ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መስከረም 5–11 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 1–12፦ “አምላክ መድሀኒቴ ነው”


“መስከረም 5–11 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 1–12፦ ‘አምላክ መድሀኒቴ ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 5–11 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 1–12፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የጥንት ነቢይ ጽሁፍ

ነብዩ ኢሳይያስ ስለ ክርስቶስ ልደት ተነበየ፣ በሃሪ አንደርሰን

መስከረም 5–11 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ 1–12

“አምላክ መድሀኒቴ ነው”

ሲያጠኑ መንፈሳዊ ምሪትን ይፈልጉ። ኔፊ እንዳስተማረው የኢሳይያስን ቃላት የበለጠ መረዳት የምንችለው “በትንቢት መንፈስ [ስንሞላ]” ነው (2ኛ ኔፊ 25፥4)።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

ምንም እንኳን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነቡ ይህ የመጀመሪያዎ ቢሆንም አስቀድመው የሚያውቋቸው የሚመስሉ ምንባቦችን ሊያገኙ ይችላሉ። የዚያም ምክንያት፣ ከሁሉም የብሉይ ኪዳን ነብያት መጽሃፈ ኢሳይያስ በሌሎች መጽሐፎች ውስጥ በአዳኙም በራሱ ጭምር ብዙ ጊዜ በመጠቀሱ ምክንያት ነው። የኢሳይያስ ቃላት ብዙ ጊዜ በመዝሙሮች እና በሌሎች ቅዱስ ሙዚቃዎች ውስጥም ይቀርባሉ። ለምንድን ነው ኢሳይያስ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰው?

በእርግጥ ከምክንያቶቹ አካል አንዱ መጽሃፈ ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ቃል በግልፅ በሚታወስ ቋንቋ የመግለፅ ስጦታ ስለነበረው ነው። ነገር ግን ከዚያም በላይ ነው። ያስተማራቸው እውነታዎች የእርሱን ትውልድ—ከ740 እስከ 701 ከክርቶስ ልደት በፊት ባሉት አመታት ሲኖሩ የነበሩ እስራኤላዊያንን—በመሻገራቸው ምክንያት ኢሳይያስ በብዙ ትውልዶች ውስጥ የነበሩ ነብያትን አነሳስቷል። የእርሱ ሚና ለእግዚአብሔር የቤዛነት ስራ አይኖቻችንን መክፈት ነበር እሱም ከአንድ አገር ወይም ከአንድ የጊዜ ዘመን የበለጠ ትልቅ ነው። ኔፊ እሱ እና ህዝቦቹ ምንም እንኳን ከተቀሩት እስራኤላውያን ቢለዩም አሁንም ድረስ የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝቦች እንደሆኑ ከኢሳይያስ ተማረ። በመጽሃፈ ኢሳይያስ ውስጥ፣ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ስለመሲሁ በፊታቸው እየተፈጸሙ ያሉ ትንቢቶችን አገኙ። እናም በመጽሃፈ ኢሳይያስ ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ በኋለኛው ቀን እስራኤልን የመሰብሰብ ስራ እና ጽዮንን የመገንባት መነሳሳትን አገኘ። መጽሃፈ ኢሳይያስን ሲያነቡ ምን ያገኛሉ?

ስለኢሳይያስ እና ጽሑፎቹ የበለጠ መረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኢሳይያስ” የሚለውን ይመልከቱ። ኢሳይያስ ስለኖረበት ጊዜ መረጃን ለማግኘት 2ኛ ነገሥት 15–20 እና 2ኛ ዜና መዋዕል 26–32ን ይመልከቱ።

ምስል
Learn More image
ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 1–12

የኢሳይያስን ትምህርቶች በጥሩ ሁኔታ እንዴት መረዳት እችላለሁ?

