ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መስከረም 12–18 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 13–14፤ 24–30፤ 35፦ “ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን”


“መስከረም 12–18። ኢሳይያስ 13–14፤ 24–30፤ 35፦ ‘ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 12–18። ኢሳይያስ 13–14፤ 24–30፤ 35፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ በቅዱስ ጫካ ውስጥ የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ሲመለከት

ቅዱስ ጫካ፣ በብሬንት ቦረፕ

መስከረም 12–18 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ 13–1424–3035

“ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን”

ፕሬዚደንት ቦኒኤች. ኮርደን እንዲህ አስተማሩ፣ “ቅዱሳን መጽሐፍት አዕምሮአችንን ያበሩታል፣ መንፈሳችንን ይመግቡታል፣ ጥያቄዎቻችንን ይመልሳሉ፣ በእግዚአብሔር ያለንን እምነት ይጨምራሉ እንዲሁም ሕይወቶቻችንን በእርሱ ላይ እንድናተኩር ይረዱናል” (“Trust in the Lord and Lean Not፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣7)።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

እግዚአብሔር ነብያቶችን እንዲያደርጉ ከጠየቃቸው ነገሮች አንዱ ስለሃጢያት ውጤቶች እንዲያስጠነቅቁ ነው። የብሉይ ኪዳን ነብያትን አስመልክቶ ይህ ብዙ ጊዜ የታላቅ መንግሥታት ሃያል መሪዎች ንስሃ እንዲገቡ አለበለዚያ እንደሚጠፉ መንገር ማለት ነበር። አደገኛ ስራ ነበር ነገር ግን ኢሳይያስ አልፈራም ነበር እናም—ለእስራኤል፣ ለይሁዳ እና በዙሪያው ላሉ አገራት ጨምሮ—በእሱ ቀን ለነበሩት መንግሥታት ማስጠንቀቂያው ደፋር ነበር ( ኢሳይያስ 13–23ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ ኢሳይያስ የተስፋ መልዕክትም ነበረው። ምንም እንኳን የተተነበየው ጥፋት በእነዚህ መንግሥታት ላይ በመጨረሻ ቢመጣም ኢሳይያስ የመመለስ እና የመታደስ እድልን ተነበየ። እግዚአብሔር ህዝቦቹን ወደ እርሱ እንዲመለሱ ይጋብዛል። “ደረቂቱን ምድር ኩሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ” እንዲሆን ያደርጋል” (ኢሳይያስ 35፥7)። ለእስራኤላውያን ቃል የገባላቸውን በረከቶች በመመለስ “ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን” ያደርጋል (ኢሳይያስ 29፥14)። ኢሳይያስ ወይም በዛ ሰዓት በሕይወት ያለ ማንኛውም ሰው ይህን ድንቅ ነገር ለማየት አልቻሉም። ነገር ግን የመጨረሻ ፍጻሜውን ዛሬ እያየነው ነው። በእርግጥም የእሱ አካል ነን!

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 13፥1–11፣ 19–2214፥1–20

የዓለም ክፉ መንግሥታት እና መሪዎቻቸው ይወድቃሉ።

ኢሳይያስ 13–14 (ነብያዊ መልዕክት ስለ) ባቢሎን “ሸክም” ተብሎ ይጠራል (ኢሳይያስ 13፥1)። አንዴ ከኃያል መሪ ጋር ታላቅ መንግሥት የነበረችው ባቢሎን ዛሬ የጥንት ታሪክ ተደርጋ ነው የምትቆጠረው። ስለዚህ ለባቢሎን የተነገረው መልዕክት ዛሬ ለእኛ የሚጠቅሙት ለምንድን ነው? በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ባቢሎን ኩራትን፣ ዓለማዊነትን እና ሃጢያትን ትወክላለች እናም ዛሬ በእነዚህ ሁሉ ተከበናል። ኢሳይያስ 13፥1–11፣ 19–2214፥1–20ን ሲያነቡ የዚህን ምልክት ያስቡ። እንደእነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችንም ማሰብ ይችላሉ፦

  • ኢሳይያስ ለባቢሎን የሰጣቸው ማስጠንቀቂያዎች አዳኙ ለሁለተኛ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ካሉት የዓለም ትንቢቶች ጋር እንዴት ይመሳሰላሉ? ( ኢሳይያስ 13፥1–11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥26–42ይመልከቱ)።

  • በባቢሎን ንጉሥ ኩራት እና በሰይጣን ኩራት መካከል ምን ዓይነት ተመሳሳይነትን ያያሉ? ( ኢሳይያስ 14፥4–20ሙሴ 4፥1–4ይመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለራሶ ምን ዓይነት ማስጠንቀቂያዎችን ያገኛሉ?

