ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች፦ ነብያት እና ትንቢት


“ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች፦ ነብያት እና ትንቢት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች፦ ነብያት እና ትንቢት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)

የሀሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች

ነብያት እና ትንቢት

በብሉይ ኪዳን የተለምዶ የክርስቲያን ክፍል ውስጥ የመጨረሻው ክፍል (ከኢሳይያስ እስከ ሚልክያ) “ነብያቶች” ተብሎ ይጠራል።1 የብሉይ ኪዳን አንድ አራተኛ የሆነው ይህ ክፍል ስልጣን ያላቸውን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቃላት ይዟል፣ እነርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ ከዚያም ስለ እርሱ ተናገሩ፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ900 እና 500 ዓመታት መካከል የእርሱን መልዕክት ለህዝቦች አካፈሉ።2

ነብያት እና ትንቢት በመላ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ታላቅ ሚናን ይጫወታሉ። ፓትርያርኮቹ አብርሐም፣ ይስሃቅ እና ያዕቆብ ራዕዮችን ተመለከቱ እንዲሁም ከሰማይ መልዕክተኞች ጋር ተነጋገሩ። ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ እንዲሁም ለእስራኤል ልጆች ያለውን የእርሱን ፍቃድ አስታወቀ። የቀዳማዊ እና የካልዕ ነገሥት መጽሐፎች የነብያት ኤልያስን እና የኤልሳዕን የሚታወሱ ስራዎች እና መልዕክቶች ይዘግባሉ። ብሉይ ኪዳን እንደማሪያም ( ኦሪት ዘጸአት 15፥20ይመልከቱ) እና ዲቦራ ( መሣፍንት4ይመልከቱ) ዓይነት የሴት ነብያት፣ በትንቢት መንፈስ የተባረኩ እንደ ርብቃ ( ኦሪት ዘፍጥረት 25፥21–23ይመልከቱ) እና ሃና ( 1ኛ ሳሙኤል 1፥20–2፥10ይመልከቱ) ስለመሳሰሉት ሌሎች ሴቶች ጨምሮ ይናገራል። ምንም እንኳን መዝሙረ ዳዊት በመደበኛ ነብይ ባይፃፍም በተለይ የመሲሁን መምጣት ስለሚጠብቅ በትንቢት መንፈስ የተሞላ ነው።

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን እነዚህ አዲስ አይደሉም። በእርግጥ፣ ነብያት የታሪክ አስገራሚ ትንሽ ክፍል ብቻ ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ዕቅድ አሰፈላጊ አካል እንደሆኑ የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያስተምረናል። የተወሰኑ ሰዎች ነብያትን ለብሉይ ኪዳን ዘመን የተለዩ አድርገው ሊመለከቱ ቢችሉም እኛ ከብሉይ ኪዳን ጊዜዎች ጋር በጋራ እንዳለን ነገር አድርገን እናያቸዋለን።

ከኢሳይያስ ወይም ከሕዝቅኤል አንድን ምዕራፍ ማንበብ ከወቅታዊው የቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክትን ከማንበብ የተለየ መስሎ ሊሰማ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ የጥንት ነብያት ለእኛ የሚናገሩት ነገር አለ ብለን ለማየት ከባድ ሊሆን ይችላል። ደግሞም፣ ዛሬ የምንኖርበት ዓለም እነርሱ ከሰበኩበት እና ከተነበዩበት ጋር በጣም የተለየ ነው። በሕይወት ያለ ነብይ በእርግጥ ስላለን ጥያቄን ያስነሳል፦ ጥረቱ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው—እንዲሁም የጥንት ነብያትን ቃላት ለማንበብ ጥረት የሚፈልገው ለምንድን ነው?

