ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 3–9 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 58–66፦ “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል”


“ጥቅምት 3–9 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 58–66፦ ‘ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 3–9 (እ.አ.አ)። ኢሳይያስ 58–66፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ በምኩራብ ውስጥ ሲያስተምር

ኢየሱስ በናዝሬት በምኩራብ ውስጥ፣ በግሬግኬ. ኦልሰን

ጥቅምት 3–9 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ 58–66

“ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል”

ኢሳይያስ 58–66ን ሲያጠኑ የኢሳይያስ ቃላት ለወደፊት እንዴት ለእርሶ ደስታን እና ተስፋን እንደሚያመጡ ያስቡ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በምድራዊ አገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ባደገበት መንደር በናዝሬት ውስጥ አንድ ምኩራብን ጎበኘ። እዚያም ከቅዱሳን መጽሐፍት ለማንበብ ቆመ፣ የኢሳይያስን መጽሐፍ ከፈተ እና አሁን ኢሳይያስ 61፥1–2፣ ብለን የምናውቀውን አነበበ። ከዚያም እንዲህ አስታወቀ፣ “ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ።” ይህ የአዳኙ ቀጥተኛ የሆነ የተቀባው እርሱ እንደሆነ፣ “ልበሰባራዎችን የሚፈውስ” እና “ለታሰሩትም መፈታትን የሚሰብክ” እንደሆነ የገለፀበት አንዱ መንገድ ነው ( ሉቃስ 4፥16–21ይመልከቱ)። ይህ ቅዱስ ጽሁፍ በእርግጥ በዚያን ቀን ተፈጸመ። እናም ልክ እንደሌሎች ብዙ የኢሳይያስ ትንቢቶች፣ በዘመናችን ውስጥ መከናወኑን ቀጠለ። አዳኙ ወደ እርሱ የሚመጡትን ልባቸው የተሰበረውን ሁሉ መፈወሱን ቀጠለ። ነፃ መውጣት ሊሰበክላቸው የሚገባ ብዙ ምርከኞች አሉ። መዘጋጀት የሚጠይቅ ታላቅ ነገር ወደፊት አለ—እሱም እግዚአብሔር “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር [የሚፈጥርበት]” (ኢሳይያስ 65፥17) እና “ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ [የሚያበቅልበት]” ጊዜ ነው (ኢሳይያስ 61፥11)። ኢሳይያስን ማንበብ እግዚአብሔር ላደረገው ነገር፣ እያደረገ ላለው ነገር እና ለህዝቦቹ ለሚያደርገው ነገር አይኖቻችንን ይከፍታል።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኢሳያስ 58፥3–12

ፆም በረከቶችን ያመጣል።

እነዚህ ጥቅሶች ለብዙ የጥንት እስራኤላውያን ፆም ከበረከት ይልቅ እንደሸክም እንደነበር ይጠቁማሉ። ብዙዎቻችን አንዳንድ ጊዜ ያንን ስሜት ልንጋራ እንችላለን። ስለፆሞት የበለጠ ትርጉም እና አላማ ለማግኘት ከፈለጉ “ለምን እንፆማለን” ለሚለው ጥያቄ ጌታ የሰጣቸውን መልሶች በ ኢሳይያስ 58፥3–12 ውስጥ ያንብቡ። በርሶ ተሞክሮ ፆም “የበደልን እስራት [የፈታው]” እና“ቀንበርን [የሰበረው]” እንዴት ነው? (ኢሳይያስ 58፥6)። ፆም በ ኢሳይያስ 58፥8–12፣ ውስጥ የተጠቀሱትን በረከቶች ያመጣሎት እንዴት ነው ? ኢሳይያስ 58፥3–12 ስለፆም በሚያስቡበት መንገድ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

Is Not This the Fast That I Have Chosen?” በሚለው መልዕክቱ ውስጥ (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 22–25)፣ ፕሬዚዳንት ሄነሪቢ. አይሪንግ ሰዎች በፆም እና በፆም በኩራት እንዴት እንደተባረኩ ብዙ ምሳሌዎችን አካፈሉ። በሕይወትዎ ውስጥ ተመሳሳይ በረከቶችን የተመለከቱት እንዴት ነው?

እንዲሁም የወንጌል ርዕሶች፣ “ፆም እና የፆም በኩራቶች” (topics.ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

ኢሳይያስ 59፥9–2161፥1–363፥1–9

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ እና ቤዛዬ ነው።

ኢሳይያስ 58–66 ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ተልዕኮ ብዙ ማጣቀሻዎችን ያገኛሉ። እንዲያሰላስሉባቸው ለመርዳት ጥቂት ምሳሌዎች ከተወሰኑ ጥያቄዎች ጋር አብረው እዚህ ቀርበዋል።

  • ኢሳይያስ 59፥9–21። በ ቁጥሮች 9–15፣ ውስጥ ስለተገለፁት ሰዎች መንፈሳዊ ሁኔታ እንዴት ያጠቃልሉታል? በ ቁጥሮች 16–21 ውስጥ ስለ “ማማለድ” ስለቀረበው ገለፃ እና ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሰዎች ስለገባው ቃልኪዳን ምን አስደነቆት?

  • ኢሳይያስ 61፥1–3። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በተገለፀው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ የባረኮት እንዴት ነው? እርሱ ምን “የምስራች” አመጣሎት? በአመድ ፋንታ ቁንጅናን የሰጦት እንዴት ነው?

  • ኢሳይያስ 63፥7–9። ምን ዓይነት “የእግዚአብሔር ቸርነትን” መጥቀስ ይችላሉ? እነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኙ በልቦ ውስጥ ምን ዓይነት ስሜቶች ጫሩ?