አዳኙ ስለኢሳይያስ ጽሑፎች ሲናገር እንዲህ አለ፣ “እነዚህን ነገሮች በትጋት [ፈልጉ]፤ … የኢሳይያስ ቃላት ታላቅ ናቸውና” ( 3ኛ ኔፊ 23፥1–3ይመልከቱ)። ይሁን እንጂ ለብዙዎች መጽሃፈ ኢሳይያስን መረዳት ከባድ ሊሆን ይችላል። በኢሳይያስ ቃላት ውስጥ ታላቅ ትርጉምን ለማግኘት ለመርዳት የተወሰኑ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ፦

  • ኢሳይያስ የተጠቀማቸውን ምልክቶች እና ምሳሌያዊ ንግግሮች ያሰላስሉ። ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ ስለወይን ቦታ ( ኢሳይያስ 5፥1–7ይመልከቱ)፣ የሰሊሆም ውኃ ( ኢሳይያስ 8፥5–10ይመልከቱ) ምልክት ( ኢሳይያስ 5፥26ይመልከቱ) እና ስለሰንደቅ አላማ ( ኢሳይያስ 11፥10፣12ይመልከቱ) ሲፅፍ ምን ለመናገር እንደፈለገ የሚያስቡትን ያሰላስሉ።

  • እያንዳንዱን ምዕራፍ ሲያነቡ እራሶን “ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን እየተማርኩኝ ነው?” ብለው ይጠይቁ ( 1ኛ ኔፊ 19፥23ይመልከቱ)።

  • ለቀናችን ተገቢ የሚመስሎትን ርዕሶች ይፈልጉ ለምሳሌ እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እና ተልዕኮ፣ የእስራኤል መበተን እና መሰብሰብ፣ የመጨረሻ ቀናት እና የሁለት ሺህ ዓመታት። ከመጽሃፈ ኢሳይያስ ስለእነዚህ ርዕሶች የሚያስተምሩ ማጣቀሻ ዝርዝሮችን ይመዝግቡ።

  • በሚፈለግበት ቦታ የጥናት እርዳታን ይጠቀሙ ለምሳሌ መዝገበ ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ የግርጌ ማስታወሻዎች፣ የምዕራፍ መግቢያዎች እና ቅዱሳን መጻህፍት መምሪያ

እንዲሁም 2ኛ ኔፊ 25፥1–8ይመልከቱ።

ኢሳይያስ135

“ክፉ ማድረግን ተዉ።”

ኢሳይያስ የይሁዳን መንግስት ስለመንፈሳዊ ሁኔታቸው በተደጋጋሚ አስጠነቀቀ። ኢሳይያስ13፣ እና5ን ካነበቡ በኋላ የህዝቡን መንፈሳዊ ሁኔታ እንዴት ሊገልፁት ይችላሉ? ለቀናችን ተግባራዊ እንደሆኑ የሚሰሙ ምን ማስጠንቀቂያዎችን ያገኛሉ?

ከማስጠንቀቂያው በተጨማሪ ለሃጥያተኛዋ እስራኤል የተስፋ መልዕክቶችን ማሳታወሻ መያዝ ይችላሉ (ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 1፥16–20፣ 25–273፥10ን ይመልከቱ)። ከእነዚህ መልዕክቶች ስለእግዚአብሔር ምን ይማራሉ?

ኢሳይያስ2411–12

በኋለኛው ቀናት እግዚአብሔር ታላቅ ስራን ይሰራል።

ብዙ የኢሳይያስ ጽሑፎች ለቀናችን ለየት ያለ ትርጉም የያዙ ትንቢቶች ናቸው። በ ምዕራፎች2411–12 ውስጥ ካሉ የኢሳይያስ የኋለኛው ቀናት መግለጫዎች በተለይ እርሶን የሚያነሳሱት የትኞቹ ናቸው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113፥1–6 ስለ ኢሳይያስ11፣ የሚረዱ ግንዛቤዎችን ያቀርባል።) ስለእስራኤል መሰብሰብ እና ስለጽዮን መቤዠት ምን ይማራሉ? እነዚህን ምዕራፎች ካነበቡ በኋላ ምን ለማድረግ ይነሳሳሉ?

እንዲሁም ኢሳይያስ 5፥2610፥20ይመልከቱ።

ኢሳይያስ6

ነብያት በእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው።

ምዕራፍ6፣ ውስጥ ኢሳይያስ ነብይ ተደርጎ ስለተጠራበት ጥሪ ዘገበ ። ይህን ምዕራፍ ሲያነቡ ኢሳይያስ ስላጋጠመው ነገር ምን አስደነቆት? ይህ ምዕራፍ ስለእግዚአብሔር፣ ስለነብያቶቹ እና እንዲሰሩ ስለተጠሩት ስራ በሚያስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያደርጋል?

