ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ህዳር 21–27 (እ.አ.አ)። ዮናስ፤ ሚክያስ፦ “ምሕረትን ይወዳል”


“ህዳር 21–27 (እ.አ.አ)። ዮናስ፤ ሚክያስ፦ ‘ምሕረትን ይወዳል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ህዳር 21–27 (እ.አ.አ)። ዮናስ፤ ሚክያስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.ኤ.አ)

አሳ ነባሪ በውቅያኖስ ውስጥ ከጀርባው ሆኖ አንድ ሰው በውቅያኖስ ዳርቻ ላይ ሲንፏቀቅ

ዮናስ በነነዌ በውቅያኖስ ዳርቻ ላይ፣ በዳንኤልኤ. ልዊስ

ህዳር 21–27 (እ.አ.አ)

ዮናስሚክያስ

“ምሕረትን ይወዳል”

ግንዛቤዎን ሲመዘግቡ በዮናስ እና በሚክያስ ውስጥ ያሉ መርሆዎች በቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ እየተማሩ ካሉት ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ያስቡ።

ያሳደረብዎትን ስሜት መዝግቡ

ዮናስ ወደ ተርሴስ በሚሄድ መርከብ ውስጥ ነበር። በመርከብ ወደ ተርሴስ መጓዝ ምንም ስህተት አልነበረም ነገር ግን ከነነዌ ማለትም የእግዚአብሔርን መልዕክት ለማድረስ ዮናስ መሄድ ከነበረበት ቦታ በጣም እርቆ መገኘቱ እንጂ። ስለዚህ መርከቧ ታላቅ ማዕበል ሲያጋጥማት ዮናስ ባለመታዘዙ ምክንያት እንደነበረ አወቀ። በዮናስ ጥያቄ መሰረት፣ ማዕበሉን ለማቆም መርከበኞቹ በባሕሩ ጥልቅ ውስጥ ወረወሩት። የዮናስ እና የአገልግሎቱ መጨረሻ ይመስል ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዮናስ ላይ ተስፋ አልቆረጠም ነበር—ልክ በነነዌ ሰዎች ላይ እና በእያንዳንዳችን ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ ሁሉ። ሚክያስ እንዳስተማረው ጌታ እኛን በማውገዝ አይደሰትም ነገር ግን “በምሕረት ይደሰታል።” ወደ እርሱ ስንመለስ “ተመልሶ ይምረናል፣ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፣ ሃጢያታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል” (ሚክያስ 7፥18–19)።

ስለዮናስ እና ሚክያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዮናስ” እና “ሚክያስ” የሚሉትን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዮናስ 1–4ሚክያስ 7፥18–19

ጌታ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሁሉ መሃሪ ነው።

የዮናስ መጽሐፍ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ንስሃ ስንገባ እግዚአብሔር እንዴት መሃሪ እንደሆነ ያሳያል። ትንቢተ ዮናስን ሲያነቡ የእርሱን የምህረት ምሳሌዎች ይፈልጉ። ያንን ምህረት በሕይወትዎ ውስጥ እንዴት እንደተለማመዱት ያሰላስሉ። ለሌሎች የበለጠ መሃሪ ለመሆን ሊረዳዎት የሚችል ምን ነገር ተማሩ?

የእግዚአብሔርን ምህረት መመልት ብዙ ጊዜ የፍቅርን እና የምስጋናን ስሜት ይጭራል። ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር የእስራኤል ጠላቶች ለነበሩት ለነነዌ ሰዎች ምህረትን ሲሰጥ፣ ዮናስን “ደስ አላሰኘውም” እናም “ተቆ[ጥቶ]” ነበር (ዮናስ 4፥1)። ዮናስ ለምን እንደዚህ የተሰማው ይመስልዎታል? ተመሳሳይ ስሜቶች ተሰምቶት ያውቃልን? በ ምዕራፍ4ውስጥ እግዚአብሔር ዮናስን ምን ለማስረዳት እየሞከረ ይመስሎታል?

ሚክያስ 7፥18–19ውስጥ ያሉትን ትምህርቶች ያሰላስሉ። እነዚህ እውነታዎች ዮናስ ለእግዚአብሔር እና ለነነዌ ሰዎች ያለውን አመለካከት ለመቀየር እንዴት ረዳው?

ሉቃስ 15፥11–32፤ ጀፍሪአር. ሆላንድ፣ “The Justice and Mercy of God፣” ኢንዛይን፣ መስከረም. 2013 (እ.አ.አ) 16–21 ይመልከቱ።

ሁለት ሰዎች በወንዝ ዳርቻ ሲያወሩ

ወንጌልን ለእግዚአብሔር ልጆች ማካፈል እንችላለን።

ዮናስ13–4

ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ወንጌልን መስማት ያስፈልጋቸዋል።

ነነዌ በአመፃ እና በጭካኔ በሚታወቀው በአሲርያ ግዛት ውስጥ ነበረች። የነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበል እና ንስሃ ለመግባት መዘጋጀታቸው ለዮናስ ምናልባት ከእውነት የራቀ መስሎት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ዳለንኤች. ኦክስ እንዳስተማሩት፦ “ማን ዝግጁ እንደሆነ እና ማን ዝግጁ እንዳልሆነ እንደፈራጆች ራሳችንን ፈፅሞ መውሰድ የለብንም። እግዚአብሔር የሁሉንም ልጆቹን ልቦች ያውቃል እናም ለመነሳሳት ከጸለይን፣ ‘ቃሉን ለመስማት በዝግጅት ላይ ያሉ የሚያቃቸውን’ ሰዎች እንድናገኝ ይረዳናል (አልማ 32፥6)” (“Sharing the Restored Gospel፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 58–59)። ከ ዮናስ3 ለመለወጥ ዝግጁ ለማይመስሉ ሰዎች እራሱ ወንጌልን ለማካፈል የሚያነሳሱ ምን ነገሮችን ተማሩ?

