ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መስከረም 26–ጥቅምት2 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 50–57፦ “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል”


“መስከረም 26–ጥቅምት2 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 50–57፦ ‘በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፣‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 26–ጥቅምት2 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 50–57፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስቶስ የእሾህ አክሊል አድርጎ በወታደር ሲፌዝበት

በክርስቶስ ላይ ማፌዝ፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች

መስከረም 26–ጥቅምት2 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ 50–57

“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል”

ኢሳይያስ 50–57 ውስጥ ወደ አዳኙ ለመቅረብ የረዳዎትን ግንዛቤዎች ያሰላስሉ። የሚቀበሉትን ስሜቶች ይመዝግቡ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በመላ አገልግሎቱ ውስጥ ኢሳይያስ ስለሃያል አዳኝ ተናግሯል (ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 9፥3–7ይመልከቱ)። እነዚህ ትንቢቶች እስራኤላውያን ከክፍለ ዘመናት በኋላ በባቢሎን ምርኮ ውስጥ በሚሆኑ ጊዜ በተለየ ውድ ይሆኑ ነበር። የባቢሎንን ግንቦች ሊያያፈርስ የሚችል ሰው በእርግጥ ሃያል ድል አድራጊ ነው። ነገር ግን ያ ኢሳይያስ በ ምዕራፎች 52–53፣ ውስጥ የጠቀሰው መሲህ ዓይነት አይደለም፦ “የተናቀ ከሰውም የተጠላ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው።… እኛ ግን እንደተመታ በእግዚአብሔርም እንደተቀሰፈ እንደተቸገረም ቆጠርነው” (ኢሳይያስ 53፥3–4)። እንደዚህ ዓይነት ያልተጠበቀ አዳኝ በመላክ እግዚአብሔር ስለትክክለኛ ነፃ መውጣት አስተማረን። ከጭቆና እና ከመከራ ሊያድነን እግዚአብሔር “የተጨቆነን እና የተሰቃየን” ላከ። አንበሳ በሚጠበቅበት ቦታ ጠቦትን ላከ ( ኢሳይያስ 53፥7ይመልከቱ)። በእርግጥ የእግዚአብሔር መንገዶች የእኛ መንገዶች አይደሉም ( ኢሳይያስ 55፥8–9ይመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ ነፃ ያወጣን እስር ቤቱን በመክፈት ሳይሆን በዚያ ውስጥ የእኛን ቦታ በመውሰድ ነው። እርሱ እራሱ በመሸከም ከሃዘናችን እና ከመከራችን ሰንሰለቶች ለእኛ እረፍት ይሰጠናል ( ኢሳይያስ 53፥4–5፣12ይመልከቱ)። የሚያድነን በርቀት ሆኖ አይደለም። “ዘላለማዊ ቸርነት” በማሳየት ተግባሩ “ከአንቺ ዘንድ [ሳይፈልስ]” ከእኛ ጋር አብሮ ይሰቃያል (ኢሳይያስ 54፥8፣10)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 50–52

ለጌታ ህዝቦች የወደፊቱ ብሩህ ነው።

እስራኤላውያን በምርኮ ውስጥ ብዙ ዓመታትን ቢያሳልፉም—ምንም እንኳን ያ ምርኮ የተሳሳቱ ምርጫዎቻቸው ውጤት ቢሆንም—ጌታ የወደፊታቸውን በተስፋ እንዲመለከቱ ፈለገ። በ ኢሳይያስ 50–52፣ ውስጥ ምን ተስፋ የተሞላባቸው መልዕክቶችን ያገኛሉ? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታ ስለእራሱ ምን ያስተምረናል፣ ይህስ ተስፋን የሚሰጥዎ ለምንድን ነው? ( ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 50፥2፣ 5–951፥3–8፣ 15–1652፥3፣ 9–10ይመልከቱ)።

