“ጥቅምት 10–16 (እ.አ.አ)። ኤርምያስ 1–3፤ 7፤ 16–18፤ 20፦ ‘በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 10–16 (እ.አ.አ)። ኤርምያስ 1–3፤ 7፤ 16–18፤ 20፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 10–16 (እ.አ.አ)
ኤርምያስ 1–3፤ 7፤ 16–18፤ 20
“በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ”
ሽማግሌ ዴቪድኤ. ቤድናር እንዲህ አሉ፦ “[እግዚአብሔርን] የምሰማበት አንዱ መንገድ በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ነው። ቅዱሳን መጽሐፍት ቀድመው የተመዘገቡ የእግዚአብሔር ድምፅ ናቸው” (“‘Hear Him’ in Your Heart and in Your Mind፣” ChurchofJesusChrist.org)።
ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ
በመጀመሪያ ኤርምያስ ጥሩ ነብይ የሚሆን አልመሰለውም ነበር። እግዚአብሔር መጀመሪያ ሲጠራው “እናገር ዘንድ አላውቅም” ብሎ ተቃወመ (ኤርምያስ 1፥6)። እግዚአብሔር “ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ” ብሎ አረጋገጠለት (ቁጥር9)። ኤርምያስ ልምድ የሌለው “ልጅ” መስሎ ተሰማው (ቁጥር6)፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ካሰበው በላይ ዝግጁ እንደሆነ ገለፀ—ለዚህ ጥሪ ከመወለዱ በፊት ተሾሞ ነበር ( ቁጥር5ይመልከቱ)። ስለዚህ ኤርምያስ ፍርሃቱን ወደ ጎን ትቶ ጥሪውን ተቀበለ። አስመሳይ ቅድስናቸው ከጥፋት እንደማያድናቸው የኢየሩሳሌምን ንጉሶች እና ካህናት አስጠነቀቀ። መናገር የማይችል የመሰለው “ልጅ” የእግዚአብሔር ቃል “እንደሚነድድ ያለ እሳት በል[ቡ]” ሊሰማው ቻለ እናም ዝም ማለት አልቻለም (ኤርምያስ 20፥9)።
የኤርምያስ ታሪክ የእኛም ታሪክ ነው። ከመወለዳችን በፊት እግዚአብሔር ያውቀናል እናም ስራውን በምድር ላይ እንድንሰራ አዘጋጀን። ከሌሎች ነገሮች መካከል ያ ስራ ኤርምያስ የተነበየውን ያካትታል፦ እሱም የእግዚአብሔርን ህዝብ አንድ በአንድ ወደ “ጽዮን ለማምጣት” መሰብሰብን ያካትታል (ኤርምያስ 3፥14)። ምን እንደምናደርግ ወይም ምን እንደምንናገር በትክክል ባናውቅም እንኳን፣ “ከአንተ ጋር ነኝና … አትፍራ ይላል እግዚአብሔር” (ኤርምያስ 1፥8፣19)።
ስለ ኤርምያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኤርምያስ” የሚለውን ይመልከቱ።
ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ነብያት የሚጠሩት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገሩ ነው።
በ ኤርምያስ 1፥4–19 ውስጥ ስለኤርምያስ ነብይ የመሆን ጥሪ ሲያነቡ ነብያት በሕይወቶ ውስጥ ያላቸውን ሚና ያሰላስሉ። እግዚአብሔር ለኤርምያስ ከሰጠው ቃላት ስለነብያቶች ምን ይማራሉ (እንዲሁም ኤርምያስ 7፥1–7ይመልከቱ)። የኤርምያስ ስብከት ብዙውን ጊዜ ውድቅ ሆኖ ነበር ( ኤርምያስ 20፥8፣10ይመልከቱ)። በ ኤርምያስ 20፥9ውስጥ ከኤርምያስ ቃላት ምን ይማራሉ? የኤርምያስን ትምህርቶች በሚያጠኑ ሰዓት ሁሉ እነዚህን ሃሳቦች ያስታውሱ። በእነዚህ ትምህርቶች ውስጥ የኋለኛው ቀን ነብያትን እንዲከተሉ የሚያነሳሳዎት ምን ነገር ያገኛሉ?
