ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 31–ህዳር6 (እ.አ.አ)። ዳንኤል 1–6፦ “የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና”


“ጥቅምት 31–ህዳር6 (እ.አ.አ)። ዳንኤል 1–6፦ ‘የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና፣’“ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [(2021) እ.አ.አ]

“ጥቅምት 31–ህዳር6 (እ.አ.አ)። ዳንኤል 1–6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ዳንኤል የንጉሥን ህልም እየፈታ

ዳንኤል የናቡከደነፆርን ህልም ሲፈታ፣ በግራንት ሮምኒ ክላሰን

ጥቅምት 31–ህዳር6 (እ.አ.አ)

ዳንኤል 1–6

“የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና”

ሽማግሌ ሪቻርድጂ. ስካት መነሳሳትን ስለመመዝገብ እንዲህ ገለፁ፣ “የእግዚአብሔር ንግግር ለእኛ የተቀደሰ እንደሆነ ለእርሱ ያሳየዋል። መመዝገብ ራዕይን የማስታወስ ችሎታችንንም ያዳብራል” [“How to Obtain Revelation and Inspiration for Your Personal Life፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2012 (እ.አ.አ) 46]።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

መቼም በኢየሱስ ክርስቶስ ባሎት እምነት ምክንያት ማንም ሰው ወደ እሳት እቶን ውስጥ ወይም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ሊወረውሮት አያስፈራራዎትም። ነገር ግን ማንኛችንም የእምነት ፈተና ሳይገጥመን በዚህ ሕይወት ውስጥ ማለፍ አንችልም። በታላቋ የባቢሎን ግዛት በምርኮ ከተወሰዱት እንደ ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ካሉ ወጣት ወንዶች ምሳሌ ሁላችንም መጠቀም እንችላለን ( 2ኛ ነገሥት 24፥10–16ን ይመልከቱ)። እነዚህ ወጣቶች የተለዩ እሴቶች ባሉት ያልተለመደ ባህል ተከበው ነበር፣ እናም እምነታቸውን እና ጽድቅ ባህላቸውን ለመተው ታላቅ ፈተናዎች ገጠማቸው። ነገር ግን ለቃልኪዳኖቻቸው ታማኝ ሆኑ። ልክ ዮሴፍ በግብጽ እና አስቴር በፋርስ እንዳደረጉት ሁሉ፣ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ውስጥ እምነታቸውን ጠበቁ እናም እግዚአብሔር አሁንም ድረስ በዚህ ቀን አማኞችን የሚያነሳሳ ታምራትን ሰራ።

ታማኝ ሆነው ለመቆየት ጥንካሬውን እንዴት አገኙ? እግዚአብሔር ሁላችንም እንድናደርግ የጠየቀውን እነዚያን ትንሽ እና ቀላል ነገሮች አደረጉ—እነሱም መጸለይ፣ መፆም፣ መልካም ጓደኞችን መምረጥ፣ በእግዚአብሔር መታመን እና ለሌሎች ብርሃን መሆን ናቸው። እነዚህን ተመሳሳይ ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን በማድረግ ስለጠነከርን በሕይወታችን ውስጥ የሚከሰቱት አንበሳዎችን እና የእሳት እቶንን መጋፈጥ እንችላለን።

ስለመጽሐፈ ዳንኤል አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መጽሐፈ ዳንኤል” የሚለውን ይመልከቱ፡፡

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዳንኤል136

እምነቴ ሲፈተን በእግዚአብሔር መታመን እችላለሁ።

በአንድ መልኩ፣ ሁላችንም በባቢሎን ውስጥ ነው የምንኖረው። በዙሪያችን ያለው ዓለም መስፈርቶቻችንን እንድናላላ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት እንድንጠይቅ በሚያደርጉ በብዙ ፈተናዎች የተሞላ ነው። ዳንኤል13፣ እና 6ን ሲያነቡ ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ስህተት እንደሆኑ የሚያውቁትን ነገሮች እንዲያደርጉ የተገፉበትን መንገዶች ያስተውሉ። እምነቶን ለማላላት ጫና ተሰምቶት ያውቃልን? ተቃውሞ ሲገጥሞት በእግዚአብሔር እንዲያምኑ የሚረዳዎትን ከእነዚህ ሰዎች ምን ተማሩ?

