢሳይያስ 41፥1043፥2–546፥4እነዚህ ጥቅሶች በ “How Firm a Foundation” (መዝሙሮች፣ ቁጥር.85) መዝሙር ውስጥ ተገልፀዋል። የቤተሰቦ አባላት መዝሙሩን በጋራ መዘመር እና በእነዚህ ስንኞች ውስጥ የሚመሳሰሉ ሃረጎችን ከጥቅሶቹ በማግኘት ሊደሰቱ ይችላሉ። እነዚህ ሃረጎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሩናል?

ኢሳይያስ 44፥3–445፥8እነዚህን ጥቅሶች ካነበቡ በኋላ፣ እግዚአብሔር በረከትን ስላፈሰሰባቸው ሲናገሩ ቤተሰቦ አንድን ተክል ውኃ ማጠጣት ይችላሉ። አንድን ተክል ውኃ ስናጠጣው ምን ይሆናል? እግዚአብሔር ሲባርከን ከእኛ ምን ይጠብቃል?

ኢሳይያስ 48፥17–18የወንዞችን እና የባሕር ማዕበሎችን ፎቶዎች ወይም ቪድዮዎች ማሳየትን ያስቡ። ሰላም እንደወንዝ መሆን የሚችለው እንዴት ነው? ጽድቅ እንደ ማዕበሎች መሆን የሚችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “How Firm a Foundation፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 85።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ቃላትን ይተርጉሙ። በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ የማይረዱትን ቃላት—እና የሚረዱትንም ቃላት ጨምሮ ትርጉሞችን ለመመልከት ይሞክሩ። አንዳንድ ጊዜ ትርጉሞች አንድን ጥቅስ በተለየ መልኩ ለማንበብ እና አዲስ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ለማግኘት ሊረዱዎት ይችላሉ።

ምስል
ኢየሱስ ከሴት ልጅ እና ከወንድ ጋር

“እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና ለችግረኞቹም ራርቶአል” (ኢሳይያስ 49፥13)።በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት፣ በአን አዴል ሄንሪ

አትም