ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 24–30 (እ.አ.አ)። ሕዝቅኤል 1–3፤ 33–34፤ 36–37፤ 47፦ “አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ”


“ጥቅምት 24–30 (እ.አ.አ)። ሕዝቅኤል 1–3፤ 33–34፤ 36–37፤ 47፦ ‘አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 24–30 (እ.አ.አ)። ሕዝቅኤል 1–3፤ 33–34፤ 36–37፤ 47፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በጎችን እየመራ

ኑ፣ ተከተሉኝ፣ በስካት ሰምነር

ጥቅምት 24–30 (እ.አ.አ)

ሕዝቅኤል 1–333–3436–3747

“አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ”

ሕዝቅኤል እርሱን እንዲያጠግበው—በምሳሌያዊ አነጋገር የእግዚአብሔርን ቃል “[እንዲበላ]” ተጋብዞ ነበር ( ሕዝቅኤል 2፥9–3፥3፣10ይመልከቱ)። በዚህ ሳምንት በእግዚአብሔር ቃል እራሶን እንዴት ያጠግባሉ?

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

ሕዝቅኤል በስደት የነበረ ነብይ ነበር። ኢየሩሳሌም በመጨረሻ ከመጥፋቷ ከብዙ ዓመታት በፊት ከሌሎች እስራኤላውያን ጋር ተይዞ ወደ ባቢሎን ተልኮ ነበር። በኢየሩሳሌም ውስጥ ሕዝቅኤል በቤተመቅደስ ውስጥ እንደ ካህን ሆኖ ያገለግል ነበር። በባቢሎን ውስጥ “ከምርኮኞች” መካከል ነበር እንዲሁም ከቤተመቅደሱ በመቶዎች በሚቆጠሩ ማይሎች እርቆ እና በጥቂት ወደ ውዱ የእግዚአብሔር ቤት የመመለስ ተስፋ “በተቀመጡበትም ቦታ ተቀመ[ጠ]” (ሕዝቅኤል 3፥15)። ከዚያም አንድ ቀን ሕዝቅኤል ህልምን አየ። “የእግዚአበሔር ክብር[ን]” አየ (ሕዝቅኤል 1፥28)—በኢየሩሳሌም ባለው ቤተመቅደስ ውስጥ ሳይሆን ነገር ግን እዛው በባቢሎን በስደት ውስጥ እያለ። በኢየሩሳሌም ያለው ክፋት የእግዚአብሔር መገኘት እዛ እስከማይኖር ድረስ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተማረ ( ሕዝቅኤል 8–1133፥21ይመልከቱ)።

አንዱ የሕዝቅኤል ስራ እስራኤላውያንን ስለእብሪተኝነታቸው ውጤት ማስጠንቀቅ ነበር—በአብዛኛው ሳይሰማ የቀረ ማስጠንቀቂያ። ነገር ግን ስለሕዝቅኤል መልዕክት የበለጠ ነገር አለ፦ ምንም እንኳን ነገሮች መጥፎ ቢሆኑም የመመለሻ መንገድ እንደነበረ ተነበየ። የእግዚአብሔር ህዝብ “የእግዚአብሔርን ቃል [ለመስማት]” (ሕዝቅኤል 37፥4)፣ ጥሪውን ቢቀበሉ ሞቶ የነበረ ነገር መልሶ ሕይወት ይዘራል። “የድንጋዩ ልብ” በ “[በስጋ] ልብ” ሊተካ ይችላል (ሕዝቅኤል 36፥26)። “መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፣” “እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ” ብሎ እግዚአብሔር ነገራቸው (ሕዝቅኤል 37፥14)። በመጨረሻ ቀናትም፣ እግዚአብሔር አዲስ ቤተመቅደስን እና አዲስ ኢየሩሳሌምን ይመሰርታል “ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም እግዚአብሔር በዚያ አለ ተብሎ ይጠራል” (ሕዝቅኤል 48፥35)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሕዝቅኤል 1–3

“ቃሌን ትነግራቸዋለህ።”