ምስል
አንድ ሴት ልጅ ታቅፋ

“ህፃንም ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና” (ኢሳይያስ 9፥6)።

ኢሳይያስ 7–9

አሳይያስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረ።

በኢሳይያስ አገልግሎት መጀመሪያ ላይ የእስራኤል መንግስት (ኤፍሬም ተብሎም ይጠራ የነበረ) ከአሲሪያውያን እራሱን ለመከላከል ከሶሪያ ጋር ህብረት ፈጠረ። እስራኤል እና ሶሪያ የይሁዳውን ንጉሥ አካዝን የእነሱን ህብረት እንዲቀላቀል ለመግፋት ፈለጉ። ነገር ግን ህብረቱ እንደሚወድቅ ኢሳይያስ ተነበየ እናም አካዝን በእግዚአብሔር እንዲያምን መከረው ( ኢሳይያስ 7–9፣ በተለይ ኢሳይያስ 7፥7–98፥12–13ይመልከቱ)።

ኢሳይያስ አካዝን ሲመክር ብዙ ታዋቂ የሆኑ ትንቢቶችን አደረገ እነሱም በ ኢሳይያስ 7፥148፥13–149፥2, 6–7ውስጥ ይገኛሉ። በአካዝ ጊዜ እነዚህ ትንቢቶች ምን ማለት እንደሆኑ ሙሉ በሙሉ ግልፅ ባይሆንም ለኢየሱስ ክርስቶስ በግልፅ ይሰራሉ (እንዲሁም ማቴዎስ 1፥21–234፥1621፥44ሉቃስ 1፥31–33ይመልከቱ)። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኝ ምን ይማራሉ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 1፥16–18የቤተሰብ አባላት እነዚህን ጥቅሶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት “Some of Us Feel We Can Never Be Good Enough” የሚለውን ክፍል ከእህት ሼረን ዩባንክ መልዕክት “Christ: The Light That Shines in Darkness” [ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ.)፣75] ማንበብ ይችላሉ። ወይም ቆሻሻዎች ከልብስ እንዴት እንደሚወገዱ ማሳየት ይችላሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለው የጌታ መልዕክት ሰይጣን እንድናምን ከሚፈልገው ጋር የሚለየው እንዴት ነው?

ኢሳይያስ 2፥1–5የቤተሰብ አባላት ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ አንዱን በመምረጥ የሚገልፀውን መሳል ይችላሉ። ቤተመቅደስ ስለእግዚአብሔር መንገዶች ምን ይነግረናል? “በእግዚአብሔር ብርሃን [ስንሄድ]” እንዴት ነው የምንባረከው? (ኢሳይያስ 2፥5)።

ኢሳይያስ 4፥5–6በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር ምን ቃልኪዳን ይገባልናል? እነዚህ ቃልኪዳኖች ምን ማለት ናቸው? እየፈጸማቸው ያለውስ እንዴት ነው? (እንዲሁም ኦሪት ዘጸአት 13፥21–22ይመልከቱ።)

ኢሳይያስ 7፥149፥1–7ከቤተክርስቲያን መጽሄቶች ስዕሎችን ወይም ፎቶዎችን በመጠቀም ስለኢየሱስ ክርስቶስ ከእነዚህ ጥቅሶች የምንማረውን ነገሮች ለመግለፅ ፓስተር መስራት ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “High on the Mountain Top፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 5።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ጌታን ለእርዳታ ጠይቁ። ቅዱሳን መጽሐፍትን ለመረዳት ግላዊ ራዕይ ያስፈልገናል። ጌታ እንደህ ሲል ቃል ገብቷል፣ “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል” (ማቴዎስ 7፥7)።

ምስል
የአይዳሆ ፎልስ አይዳሆ ቤተመቅደስ በአውሎ ነፋስ ውስጥ

ቤተ አምልኮ “ጥላ” እና “ከአውሎ ነፋስና ከዝናብ መሸሸጊያ” እንደሚሆን ኢሳይያስ አስተማረ (ኢሳይያስ 4፥6)።የአይዳሆ ፎልስ አይዳሆ ቤተመቅደስ

አትም