የዳንኤል መጽሐፍ እና ሌሎች ብዙ ቅዱሳን መጽሐፍት ታላቅ እምነት ወደ ታላቅ ተአምራት የመራበትን ልምዶች መዝግበው ይዘዋል። ነገር ግን እምነታችን ወደምንሻቸው ተአምራት ባይመራንስ? (ለምሳሌ፣ አልማ14፥8–13ይመልከቱ)። በ ዳንኤል 3፥13–18፣ ውስጥ በሚያነቡት መሰረት ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ይህን ጥያቄ እንዴት ይመልሱታል ብለው ያስባሉ? ምሳሌያቸው የእምነት ፈተናዎን በሚመለከቱበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያደርጋል? ስለእነዚህ ጥቅሶች የበለጠ መረጃ ለማኘት የሽማግሌ ዴኒስኢ. ሲሞንስን መልዕክት “But If Not…” (ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2004 (እ.አ.አ)፣ 73–75) ይመልከቱ።

የዳንኤል መጽሐፍ የአንድ ሰው የጽድቅ ምርጫዎች ሌሎችን በጌታላይ ታላቅ እምነት እንዲኖራቸው ለመምራት እንደሚችል ያሳያል። ምን የዚህን ዓይነት ምሳሌዎች በ ምዕራፎች13፣ እና6፣ ውስጥ ያገኛሉ? ምርጫዎት በሌሎች ላይ ምን ዓይነት ውጤቶች እንዳለው ያሰላስሉ ( ማቴዎስ 5፥16ይመልከቱ)።

እንዲሁም የዲተርኤፍ. ኡክዶርፍን፣ “Be Not Afraid, Only Believe፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ የዴቪድአር. ስቶንን፣ “Zion in the Midst of Babylon፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2006 (እ.አ.አ)፣ 90–93 ይመልከቱ።

አራት ወንድ ልጆች በአንድ ሰው በጠረጴዛ ላይ  የቀረበውን ስጋ ሲቃወሙ

ዳንኤል እና ጓደኞቹ የንጉሡን ምግብ ሲቃወሙ የሚያሳይ፣ በብራየን ኮል

ዳንኤል2

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ናት።

ዳንኤል የናቡከደነፆር ህልም የወደፊት ዓለማዊ መንግስታትን እንደሚተነብይ በራዕይ አማክኝነት አየ እንዲሁም “ለዘላለም የማይፈርስ” የእግዚአብሔር የወደፊት መንግስትንም አየ (ዳንኤል 2፥44)። ሽማግሌ ዲ.ታድ ክርስቶፈርሰን እንዳስተማሩት፣ “ቤተክርስቲያኗ ያቺ በኋለኛው ቀን የተተነበየችው መንግስት ናት፣” “በሰው ሳይፈጠር ነገር ግን በሰማይ እግዚአብሔር የተዋቀረ እና ‘እጅ ሳይነካው ከተራራ የተፈነቀለ’ ምድርንም ለመሙላት እየተንከባለለ እንዳለ ድንጋይ [ናት]” (“Why the Church፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣111)። የድንጋዩን መግለጫ በ ዳንኤል 2፥34–35፣ 44–45፣ ውስጥ ሲያነቡ ስለእግዚአብሔር የኋለኛው ቀን መንግስት ያስቡ። በድንጋዩ እና በመንግስት መካከል ምን ዓይነት መመሳሰል ያያሉ? የእግዚአብሔር መንግስት ዛሬ ምድርን ሲሞላት እንዴት ያያሉ?

