ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 17–23። ኤርምያስ 30–33፤ 36፤ ሰቆቃው ኤርምያስ 1፤ 3፦ “ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ”


“ጥቅምት 17–23 (እ.አ.አ)። ኤርምያስ 30–33፤ 36፤ ሰቆቃው ኤርምያስ 1፤ 3፦ ‘ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 17–23 (እ.አ.አ)። ኤርምያስ 30–33፤ 36፤ ሰቆቃው ኤርምያስ 1፤ 3፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

የነብዩ ኤርምያስ የድንጋይ ላይ ቅርፅ

የነብዩ ኤርምያስ ለቅሶ፣ ቅርፅ በናዛሪን ትምህርት ቤት

ጥቅምት 17–23 (እ.አ.አ)

ኤርምያስ 30–3336ሰቆቃው ኤርምያስ13

“ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ”

ግንዛቤዎን ሲመዘግቡ በኤርምያስ እና በሰቆቃው ኤርምያስ ውስጥ ያሉ መርሆዎች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተማሩት ሌሎች ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ያስቡ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

እግዚአብሔር መጀመሪያ ኤርምያስን ነብይ እንዲሆን ሲጠራው የእሱ ተልዕኮ “[መንቀል] እና [ማፍረስ]” እንደሆነ ነገረው (ኤርምያስ 1፥10)—እናም በኢየሩሳሌም ውስጥ ብዙ የሚነቀሉ እና የሚፈርሱ ክፉዎች ነበሩ። ነገር ግን ያ የኤርምያስ ተልዕኮ አንዱ ክፍል ብቻ ነበር—እንዲሁም “[ሊ]ሰራ እና [ሊ]ተክል” ተጠርቶም ነበር (ኤርምያስ 1፥10)። በእስራኤል አመጽ ፈራርሶ በቀረው ውስጥ ሊሰራ እና ሊተከል የሚችል ምን አለ? በተመሳሳይ መልኩ ሃጢያት ወይም መከራ ሕይወቶቻችንን ሲያፈራርስ እንዴት መልሰን መስራት እና መትከል እንችላለን? መልሱ ያለው “የጽድቅ ቁጥቋጥ” (ኤርምያስ 33፥15)፣ በሆነው ቃል በተገባው መሲህ ላይ ነው። መሲሁ “አዲስ ቃልኪዳን” ያመጣል (ኤርምያስ 31፥31)—ያም ስር ካልሰደደ ቁርጠኝነት ወይንም ከላይ ላይ አምልኮ የበለጠ ይጠይቃል። የእርሱ ህግ “በውስጣችን” “በልቦቻችን” የተፃፈ መሆን አለበት። ያ ነው በትክክል እግዚአብሔር “[የእኛ] አምላክ” እና እኛ ደግሞ “[የእርሱ] ህዝብ ነን” ማለት (ኤርምያስ 31፥33)። የእድሜ ልክ ሂደት ነው፣ እንዲሁም ስህተቶችን እንሰራለን እናም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያስለቅስ ምክንያት ይገጥመናል። ነገር ግን ያን ስናደርግ፣ ከእግዚአብሔር ይህ ቃልኪዳን ይኖረናል፦ “ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ” (ኤርምያስ 31፥13)።

ስለሰቆቃው ኤርምያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት “መጽሐፈ ሰቆቃው ኤርምያስ” የሚለውን በቅዱሳን መጽሐፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኤርምያስ 30–3133

ጌታ እስራኤልን ከምርኮ ያወጣቸዋል እና ይሰበስባቸዋል።

ኤርምያስ 30–3133 ውስጥ እስራኤላውያን ወደ ምርኮ ውስጥ ሲገቡ ስለሚያጋጠማቸው “ዋይታ እና የመራራ ለቅሶ” ጌታ እውቅና ሰጠ (ኤርምያስ 31፥15)። ይሁን እንጂ፣ የመፅናናት እና የተስፋ ቃላትንም ሰጣቸው። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ምን ሃረጎች ለእስራኤሎች መፅናናትን እና ተስፋን ሰጥቷቸዋል ብለው ያስባሉ? ከእግዚአብሔር ለህዝቦቹ የተሰጡ ምን ቃልኪኖችን ያገኛሉ? እነዚህ ቃልኪዳኖች ለእርሶ ዛሬ እንዴት ተግባራዊ ሊሆኑ ይችላሉ?