ለእኛ የሆነ የሚናገሩት ነገር አላቸው

በአብዛኛው ክፍል፣ ዛሬ ሰዎች የብሉይ ኪዳን ነብያት ዋነኛ ታዳሚዎች አይደሉም። እነዚያ ነብያት በሰዓታቸው እና በቦታቸው ወቅታዊ ችግሮችን እየገለፁ ነበር—ልክ እንደኋለኛው ቀን ነብያት ወቅታዊ ችግሮቻችንን ዛሬ እንደሚገልፁት።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ነብያት ከወቅታዊ ችግሮች ባሻገር ሊመለከቱ ይችላሉ። ለማንኛውም እድሜ ተገቢ የሆነውን የዘላለም እውነቶች ያስተምራሉ። እናም፣ በራዕይ በመባረክ ትልቁን ምስል፣ የእግዚአብሔርን ስራ ሰፊ እይታ ይመለከታሉ። ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ በእሱ ቀን ላሉት ሰዎች ብቻ አይደለም ስለሃጢያታቸው ያስጠነቀቀው—ከ200 ዓመታት በኋላ ወደፊት ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ነፃ መውጣት እና ጎን ለጎንም ሁሉም የእግዚአብሔር ህዝቦች የሚሹትን ነፃ መውጣት ሊያስተምር ሊፅፍም ይችላል። በተጨማሪም፣ ዛሬ እራሱ ሙሉ በሙሉ መከናወናቸውን እየጠበቁ ያሉ—እንደ የ“አዲስ ምድር” ቃልኪዳን (ኢሳይያስ 65፥17) “እግዚአብሔርን በማወቅ የተሞላች” ስለሆነች (ኢሳይያስ 11፥9) የጠፉት የእስራኤል ነገዶች ተሰብስበው እና “ሕዝብ” “ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ [እንደማይኖር]” ትንቢቶችን ሊፅፍ ይችላል (ኢሳይያስ 2፥4)። ልክ እንደኢሳይያስ ዓይነት የብሉይ ኪዳን ነብያቶችን ቃላት በማንበብ የሚመጣ ደስታ እና መነሳሳት አንዱ አካል እኛ እነሱ በተመለከቱት ክብራዊ ቀን ውስጥ ሚና እንደተጫወትን መገንዘብ ነው።3

የጥንት ትንቢቶችን ሲያነቡ ስለተፃፉበት ሁኔታ መማር ይጠቅማል። ነገር ግን እራሶን በእነሱ ውስጥ መመልከት ወይም ኔፊ እንዳስቀመጠው “[ከእርሶ] ጋር [ማመሳሰል]” ይችላሉ ( 1ኛ ኔፊ 19፥23–24ይመልከቱ)። አንዳንድ ጊዜ ባቢሎንን እንደ ጥንት ከተማ ብቻ ሳይሆን አንደ ዓለማዊነት እና የኩራት ምልክት አድርጎ መገንዘብ ማለት ነው። ለእየሩሰሳሌም ልክ እንደ ተለወዋጭ ቃል አድርጎ ከመውሰድ ይልቅ በማንኛውም ዘመን ውስጥ እስራኤልን እንደ የእግዚአብሔር ህዝብ መረዳት እና ጽዮንን እንደ የኋለኛው ቀን የእግዚአብሔር ህዝብ የመቀበል ምክንያት ማለት ሊሆን ይችላል።

ቅዱሳን መጽሐፍትን ማመሳሰል እንችላለን ምክንያቱም አንድ ትንቢት በብዙ መንገዶች እንደሚከናወን ስለምናውቅ።4 የዚህ ጥሩ ምሳሌ በ ኢሳይያስ 40፥3ውስጥ ያለው ትንቢት ነው፦ “የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፣ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካከሉ።” በባቢሎን ውስጥ በምርኮ ለተያዙት አይሁዶች ይህ መግለጫ እግዚአብሔር ከምርኮ የሚወጡበትን እና ወደ ኢየሩሳሌም የሚመለሱበትን መንገድ እየሰጠ እንዳለ ሊገልፅ ይችላል። ለማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ እና ሉቃስ ይህ ትንቢት የአዳኙን ምድራዊ አግልግሎት መንገድ ባዘጋጀው በመጥምቁ ዮሐንስ ውስጥ ተከናውኗል።5 እና ጆሴፍ ስሚዝ ይህ ትንቢት በኋለኞቹ ቀናት ለክርስቶስ የሺህ ዓመታት አገልግሎት ዝግጅት አሁንም እየተከናወነ እንደሆነ መገለጥን ተቀበለ።6 በተወሰነ መልኩ የጥንት ነብያት ለእኛ በእርግጥ እንደተናገሩ ለመረዳት አሁንም እየቀረብን ነው። ለጥንት እስራኤል የሚዛመዱ እንደሆኑ ሁሉ ለእኛም የሚዛመዱ ብዙ ውድ፣ ዘላለማዊ እውነቶችን አስተማሩ።