እንዲሁም የጎርደንቢ. ሂንክሊን፣ “The Stone Cut Out of the Mountain,” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2007 (እ.አ.አ)፣ 83–86፤ የኤል.ዊትኒ ክሌይተንን “The Time Shall Come፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 11–13 ይመልከቱ።

ዳንኤል 3፥19–28

አዳኙ በፈተናዎቼ ውስጥ ይደግፈኛል።

ከሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ጋር በእሳት እቶን ውስጥ ስለተገለፀው አራተኛ አካል ሲያነቡ ምን ዓይነት ግንዛቤ ወደ እርሶ መጣ? በሚያጋጥሞት ፈተናዎች ውስጥ ይህ ዘገባ እንዴት ሊረዳዎት ይችላል? በሚከተሉት ውስጥ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ሊያገኙ ይችላሉ፣ ሞዛያ 3፥5–7አልማ 7፥11–13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61፥36–37121፥5–8

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዳንኤል 1–2 ዳንኤል1 እና2 ን በጋራ ሲያነቡ ዳንኤል እና ጓደኞቹ የንጉሡን ስጋ እና ወይን ከመብላት እና ከመጠጣት በመታቀባቸው የተቀበሉትን በረከቶች መመልከት ይችላሉ። (“God Gave Them Knowledge፣” ChurchofJesusChrist.org፣ የሚለውን ቪድዮ ይመልከቱ።) አነዚያን በረከቶች የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ስንጠብቅ ከገባልን ቃልኪዳኖች ጋር ለምሳሌ ከጥበብ ቃል ጋር ማነፃፀር ይችላሉ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥18–21ይመልከቱ)። የጥበብ ቃልን በመጠበቃችን እንግዚአብሔር እንዴት ነው የባረከን?

ዳንኤል3ዳንኤል3፣ ውስጥ ስላለው ታሪክ ቤተሰብዎ እንዲማሩ እንዴት ይረዳሉ? “የሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ” ታሪክ በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሊረዳ ይችላል። ስለሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ምን ያስገርመናል። እምነታችንን የሚፈትን እና እግዚአብሔርን እንደምናምን ማሳየትን የሚጠበቅብን ምን ዓይነት ሁኔታዎች ያጋጥሙናል?

ዳንኤል 6፥1–23ቤተሰቦ በ ዳንኤል 6፥1–23 ውስጥ ያለውን ታሪክ ክፍሎች በመተወን ሊደሰቱ ይችላሉ (ለምሳሌ፣ ቁጥሮች 10–12 ወይም 16–23)። ከዳንኤል ምሳሌ ምን እንማራለን? እርሱን የበለጠ ለመምሰል ምን ማድረግ እንችላለን?

ዳንኤል 6፥25–27በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት እግዚአብሔር ዳንኤልን ከአንበሶች ሲያድን ንጉሥ ዳርዮስ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አሳደረ? እንዲሁም ንጉሥ ናቡከደነፆር በተመሳሳይ መንገድ ተፅዕኖ እንደደረሰበት በ ዳንኤል 2፥473፥28–29 ውስጥ ማንበብ ይችላሉ። ሌሎች ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ምን እድሎች አሉን? የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የሌሎች ሰዎች እምነት በሌሎች ሰዎች ላይ እንዴት መልካም ተፅዕኖ እንዳሳደረ ካዩት ምሳሌዎች ይወያዩ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “I Want to Live the Gospel፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣148።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ትምህርቱን ያስተምሩ። የጌታ ወንጌል በቀላልነቱ ቆንጆ ነው ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥57ይመልከቱ)። በትምህርት ላይ ያተኮሩ ቀላል እንቅስቃሴዎች እና ውይይቶች የወንጌልን መልዕክት ወደ ቤተሰቦ ልቦች ውስጥ እንዲያደርስ መንፈስ ቅዱስን ሊጋብዙ ይችላሉ።

ዳንኤል በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ

ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ፣ 1872 (እ.አ.አ)። ሪቬር፣ ብሪተን [1840–1920 (እ.አ.አ)]። እውቅና፦ የዋልከር የስነጥበብ ጋለሪ፣ የብሔራዊ ሙዚየሞች ሊቨርፑል/ብሪጅማን ምስሎች