ኤርምያስ 31፥31–3432፥37–42

“እነሱም ህዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።”

እስራኤላውያን ከጌታ ጋር የነበራቸውን ቃልኪዳን ቢያፈርሱም እንኳን፣ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር በድጋሚ “አዲስ” እና “የዘላለም ቃልኪዳን” እንደሚመሰርት ኤርምያስ ተነበየ (ኤርምያስ 31፥3132፥40)። አዲሱ እና የዘላላም ቃልኪዳኑ “የኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ሙላት ነው [ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66፥2ይመልከቱ]። የክህደትን ጊዜ ተከትሎ በሚገለፅበት በእያንዳንዱ ሰዓት አዲስ ነው። የእግዚአብሔር ቃልኪዳን በመሆኑ እና ሰዎች ለመቀበል ፍቃደኞች በሆኑበት በእያንዳንዱ የወንጌል ዘመን ስለተደሰቱበት የዘላለም ነው“አዲሱ እና የዘላለም ቃልኪዳን፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ሰያፍ ቅርጸት ተጨምሮበታል)።

ኤርምያስ 31፥31–3432፥37–42ን ሲያነቡ የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝብ አካል መሆን ማለት ለእርሶ ምን ማለት እንደሆነ ያሰላስሉ። እነዚህ ጥቅሶች ከእግዚአብሔር ጋር ያሎትን የቃልኪዳን ግንኙነት በሚመለከቱበት መንገድ ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራሉ? የእርሱን ህግ በልቦ ውስጥ መፃፍ ማለት ምን ማለት ነው? ( ኤርምያስ 31፥33ይመልከቱ)።

እንዲሁም ኤርምያስ 24፥7ዕብራውያን 8፥6–12ን ይመልከቱ።

ሴት ልጅ ቅዱሳን መጽሐፍትን እያጠናች

ቅዱሳን መጽሐፍት ንስሃ እንድንገባ እና ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ሊያነሳሱን ይችላሉ።

ኤርምያስ36

ቅዱሳን መጽሐፍት እኔን ከክፉ ለማሸሽ ኃይል አላቸው።

እግዚአብሔር ኤርምያስን ህዝቡ እነዚህን ትንቢቶች የሚሰሙ ከሆነ “ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ዘንድ እኔም ሃጢያታቸውን ይቅር እል ዘንድ” የሚሉትን ትንቢቶቹን “በመጽሐፍ ክርታስ” ውስጥ ወይም ብራና ላይ እንዲመዘግብ አዘዘው (ኤርምያስ 36፥2–3)። ኤርምያስ36ን ሲያነቡ የሚከተሉት ሰዎች ስለእነዚህ ትንቢቶች እንዴት እንደተሰማቸው መመዝገብን ያስቡ፦

ጌታ፦

ኤርምያስ፦

ባሮክ፦

ይሁዲ እና ንጉሥ ኢዮአቄም፦

ኤልናታን፣ ድላያ እና ገማርያ፦

ስለቅዱሳን መጽሐፍት እና በሕይወቶ ውስጥ ስላላቸው ሚና እንዴት እንደሚሰማዎት ያሰላስሉ። ከክፉ እንዲሸሹ እንዴት ረድቶዎት ያውቃሉ?

እንዲሁም የጁሊቢ. ቤክ፣ “My Soul Delighteth in the Scriptures፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2004 (እ.አ.አ)፣ 107–9 ይመልከቱ።