ምዕራፎች 51–52 ውስጥ ጌታ ይህን ተስፋ ወደፊት እውን ለማድረግ እስራኤላውያን እንዲተገብሩ የጋበዛቸውን ነገሮች መዘርዘር ይችላሉ። በእነዚህ ቃላት አማካኝነት ጌታ ምን እንዲያደርጉ የሚጋብዞት ይመስሎታል? ለምሳሌ “ተነሺ” እና “ኃይልሽን ልበሺ” ማለት ምን ማለት ይመስሎታል? (ኢሳይያስ 51፥9፤ እንዲሁም ኢሳይያስ 52፥1ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113፥7–10ይመልከቱ)። “አድምጡ” (ወይም “ለመታዘዝ አድምጡ”) የሚለው ግብዣ ለምን ብዙ ጊዜ የተደጋገመ ይመስሎታል? (ረስልኤም. ኔልሰን፣ “Hear Him፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣89)።

እንዲሁም ሞዛያ 12፥20–2415፥13–183ኛ ኔፊ 20፥29–46ይመልከቱ።

ምስል
ክርሰቶስ መስቀል ተሸክሞ የሚያሳይ ቅርጽ

በፍቅር ምክንያት፣ በቀራጺ አንጄላ ጆንሰን

ኢሳይያስ53

ኢየሱስ ክርስቶስ የእኔን ሃጢያት እና ሃዘኖች በራሱ ላይ ወሰደ።

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ምዕራፎች የኢየሱስ ክርስቶስን የቤዛነት ተልዕኮ ከ ኢሳይያስ53፣ በበለጠ ቆንጆ አድርገው ይገልፃሉ። በእነዚህ ቃላቶች ላይ ለማሰላሰል ጊዜ ይመድቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ ሲያነቡ አዳኙ—የተሸከማቸውን “ህመሞች፣” “ሃዘኖች” እና “መተላለፎች”—ለሁሉም ሰው በለተይም ለእርሶ የተሰቃየውን ነገሮች ቆም ብለው ያሰላሰሉ ። እንደ “እኛ” እና “የእኛ” የሚሉትን ቃላት “እኔ” እና “የእኔ” በሚሉ ቃላት መተካት ይችላሉ። እነዚህ ጥቅሶች ምን ዓይነት ስሜቶችን ወይም ሃሳቦችን በውስጦ ያስነሳሉ? እነሱን መፃፍን ያስቡ።

ነብዩ አቢናዲ ስለ አዳኙ ለማስተማር የኢሳይያስን ቃላት እንዴት እንደተጠቀመ ለማየት ሞዛያ1415፥1–13 ን መከለስ ይፈልጉ ይሆናል።

ኢሳይያስ5457፥15–19

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንድመለስ ይፈልጋል።

በሃጢያቶቻችን ወይም በክፋቶቻችን ምክንያት ሁላችንም ከጌታ የራቅን መስሎ የሚሰማን ጊዜ አለ። አንዳንዶች ይቅር አይለንም ብለው ተስፋን ቆርጠዋል። በዚህ ዓይነት ጊዜ ውስጥኢሳይያስ54 እና57 ማረጋገጫ እና ማበረታቻ ለማግኘት የሚነበቡ ታላቅ ምዕራፎች ናቸው። በተለይ በ ኢሳይያስ 54፥4–1057፥15–19፣ ወስጥ ስለአዳኙ ምህረት እና ለእርሶ ስላለው ስሜት ምን ይማራሉ? ስለእርሱ እነዚህን ነገሮች ማወቅ በሕይወቶ ውስጥ ምን ልዩነት ያመጣል?

ኢሳይያስ 54፥11–17 ውስጥ የተጠቀሱት በረከቶች ለእርሶ እንዴት ተግባራዊ ይሆናሉ?