የዮናስን አመለካከት ( ዮናስ13–4ይመልከቱ) ከአልማ እና ከሞዛያ ወንድ ልጆች ስሜቶች ጋር ማነፅፀር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ( ሞዛያ 28፥1–5አልማ 17፥23–25ይመልከቱ)።

3ኛ ኔፊ 18፥32ይመልከቱ።

ሚክያስ 4፥11–135፥8–157፥5–7

ኢየሱስ ክርስቶስ የሚክያስን ጽሑፎች ጠቀሰ።

አዳኙ ኢሳይያስን እና መዝሙረ ዳዊትን እንደጠቀሰ በደንብ ይታወቃል። በተጨማሪም ሚክያስን ብዙ ጊዜ እንደጠቀሰው ያውቃሉ? የሚከተሉትን ምሳሌዎች ያስቡ እናም እነዚህ ገፆች ለምን ለአዳኙ ጠቃሚ እንደሆኑ ያሰላስሉ። እነሱ ለእርሶ ጠቃሚ የሆኑት ለምንድን ነው?

ሚክያስ 4፥11–13 ( 3ኛ ኔፊ 20፥18–20ይመልከቱ)። ጌታ የኋለኛው ቀን ማሰባሰብን ከስንዴ አጨዳ ጋር አነፃፀረ ( አልማ 26፥5–7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥3–4ይመልከቱ)። ይሄ ንፅፅር ስለእስራኤል መሰብሰብ ምን ይጠቁማል?

ሚክያስ 5፥8–15 ( 3ኛ ኔፊ 21፥12–21ይመልከቱ)። እነዚህ ጥቅሶች በመጨሻዎቹ ቀናት ስለሚኖሩት የእግዚአብሔር ሰዎች (“የያዕቆብ ቀሪዎች”) ለናንተ ምን ይጠቁማሉ?

ሚክያስ 7፥5–7 ( ማቴዎስ 10፥35–36ይመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት መጀመሪያ “ወደ እግዚአብሔር [መመልከት]” ለምን ይጠቅማል? ይህ ምክር ለምንድን ነው ዛሬ የሚጠቅመው?

ሚክያስ 6፥1–8

“እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድን ነው?”

ሚክያስ “ወደ እግዚአብሔር ፊት [መጥቶ] በልዑል አምላክ ፊት [መስገድ]” ምን እንደሚመስል እንድናስብ ይጋብዘናል (ሚክያስ 6፥6)። እግዚአብሔር ሕይወቶን ሲገመግም ለእርሱ ምን ጠቃሚ እንደሆነ ቁጥሮች 6–8 ምን ይጠቁሞታል?

ማቴዎስ 7፥21–2325፥31–40፤ የዴልጂ. ረንለንድን፣ “Do Justly, Love Mercy, and Walk Humbly with God፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 109–12 ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዮናስ 1–4ልጆችዎ የዮናስን ታሪክ የሚናገሩ ትወናዎችን ለምሳሌ መኮብለልን በማስመሰል፣ በማዕበል የተሞላ ውቅያኖስን ድምፅ በማውጣት ወይም በትልቅ አሳ መዋጥን በማስመሰል በመተወን ሊደሰቱ ይችላል ( “ነብዩ ዮናስ” በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮችውስጥ ይመልከቱ)። ከዮናስ ልምድ ምን እንደተማሩ የቤተሰብ አባላትን ይጠይቁ። ከዮናስ ስለሚገኝ አንድ ትምህርት ምሳሌ “ነብዩን ተከተሉ” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 110–11) ቁጥር 7ን ይመልከቱ።

ዮናስ3ወንጌልን ስለማካፈል ዮናስ ምን ተማረ? ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመስማት ሊባረኩ የሚችሉ እነማንን እናውቃለን?

ሚክያስ 4፥1–5በእነዚህ ቁጥሮች መሰረት፣ ለእግዚአብሔር ሰዎች ሰላምን እና ብልፅግናን የሚያመጣው ምንድን ነው? ይህን ትንቢት በቤታችን ውስጥ እንዲሳካ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?

ሚክያስ 5፥2ኢየሱስ ልጅ ሳለ ከእናቱ ጋር የሚያሳይን ፎቶ በክፍሉ አንድ ጎን ላይ እና የጥበበኞቹን ሰዎች ፎቶ ደግሞ በሌላኛው ጎን ላይ ማሳየት ይችላሉ ( የወንጌል ስለጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥር 33ይመልከቱ)። ሚክያስ 5፥2 እና ማቴዎስ 2፥1–6ን በጋራ ያንብቡ። የሚክያስ ትንቢት ጥበበኛ ሰዎቹ ኢየሱስን እንዲያገኙት የረዳቸው እንዴት ነው? የቤተሰብ አባላት የጥበበኛ ሰዎቹን ፎቶ ከኢየሱስ ፎቶ አጠገብ ማድረግ ይችላሉ። ቤተሰቦ “The Christ Child: A Nativity Story” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ በመመልከት ሊደሰቱ ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከሩ መዝሙሮች፦ “አንተ ወደ ፈለግከው እሄዳለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 270።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የእግዚአብሔርን ፍቅር አግኙ። ቅዱሳን መፃህፍትን ሲያነቡ የሚያስተውሏቸውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማረጋገጫዎች መመዝገብን ያስቡ። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር በዮናስ ታሪክ ውስጥ ለልጆቹ ፍቅሩን እንዴት እንዳሳየ ይመልከቱ።

አንድ ሰው ከጀልባ ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ሲወረወር

ምስል በኬቨን ካርደን