ሰቆቃው ኤርምያስ13

በሃጢያት ምክንያት የሚያጋጥመንን ሃዘን ጌታ ማቅለል ይችላል።

የሰቆቃው ኤርምያስ መጽሐፍ ከኢየሩሳሌም እና ከቤተመቅደሷ ውድመት በኋላ የተፃፉ ግጥሞች ስብስብ ነው። አነዚህ ሙሾዎች መጠበቃቸው እና በብሉይ ኪዳን ውስጥ መካተታቸው ለምን የሚጠቅም ይመስሎታል? በ ሰቆቃው ኤርምያስ1 እና3 ውስጥ የትኛው ምሳሌያዊ አነጋገር እስራኤላውያን የተሰማቸውን ታላቅ ሃዘን ለመገንዘብ እንደረዳዎት ያስቡ። ምን የክርስቶስ የተስፋ መልዕክቶችን አገኙ? (በተለይ ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥20–33፤ እንዲሁም ማቴዎስ 5፥4ያዕቆብ 4፥8–10አልማ 36፥17–20ይመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኤርምያስ 31፥3የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያላቸውን “የዘላለም ፍቅር” ያሳዩት እንዴት ነው? ክርስቶስ ለእኛ የፈጠራቸውን ነገሮች ወይም በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ያደረጋቸውን ነገሮች ፎቶዎች ማሳየት ቤተሰቦ የእርሱ “የፍቅር ቸርነት” እንዲሰማቸው ሊረዳ ይችላል።

ኤርምያስ 31፥31–3432፥38–41በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃልኪዳኖችን ስንገባ እርሱ የሰጠንን ተስፋዎች ዝርዝር መፃፍን ያስቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለቃለኪዳኖቻችን ጠቀሜታ ምን ያስተምሩናል?

የቤተሰብ አባላት በወረቀት የልብ ቅርፅ ላይ ስለአዳኙ እንዴት እንደሚሰማቸው የሚያሳይን ነገር ሊፅፉ (ወይም ሊስሉ) ይችላሉ። የእርሱን ህግ በልቦቻችን ውስጥ መፃፍ ማለት ምን ማለት ነው? ( ኤርምያስ 31፥33ይመልከቱ)። የእርሱ ህዝብ መሆን እንደምንፈልግ ለእግዚአብሔር የምናሳየው እንዴት ነው?

ኤርምያስ36ሰለቅዱሳን መጽሐፍት ጠቀሜታ እንዲማሩ ቤተሰቦን ለመርዳት ኤርምያስ36 እንዴት መጠቀም ይችላሉ? ( ለምሳሌ፣ ቁጥሮች 1–6፣ 10፣ 23–24፣ 27–28፣32ይመልከቱ)። አንድ የቤተሰብ አባል ከዚህ ምዕራፍ ውስጥ አንድን ጥቅስ እንዲያነቡ ሌላኛው የቤተሰብ አባል ደግሞ እንዲፅፉት መጠየቅ ይችላሉ፣ ልክ ባሮክ ለኤርምያስ እንዳደረገው። ልክ የነብያትን ቃላት እንደጠበቀው እንደ ባሮክ ዓይነት ሰዎች ላደረጉት ጥረቶች አመስጋኞች የሆንነው ለምንድን ነው? ቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ያሉትን የእግዚአብሔር ቃላት ዋጋ እንደምንሰጥ ለእርሱ ለማሳየት ምን ማድረግ እንችላለን?

ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥1–17፣ 21–25፣ 31–32ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥1–17 ውስጥ የተገለፁት ስሜቶች ሃጢያት ስንሰራ ከሚሰሙን ስሜቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እንደቤተሰብ መነጋገር ይችላሉ። በ ቁጥሮች 21–25፣ 31–32 ውስጥ ያሉት መልዕክቶች በሕይወታችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “I Feel My Savior’s Love፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 74–75።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ራዕይን ይፈልጉ። በቀን ውስጥ ሲያሰላስሉ፣ ስላጠኑት መጽሐፍ ቅዱሳት ተጨማሪ ሃሳቦችን እና ግንዛቤዎችን ሊቀበሉ ይችላሉ። የወንጌል ጥናት ጊዜ የሚመድቡለት ነገር ሳይሆን ሁሌም የሚያደርጉት ነገር እንደሆነ አድርገው ያስቡት። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 12ን ይመልከቱ።)

ከተማ በውጪ ሲቃጠል አንድ ሰው በዋሻ ውስጥ አዝኖ ሲታይ።

ኤርሚያስ ስለኢየሩሳሌም መጥፋት እያለቀሰ፣ በሬምብራንድት ቫን ሪጅን