ከመወለዴ በፊት እግዚአብሔር ያውቀኝ ነበር።
ኤርምያስ ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔር ያውቀው ነበር እናም በምድር ላይ የተለየ ተልዕኮ እንዲፈጽም መረጠው ወይም አስቀድሞ ሾመው ( ኤርምያስ 1፥5ይመልከቱ)። ኤርምያስ ይህን ማወቁ አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስሎታል?
እግዚአብሔር ከመወለዶ በፊት ያውቆት ነበር እንዲሁም ለተለዩ ሃላፊነቶች አስቀድሞ ሾሞዎታል ( አልማ 13፥1–4፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥53–56፤ አብርሐም 3፥22–23ይመልከቱ)። ይህ እውቀት በሕይወቶ ውስጥ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? የፓትሪያርክ በረከቶን ከተቀበሉ በጸሎት ሊከልሱት እና እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ቀድሞ የሾሞትን እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ እርሱን ሊጠይቁት ይችላሉ።
በተጨማሪም ከወንጌል ርእስቶች፣ “አሰቀድሞ መሾም፣” “የቅድመ ምድር ህይወት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።
“እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል።”
እስራኤላውያን ይኖሩባት በነበረችው ደረቅ ምድር ውስጥ ውድ የሆነውን ውኃ የውኃ ጉድጓዶች በሚባሉ የከርሰምድር ማጠራቀሚያ ውስጥ ያጠራቅሙ ነበር። በውኃ ጉድጓዶች ከመመካት ይልቅ ውኃን ከምንጭ መቀበል ለምን የተሻለ ይሆናል? “የሕያውን ውኃ ምንጭ” መተው ማለት ምን ማለት ነው? በ ኤርምያስ 2፥13 ውስጥ የተጠቀሰው “የተቀደዱት ጉድጓዶች” ምንን የሚወክሉ ይመስሎታል? ኤርምያስ2 እና7ን ሲያነቡ ህዝቡ የእግዚአብሔርን የሕያው ውኃ እንዴት እንደተዉ ያስተውሉ እናም በሕይወቶ ውስጥ የሕያውን ውኃ እንዴት እየተቀበሉ እንዳሉ ያስቡ።
ኤርምያስ7 የተጻፈው “እግዚአብሔርን [ለማምለክ] … በእግዚአብሔር ቤት በር” እየገቡ ለነበሩ ሰዎች ነው (ኤርምያስ 7፥2)። ይሁን እንጂ የዚህ ውጫዊ የአምልኮ ገፅታ ቢኖራቸውም ቅሉ የታላቅ ክፋት ጥፋተኛ ነበሩ ( ቁጥሮች 2–11ይመልከቱ)። በ ቁጥሮች 21–23ውስጥ እግዚአብሔር ለእርሶ ምን ዓይነት መልዕክቶች እንዳለው ይሰማዎታል?