  • አዳኙ እንዴት ነው “ከሃዘን እና ከመከራ … [የሚያሳርፈን]”? (ኢሳይያስ 14፥3)።

ምስል
ኢየሱስ በቀይ ልብስ

ሊመራ እና ሊነግሥ ተመልሶ ይመጣል፣ በሜሪአር. ሳወር

ኢሳይያስ 24፥21–2325፥6–826፥1928፥16

የኢሳይያስ ጽሑፎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቁሙኛል።

የኢሳይያስ ትምህርቶች ብዙውን ጊዜ የሃጢያት ክፍያውን፣ ትንሳኤውን እና ሁሉተኛ ምፅአቱን ጨምሮ የአዳኙን ተልዕኮ ይጠቅሳሉ ። የሚከተሉትን ጥቅሶች ሲያነቡ ምን ዓይነት የተልዕኮው ገፅታዎች ወደ አዕምሮዎ ይመጣሉ፦ ኢሳይያስ 24፥21–2325፥6–826፥1928፥16? ስለአዳኙ የሚያስታውሶትን ሌሎች ምን ምንባቦች ያገኛሉ?

እንዲሁም ኢሳይያስ 22፥22–25ይመልከቱ።

ኢሳይያስ 24፥1–1228፥7–829፥7–1030፥8–14

ክህደት ማለት ከእግዚአብሔር እና ከነብያቶቹ ፊትን ማዞር ማለት ነው።

ከእግዚአብሔር ፊትን የማዞርን እና ነብያቶቹን ውድቅ የማድረግን ወጤቶች ለማስጠንቀቅ ኢሳይያስ የተለያዩ ምሳሌያዊ ንግግሮችን ተጠቀመ። እነዚህም ባዶ ምድርን (ኢሳይያስ 24፥1–12)፣ ስካርን (ኢሳይያስ 28፥7–8)፣ ርሃብ እና ጥማትን (ኢሳይያስ 29፥7–10) እና የፈረሰ ቅጥር ወይም ገልን (ኢሳይያስ 30፥8–14) ያካትታሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በሚያነቡት መሰረት ቃልኪዳኖቻችንን መጠበቅ ለምን ይጠቅማል? ለእግዚአብሔር እና ለአገልጋዮቹ ታማኝ ለመሆን ምን እያደረጉ እንዳሉ ያስቡ።

እንዲሁም ኤም.ረስል ባላርድ፣ “Stay in the Boat and Hold On!ሊያሆና፣ ህዳር 2014 (እ.አ.አ)፣ 89–92፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ክህደት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።

ኢሳይያስ2930፥18–2635

እግዚአብሔር የጠፉ ወይም የተሰበሩ ነገሮችን መመለስ ይችላል።

ሰዎች ወይም ማህበረሰቦች ፊታቸውን ከእግዚአብሔር ሲያዞሩ፣ ሰይጣን ውጤቶቹ የማይለወጡ እንደሆኑ አድርገን እንድናስብ ይፈልጋል። ይሁን እንጂ፣ ኢሳይያስ ሰዎች ንስሃ ሲገቡ እና ወደ እርሱ ፊታቸውን ሲመልሱ እግዚአብሔር የሚያደርገውን አንዳንድ ድንቅ ነገሮች ይገልፃል። ከ ኢሳይያስ 29፥13–2430፥18–2635 ስለጌታ፣ ስለፍቅሩ እና ስለኃይሉ ምን ይማራሉ?