ስለሕዝቅኤል የማገልገል ጥሪ በ ሕዝቅኤል 1–3 ውስጥ ማንበብ እግዚአብሔር ለሌሎች “[ቃሉን ለመናገር]” ስለሰጦት እድሎች እንዲያስቡ ሊያደርግ ይችላል (ሕዝቅኤል 3፥4)። በ ሕዝቅኤል 2–3፣ ውስጥ ለሕዝቅኤል የማበረታቻ እና የመመሪያ ቃሎቹን ያስተውሉ። ምንም እንኳን የሚያገለግሏቸው ሰዎች ምናልባት እንደ ሕዝቅኤል ሰዎች እብሪተኞች ላይሆኑ ቢችሉም፣ ለሕዝቅኤል የተነገሩት የእግዚአብሔር ቃሎች በቤተክርስቲያን፣ በቤት እና በሌላ ቦታ የሚሰጡትን አገልግሎት በሚመለከቱበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንዳሳደሩ ያስቡ።

እንዲሁም ሕዝቅኤል 33፥1–9፤ ዲ.ታድ ክርስቶፈርሰን፣ “The Voice of Warning፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 108–11 ይመልከቱ።

ሕዝቅኤል 33፥10–19

ጌታ ይቅር ለማለት ይፈልጋል።

የተማረኩ እስራኤላውያን ፣ “ሃጢያታችን በላያችን [ካ]ሉ”፣ “እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን?” ሲሉ ተደነቁ (ሕዝቅኤል 33፥10)። በምላሹ፣ እግዚአብሔር ስለንስሃ እና ይቅርታ ጠቃሚ እውነታዎችን አስተማራቸው። እነዚህ ጥያቄዎች እነዚያን እውነቶች እንዲያሰላስሉ ይረዳዎታል፦

ሕዝቅኤል34

ጌታ በጎቹን እንድመግብ ጋብዞኛል።

ሕዝቅኤል34፣ ውስጥ እግዚአብሔር የህዝቦቹን መሪዎች “እረኞች” ብሎ ይጠራል። ሲያነቡ፣ መሪ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይህ ርዕስ ምን እንደሚጠቁም ያሰላስሉ። እግዚአብሔር እንዲመግቧቸው የሚፈልገው “በጎች” እነማን ናቸው? የአዳኙ እንደእረኛችን ያስቀመጠውን ምሳሌ እንዴት መከተል ይችላሉ? ( ቁጥሮች 11–31ን ይመልከቱ)።

እንዲሁም ዮሐንስ 21፥15–17ን ይመልከቱ።

በረሃ እና የሙት ባሕር

ሕዝቅኤል ወንዝ ከቤተመቅደስ ሲፈስ እና የሙት ባሕርን ሲፈውስ በራዕይ ውስጥ አየ።

ሕዝቅኤል37

እግዚአብሔር ህዝቦቹን እየሰበሰበ እና አዲስ ሕይወት እየሰጠ ነው።

የእስራኤል መሰብሰብ በ ሕዝቅኤል37 ውስጥ በሁለት ምልክቶች ተገልጿል። ስለ መጀመሪያው—የሞቱ አጥንቶች ወደ ሕይወት ስለመመሳቸው ሲያነቡ ( ቁጥሮች 1–14ይመልከቱ)—እስራኤልን በሁለቱም የመጋረጃ አቅጣጫዎች ስለመሰብሰብ ምን እንደተማሩ ያሰላስሉ( ሕዝቅኤል 36፥24–30ይመልከቱ)።

ሁለተኛው ምልክት ( ቁጥሮች 15–28ይመልከቱ) ሁለት በትሮችን ማለትም ምሁራን በማጠፊያ የተያያዘ የእንጨት መፃፊያ ሰሌዳ ብለው የተረጎሙትን ያጠቃልላል። የይሁዳ በትር መጽሐፍ ቅዱስን ሊወክል ይችላል (የመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠው ድርሻ ያለው በይሁዳ ዘሮች ስለተፃፈ) እንዲሁም የዮሴፍ በትር መጽሐፈ ሞርሞንን ሊወክል ይችላል (የሌሂ ቤተሰቦች የግብፁ ዮሴፍ ዘሮች ስሆኑ)። ያንን በአዕምሮ ውስጥ በመያዝ እነዚህ ጥቅሶች እስራኤላውያንን በመሰብሰብ ረገድ ስለቅዱሳን መጻህፍት ድርሻ ምን አስተማሮት? 2ኛ ኔፊ 3፥11–13 (ስለጆሴፍ ስሚዝ እና ስለመጽሐፈ ሞርሞን ትንቢት) ግንዛቤዎ ላይ ምን ይጨምራል?