ኢሳይያስ 58–66፣ ውስጥ አዳኙን የሚገልፁ ሌሎች ምን ማጣቀሻዎችን አገኙ?

እንዲሁም ሞዛያ 3፥7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥46–53ን ይመልከቱ።

ምስል
በወንድ እጆች ከተያዘ ፋኖስ አንድ ሴት የሸክላ የዘይት ፋኖስ ስታበራ

“እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል” (ኢሳይያስ 60፥19)። የብርሃን ስጦታ፣ በኤቫ ቲሞቲ

ኢሳይያስ6062

“እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል።”

ኢሳይያስ60 እና62 ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዓለምን በመጨረሻው ቀናት እንዴት እንደሚባርክ ለማስተማር ስለብርሃን እና ጨለማ፣ ስለአይኖች እና ማየት ይናገራሉ። ለእነዚህ ሃሳቦች በተለይ በ ኢሳይያስ 60፥1–5፣ 19–2062፥1–2፣ ውስጥ ይመልከቱ። እነዚህን ምዕራፎች ሲያነቡ እግዚአብሔር ልጆቹን ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዴት እየሰበሰበ እንዳለ ያሰላስሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ሚናዎት ምንድን ነው?

እንዲሁም 1ኛ ኔፊ 22፥3–123ኛ ኔፊ 18፥24ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥9፤ ቦኒኤች. ኮርደን፣ “That They May See፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 78–80 ይመልከቱ።

ኢሳይያስ 64፥1–565፥17–2566

ክርስቶስ በሚሊኒየም ወቅት በምድር ላይ ይነግሣል።

ኢሳይያስ “የቀድሞው ጭንቀት [ስለሚረሳበት]” ቀን ተናገረ (ኢሳይያስ 65፥16)። ይህ ትንቢት በሙሉ ትርጓሜው ብዙ ክንዋኔዎች ሲኖረው፣ ያ ቀን ገና የሚመጣ ነው—ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመለስ እና ሚሊኒየም ተብሎ የሚጠራውን የሰላም እና የጽድቅ ዘመን ሲመሰርት። ኢሳይያስ ይህን የወደፊት ቀን በሚከተሉት ውስጥ ገለፀ፣ ኢሳይያስ 64፥1–565፥17–2566። “ደስታ” እና “ሐሤት” የሚሉትን ቃላት ምን ያህል ጊዜ እንደተጠቀመ ያስተውሉ። የአዳኙ መመለስ ለእርሶ ለምን የደስታ ቀን እንደሚሆን ያሰላስሉ። ለእርሱ መምጣት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ ይቸላሉ?

እንዲሁም የእምነት አንቀፆች 1፥10፤ ረስልኤም. ኔልሰን፣ “The Future of the Church: Preparing the World for the Savior’s Second Coming፣” ኢንዛይን፣ ሚያዚያ 2020 (እ.አ.አ)፣ 13–17 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍን ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኢሳይያስ 58፥3–11የቤተሰብ አባላት ኢሳይያስ ስለፆም ያስተላፈውንመልዕክት በ ኢሳይያስ 58፥3–5 እና በ ኢሳይያስ 58፥6–8፣ ውስጥ የተገለፀውን የፆም ዓይነት ከተወኑት የበለጠ ሊረዱት ይችላሉ። ፆማችንን በይበልጥ “[እግዚአብሔር] እንደመረ[ጠው] ፆም” እንዴት ማድረግ እንችላለን? ከመፆም ምን ዓይነት በረከቶችን አይተናል?

ኢሳይያስ 58፥13–14በሰንበት ቀን “ፈቃ[ዳችንን] በማግኘት” እና “በጌታ በመደሰት” መካከል ያለው ልዩነትምንድን ነው? ሰንበትን “[አስደሳች]” ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ኢሳይያስ 60፥1–5የቤተሰብ አባላት ኢሳይያስ 60፥1–3ን ሲያነቡ ጥቅሶቹ ብርሃንን ሲጠቅሱ መብራቱን ማብራት እና ጭለማን ሲጠቅሱ ደግሞ መብራቱን ማጥፋት ይችላሉ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለእኛ እንደብርሃን የሆነው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ህዝቦች የወንጌልን ብርሃን ሲያካፍሉ ኢሳይያስ ምን ይከሰታል ብሎ ተነበየ? ( ኢሳይያስ 60፥3–5ይመልከቱ)።

ኢሳይያስ 61፥1–3በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ አዳኙ እንዴት ነው የኢሳይያስን ትንቢቶች ያከናወነው? የእርሱ ተልዕኮ ገፅታዎች ያሳያሉ ብለው የሚሰማቸውን የአዳኙን ፎቶዎች እንዲመለከቱ የቤተሰብ አባላትን መጋበዝ ይችላሉ (ፎቶዎች በቤተክርስቲያን ጋዜጣዎች ወይም የወንጌል የስነጥበብ መጽሐፍ፣ ውስጥ ሊገኝ ይችላል)። እንደ “I Feel My Savior’s Love” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75 ያለ አዳኙ እንዴት እንደሚባርከን የሚወሳ መዝሙር መዘመርም ይችላሉ፣)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦“When He Comes Again፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 82–83።

የግል ጥናትን ማሻሻል

አካባቢዎትን ያዘጋጁ። አካባቢያችን በመማር ችሎታችን ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። የመንፈሱ ተፅዕኖ እየተሰማዎት ቅዱሳን መጽሐፍትን ለማጥናት የሚችሉበትን ቦታን ያግኙ። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 15ን ይመልከቱ።)

ምስል
ኢየሱስ በሰማይ ውስጥ

“ብርሃንሽ መጥቶአልና የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ አብሪ” (ኢሳይያስ 60፥1)። ብርሃን እና ሕይወት፣ በማርክ ማብሪ

አትም