እግዚአብሔር ህዝቦቹን ይሰበስባል።
ኤርምያስ ስለተበታተኑት እስራኤላውን መሰብሰብ ሲተነብይ ከግብፁ ስደት እጅግ በጣም ታላቅ እንደሚሆን ተናገረ ( ኤርምያስ 16፥14–15ይመልከቱ)። ተመሳሳይ በሆነ መንፈስ ፕሬዚዳንት ረስልኤም. ኔልሰን እንዲህ አሉ፦ “በዚህ ወሳኝ ጊዜ …እስራኤልን ለመሰብሰብ ለመርዳት ወደ ምድር ተልከዋል። በአሁን ሰዓት ከዛ [መሰብሰብ] የበለጠ ጠቃሚ የሚሆን በዚህ ምድር ላይ የሚደረግ ምንም ነገር የለም። … ይህ መሰብሰብ ለእርሶ ሁሉንም ነገር ማለት መሆን አለበት” (ረስልኤም. ኔልሰን እና ዌንዲደብሊው. ኔልሰን፣ “Hope of Israel” [የዓለም አቀፍ የወጣቶች አምልኮ፣ ሰኔ3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ ተጨማሪ ኒው ኤራ እና ኢንዛይን፣ ነሐሴ 2018 (እ.አ.አ)፣12፣ ChurchofJesusChrist.org)።
ኤርምያስ 3፥14–18፤ 16፥14–21ን ሲያጠኑ ስለኋለኛው ቀን የእስራኤል መሰብሰብ ምን ያነሳሳዎታል? እነዚህ ጥቅሶች ያ መሰብሰብ እንዴት እንደሚከናወን ምን ይጠቁማሉ? ከላይ በተጠቀሰው የፕሬዚዳንት ኔልሰን ቀሪ መልዕክት ውስጥ ምን ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ያገኛሉ?
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ኤርምያስ 1፥5።ከመወለዳችን በፊት ከሰማይ አባታችን ጋር ስለነበረን ሕይወት ለማውራት ይህን ጥቅስ ሊጠቀሙ ይችላሉ። እንደ “I Lived in Heaven” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣4) እና “Introduction: Our Heavenly Father’s Plan” ( የብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 1–5) ዓይነት ግብዓቶች ሊረዱ ይችላሉ። የቅድመ ሕይወታችንን ማወቅ በምድራዊ ሕይወታችን አኗኗር ላይ እንዴት ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
-
ኤርምያስ 2፥13፤ 17፥13–14።የቤተሰብ አባላት እነዚህን ጥቅሶች በዓይነ ህሊናቸው እንዲመለከቱት ለመርዳት ውኃን በተሰነጠቀ ወይም በተሰበረ መያዣ ውስጥ ሲጨምሩ ምን እንደሚሆን ማሳየት ይችላሉ። “የሕያው ውኃ ምንጭ” እና “የተቀደዱት ጉድጓዶች” ምንን ይወክላሉ? (ኤርምያስ 2፥13)። ከእግዚአብሔር የሕያው ውኃ የሚጠጡትሰ እንዴት ነው?
-
ኤርምያስ 16፥16።ፕሬዚዳንት ራስልኤም. ኔልሰን በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያሉ አሳ አጥማጆችን እና አዳኞችን ከኋለኛው ቀን ሚስዮናውያን ጋር አነፃፅረዋል ( “The Gathering of Scattered Israel፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2006 (እ.አ.አ)፣81 ይመልከቱ)። የቤተሰብ አባላት በቤትዎ ዙሪያ ያሉ ቁሳቁሶችን “ማደን” እና የተበታተኑ እስራኤላውያንን እንዴት “ማጥመድ” እና “ማደን” እንደሚችሉ መነጋገር ይችላሉ።
-
ኤርምያስ 18፥1–6።እነዚህን ጥቅሶች ለማሰስ ሸክላ እንዴት እንደሚሰራ ሊወያዩ ወይም ሊያሳዩ ይችላሉ። በ ኤርምያስ 18፥1–6፣ ውስጥ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ምን መልዕክት አለው? በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ እንደ የሸክላ ጭቃ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (እንዲሁም ኢሳይያስ 64፥8ይመልከቱ)። ከሸክላ ሰሪ ጭቃ ጋር ለሚያነፃፅረን ሌላ ታሪክ የሽማግሌ ሪቻርድጄ. ሜይኔስን መልዕክት “The Joy of Living a Christ-Centered Life” (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 27–30) ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፦ “እስራኤል፣ እስራኤል እግዚአብሔር አየተጣራ ነው፣” መዝሙር፣ ቁጥር 7።