በዘመናችን እግዚአብሔር ኃይሉን ከገለጠበት መንገድ አንዱ ወንጌሉን ዳግም መመለሱ ነው። ኢሳይያስ29 ከዳግም መመለስ ክስተቶች ጋር የሚዛመዱ የተለያዩ ምንባቦችን ይዟል። ለምሳሌ:

እነዚህን ገፆች ሲያነቡ ስለወንጌል መመለስ ምን ሃሳቦች እና ስሜቶች አልዎት?

እንዲሁም “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፦ ለሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ የሚሆን ለአለም የተላለፈ አዋጅ” (ChurchofJesusChrist.org)ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 25፥4–9ቤተሰቦ ከአውሎ ነፋስ ወይም ከሃሩር የበጋ ቀን የመከለል በረከት አጋጥሞት ያውቃልን? ( ቁጥር4ይመልከቱ)። እነዚህን ጥቅሶች እና በ ኢሳይያስ 25፥4–9ውስጥ ስላሉ ሌሎች የጌታ መግለጫዎች ሲያነቡ ስለዚህ ይነጋገሩ። እግዚአብሔር እንዴት ነው እንደነዚህ ነገሮች የሆነው?

ኢሳይያስ 25፥8–926፥19በጌቴሴማኒ ውስጥ፣ በመስቀል ላይ እና ከትንሳኤው በኋላ የሚያሳዩትን የአዳኙን ፎቶዎች ማሳየት የቤተሰብ አባላት በእነዚህ ጥቅሶች እና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ያሉትን ግንኙነቶች እንዲመለከቱ ሊረዳቸው ይችላል ( የወንጌል ስነጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥሮች 56575859ይመልከቱ)። ቤተሰቦ ለምን “በማዳኑ ደስ [እንደሚላቸው]” እንዲያካፍሉ ይጋብዙ (ኢሳይያስ 25፥9)።

ኢሳይያስ 29፥11–18እነዚህ ጥቅሶች ቤተሰቦ ስለወንጌል መመለስ እና ስለመጽሐፈ ሞርሞን መምጣት “ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን” (ቁጥር14) እንዲወያዩ ሊረዱ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች ለእኛ ድንቅ እና ተአምራት የሆኑት ለምንድን ነው? የቤተሰብ አባላት የመመለስ ድንቅ በረከቶችን የሚወክሉ ቁሳቁሶችን በቤቶ ውስጥ እንዲያገኙ ይጋብዙ።

ኢሳይያስ35ቤተሰቦ ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመችን ጽዮንን እንዴት እየገነባ እንዳለ ለመገንዘብ የሚረዱ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉ ምስሎችን በመሳል ሊደሰቱ ይችላሉ። ከእነዚህ ምስሎች ምን እንማራለን? የጽዮንን ግንባታ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “On a Golden Springtime፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣88።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ልጆች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ ፍቀዱ። ልጆች ከወንጌል መርሆ ጋር የሚዛመድን ነገር ሲፈጥሩ መርሆውን የበለጠ እንዲገነዘቡት ይረዳቸዋል። እንዲገነቡ፣ እንዲስሉ፣ ቀለም እንዲቀቡ፣ እንዲፅፉ እና እንዲፈጥሩ ይፍቀዱላቸው። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣25ን ይመልከቱ።)

ምስል
ማርያም እና ዮሐንስ ኢየሱስን በመስቀል ላይ እንዳለ ሲመለከቱ

“እነሆ አምላካችን ይህ ነው፣ ተስፋ አድርገነዋል፣ ያድነንማል” (ኢሳይያስ 25፥9)። ጄምስ ቲሶት [ፈረንሳይኛ 1836–1902 (እ.አ.አ)]። አንቺ ሴት፣ እነሆ ልጅሽ (ስታባት ማተር)፣ 1886–1894 (እ.አ.አ)። ብርሃን የማያስተላልፍ የውኃ ቀለም በግራፋይት ላይ በግራጫ የተሸመነ ወረቀት ላይ፣ ምስል፦ 11 11/16 x 6 ኢ (29.7 x 15.2 ሴሜ)። የብሩክሊን ሙዚየም፣ በህዝብ ምዝገባ የተገዛ፣ 00.159.300

አትም