ኢሳይያስ 55–56

እግዚአብሔር ለሁሉም “ቃልኪዳ[ኑ]ን [እንዲ]ይዙ” ይጋብዛል።

ለብዙ ትውልዶች እስራኤል እንደእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝብ ተደርጋ ተቆጠረች። ይሁን እንጂ፣ የእግዚአብሔር እቅድ ሁሌም ከአንድ አገር የበለጠን ያካትታል፣ ምክንያቱም “የተጠ[ሙት] ሁሉ” “ወደ ውኃ [እንዲመጡ]” ተጋብዘዋል (ኢሳይያስ 55፥1)። ኢሳይያስ55 እና56ን ሲያነቡ ይህን በአዕምሮዎ ውስጥ ያስቀምጡ እናም የእግዚአብሔር ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያሰላስሉ። ከእርሱ “[የተለዩ]” ሆነው ለሚሰማቸው ሰዎች የእግዚአብሔር መልዕክት ምንድን ነው? (ኢሳይያስ 56፥3)። “ቃል ኪዳኔን የሚይዙ” ስለተባሉ ሰዎች ያሉትን ዝንባሌዎች እና ተግባሮች በሚገልፁ ጥቅሶች ላይ ምልክት ማድረግን ያስቡ ( ኢሳይያስ 56፥4–7ይመልከቱ)።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 51–52በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ስላሉ የአዳኙ ግብዣዎች ሲወያዩ የቤተሰብ አባላት እንዲተውኗቸው መጋበዝ ይችላሉ። ለምሳሌ “ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሱ፣” “ን[ቁ]፣ ቁ[ሙ]፣” ወይም “ትቢያን አራግ[ፉ]” ማለት ምን ይመስላል? (ኢሳይያስ 51፥6፥1752፥2)። እነዚህ ሃረጎች ኢየሱስ ክርስቶስን ስለመከተል ምን ያስተምሩናል?

ኢሳይያስ 52፥9ይህን ጥቅስ ካነበቡ በኋላ ቤተሰቦ ደስታን የሚያመጣላቸውን መዝሙር ወይም የልጆች መዝሙር “በጋራ መዘመር” ይችላሉ። በ ኢሳይያስ52 ውስጥ ምን ተስፋዎች “ደስ [እንዲለን]” ያደርጉናል”?

ኢሳይያስ 52፥1155፥7እነዚህ ጥቅሶች “ንጽሐን ሁኑ” የሚለው ሃረግ ምን ማለት ነው ወደሚል ውይይት ሊያመሩ ይችላሉ። ልክ እንደዚህ ውይይት አንድ አካል በ For the Strength of Youth [በራሪ ጽሑፍ 2011 (እ.አ.አ)] ውስጥ ርዕሶችን መከለስ ወይም በመንፈስ ንፁህ ስለመሆን በረከቶች ቅዱሳን መጽሐፍን ማንበብ ይችላሉ ( 3ኛ ኔፊ 12፥8ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥45–46ይመልከቱ)።

ኢሳይያስ53ኢሳይያስ የሰጠውን የአዳኙን መግለጫዎች ለማስተዋወቅ ቤተሰቦ ታሪኮች፣ ፊልሞች እና ሌሎች ሚዲያዎች ሰዎችን የሚያድኑ ጀግኖችን እንዴት እንደሚገልፁ መነጋገር ይችላሉ። አነዚያን መግለጫዎች በ ኢሳይያስ53፣ ወስጥ ካነበቡት የአዳኙ መግለጫዎች ጋር ማነፃፀር ይችላሉ። “My Kingdom Is Not of This World” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ መመልከት እና በ ኢሳይያስ53 ውስጥ ያሉ ትንቢቶች እንዴት እንደተከናወኑ መነጋገር ይችላሉ። አዳኙ ስለእኛ የተሸከማቸው አንዳንድ ህመሞች እና ሃዘኖች ምንድን ናቸው?

ኢሳይያስ 55፥8–9እርስዎ ከመሬት ከፍታ ላይ ሲሆኑ ነገሮች እንዴት የተለዩ መስለው ይታያሉ? የእግዚአብሔር መንገዶች እና ሃሳቦች ከእኛ የላቁ ናቸው ማለት ለእርሶ ምን ማለት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “እኔ በመደነቅ ቆሜያለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 193።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ሙዚቃን ተጠቀሙ። መዝሙሮች የወንጌልን መርሆዎች በኃይል ያስተምራሉ። በ ኢሳይያስ53፣ ውስጥ ስለተሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ እውነቶች ትምህርት ለመረዳት የቅዱስ ቁርባን መዝሙሮችን ማዳመጥን ወይም ማንበብን ያስቡ። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 22ን ይመልከቱ።)

ምስል
የክርሰቶስ የቁም ስዕል

የእርሱ ብርሃን፣ በማይክልቲ. ማልም

አትም