እንዲሁም 2ኛ ኔፊ 29፥14፤ “The Book of Mormon Gathers Scattered Israel” (የሚለውን ቪዲዮ ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሕዝቅኤል 33፥1–5እነዚህን ጥቅሶች ለማብራራት አንድ የቤተሰብ አባል በመስኮት ወደ ውጪ በመመልከት እና ለተቀሩት የቤተሰብ አባላት ውጪ ምን እየተከናወነ እንዳለ በመናገር እንደ “[መለከት ነፊ]” ሊያስመስል ይችላል። በሕይወት ያለው ነብያችን እንዴት ነው ለእኛ እንደመለከት ነፊ የሆነው?

ሕዝቅኤል 33፥15–16እነዚህ ጥቅሶች በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት መቀበል ስለምንችለው ይቅርታ ምን ያስተምሩናል?

ሕዝቅኤል 36፥26–27አንድ ሰው “ድንጋያማ ልብ” ነው ያለው ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ሲወያዩ የተወሰኑ ድንጋዮችን ለቤተሰቦ ያሳዩ። አዳኙ የሚሰጠንን “አዲስ ልብ” እና “አዲስ መንፈስ” የሚገልፁ ቃላትን እንዲጠቁሙ ይፍቀዱላቸው ( ሞዛያ 3፥195፥2ይመልከቱ)።

ሕዝቅኤል 37፥15–28የቤተሰብ አባላት ሁለት በትሮችን በማግኘት በአንዱ ላይ ለይሁዳ (መጽሐፍ ቅዱስ) በሌላኛው ላይ ደግሞ ለጆሴፍ (መጽሐፈ ሞርሞን) ብለው መፃፍ ይችላሉ ( ቁጥሮች 16–19ይመልከቱ)። ከዚያም ወደ አዳኙ እንዲቀርቡ እና “[የእርሱ] ህዝብ” እንዲሆኑ የሚረዷቸውን ታሪኮች ወይም ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከመጽሐፈ ሞርሞን ሊያካፍሉ ይችላሉ (ቁጥር23)።

ሕዝቅኤል 47፥1–12እነዚህ ጥቅሶች ከቤተመቅደስ ስለሚፈሰው እና የሙት ባሕርን ስለሚፈውሰው—በጣም ጨዋማ በመሆኑ የተነሳ አሶች እና እፅዋቶች በውስጡ መኖር ስለማይችሉበት ባሕር ሕዝቅኤል ያየውን የውኃ ራዕይ ይገልፃሉ። ልጆች የዚህን ራዕይ ስዕል በመሳል ሊደሰቱ ይችላሉ። ከቤተመቅደሱ የሚፈሰው ውኃ ምንን ሊወክል ይችላል? (“And the River Will Grow፣” ChurchofJesusChrist.orgየሚለውን ቪዲዮ ይመልከቱ)። ቤተመቅደስ እንዴት ነው እኛን ለመፈወስ የሚረዳው? ( ሕዝቅኤል 47፥8–9፣11ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “Dear to the Heart of the Shepherd፣” መዝሙር፣ ቁጥር221።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ሁሉንም ነገር ለመሸፈን አይሞክሩ። የሕዝቅኤልን እያንዳንዱን እውነታ ከቤተሰቦ ጋር ለማሰስ ላይችሉ ይችላሉ። ምን ላይ እንደሚያተኩሩ ለመወሰን መንፈሳዊ ምሪትን ይሹ። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 7ን ይመልከቱ።)

ወንዝ ከቤተመቅደስ ሲፈስ የሚያሳይ ምስል

“እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ይወጣ ነበር።… ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል” (ሕዝቅኤል 47፥1፣9)። ከ shutterstock.comበፍቃድ የተወሰደ ምስል።