የጥንት ነቢይ ጽሁፍ

የጊዜዎች ሙላት፣ በግሬግኬ. ኦልሰን

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከሩ

ምናልባት እራሶን በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ውስጥ ከማየት የበለጠ ጠቃሚ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በእነሱ ውስጥ ማየት ነው። እርሱን ከፈለጉ ያገኙታል፣ ምንም እንኳን በስም ባይጠራም። የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር፣ ጌታ ይሆዋ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ማስታወስ ሊረዳ ይችላል። በማንኛውም ጊዜ ነብያቶች እግዚአብሔር እያደረገ ስላለው ነገር ወይም ስለሚያደርገው ነገር ሲገልፁ ስለአዳኙ እየተናገሩ ነው።

እንዲሁም ስለተቀባው ( ኢሳይያስ 61፥1ይመልከቱ)፣ ቤዛ ( ሆሴዕ 13፥14ይመልከቱ) እና ከዳዊት ዘር ስለሚመጣው የወደፊት ንጉሥ መግለጫን ያገኛሉ ( ኢሳይያስ 9፥6–7ዘካርያስ 9፥9ይመልከቱ)። እነዚህ በሙሉ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገሩ ትንቢቶች ናቸው። በአጠቃላይ ነፃ ስለመውጣት፣ ይቅርታ፣ ቤዛነት እና መመለስ ያነባሉ። አዳኙ በአዕምሮዎ እና በልቦ ውስጥ ሲኖር እነዚህ ትንቢቶች እንደሚጠበቀው ወደ እግዚአብሔር ልጅ ይጠቁሞታል። ትንቢትን የመረዳት ምርጡ መንገድ “የትንቢት መንፈስ” ማግኘት ነው እሱም “የኢየሱስ ምስክር” እነደሆነ ዮሐንስ ነግሮናል (ራዕይ 19፥10)።

ማስታወሻዎች

  1. ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ እና ሕዝቅኤል በመጽሐፋቸው ርዝመት ምክንያት ብዙውን ጊዜ ዋና ነብያቶች ተብለው ይጠራሉ። ሌሎቹ ነብያት (ሆሴዕ፣ ኢዮኤል፣ አሞጽ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ሚክያስ፣ ናሆን፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ እና ሚልክያ) መጽሐፋቸው የበለጠ አጭር በመሆናቸው ምክንያት ታናሽ ነብያት ተብለው ይጠራሉ። የሰቆቃው ኤርምያስ መጽሐፍ የነብያት ሳይሆን የጽሑፎች አካል ተደርጎ ነው የሚቆጠረው።

  2. የትንቢት መጽሐፎች እንዴት እንደተሰበሰቡ አናውቅም። በተወሰኑ ሁኔታዎች አንድ ነብይ የጽሑፎቹን እና ትንቢቶቹን ስብሰብ ተቆጣጥሮ ሊሆን ይችላል። በሌላ ሁኔታዎች፣ ከእርሱ ሞት በኋላ ተመዝግበው እና ተሰብስበው ይሆናል።

  3. “የዚህን ደስታ እና አስቸኳይነት አስቡ፦ እያንዳንዱ ነብይ ከአዳም ጀምሮ የእኛን ቀን አይተዋል። እናም እያንዳንዱ ነብይ ስለ እኛ ቀን፣ ማለትም እስራኤል ስለምትሰበሰብበት እና ዓለም ለሁለተኛው ምፅአት ስለሚዘጋጅበት ቀን ተናግረዋል። አስቡበት! በፕላኔት መሬት ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ እኛ ነን በዚህ በመጨረሻ፣ በታላቁ የመሰብሰብ ክስተት ውስጥ መሳተፍ የምንችለው። ያ ምንኛ አስደሳች ነው!” (ረስልኤም. ኔልሰን፣ “Hope of Israel” [የዓለም አቀፍ የወጣቶች አምልኮ፣ ሰኔ3፣ 2018 (እ.አ.አ)], ተጨማሪ ኒው ኢራ እና ኢንሳይን፣8፣ ChurchofJesusChrist.org)። እንዲሁም የሮናልድኤ ራስባንድን፣ “Fulfillment of Prophecy፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 75–78 ይመልከቱ።

  4. አዳኙ ስለኢሳይያስ ሲናገር እንዲህ አለ፣ “የተናገራቸው እንዲሁም በተናገራቸው ቃላት መሰረት ሁሉም ነገሮች ሆነዋልም [እንዲሁም] ይሆናሉም ” (3ኛ ኔፊ 23፥3፤ ሰያፍ ቅርጸት ተጨምሮበታል)።

  5. ማቴዎስ 3፥1–3ማርቆስ 1፥2–4ሉቃስ 3፥2–6ን ይመልከቱ።

  6. ትምህርት እና ቅል ኪዳኖች 33፥1065፥388፥66ን ይመልከቱ።