በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ዮናስ


“ነቢዩ ዮናስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2021 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ዮናስ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዮናስ 1–4

ነቢዩ ዮናስ

በጌታ ምህረት መታመንን መማር

ዮናስ አዝኖ

ዮናስ ነቢይ ነበር። ንስሐ ካልገቡ ከተማቸው እንደምትጠፋ በነነዌ ያሉ ሰዎችን እንዲያስጠነቅቅ ጌታ ነገረው።

ዮናስ 1፥1–2

ዮናስ በመርከብ ሲሳፈር

ነገር ግን የነነዌ ሰዎች ለእስራኤላውያን ጠላቶች ነበሩ። ዮናስ ለእነርሱ ለመስበክ አልፈለገም። ስለዚህ ከነነዌ በጣም ርቆ ለመጓዝ በመርከብ ተሳፈረ።

ዮናስ 1፥3

በማዕበል እየተናጠ ባለ ባሕር ላይ ያለች መርከብ

ዮናስ በመርከቡ ላይ እያለ ሃይለኛ አውሎ ነፋስ መጣ። በመርከቡ ላይ የነበሩት ሰዎችም ለህይወታቸው ፈርተው ነበር። እንዲያድናቸው ወደጌታ እንዲጸልይ ዮናስን ጠየቁት።

ዮናስ 1፥4–6

ዮናስ ከመርከበኞች ጋር ሲነጋገር

ዮናስ ጌታ እንዲያደርግ ከጠየቀው እየሸሸ ስለሆነ ጌታ ማዕበሉን እንደላከው አወቀ። ዮናስም በመርከቡ ላይ ያሉትን ሰዎች ለማዳን ፈለገ። ወደ ባህር ውስጥ ቢጥሉት አውሎ ንፋሱ እንደሚቆም ተናገረ።

ዮናስ 1፥12

መርከበኞቹ ዮናስን ከመርከቡ ውጪ ወረወሩት

ሰዎቹም ዮናስን ከመርከቡ ውጪ ለመጣል አልፈለጉም ነበር። መርከቡን ወደ ደረቅ ምድር ለመውሰድ ሞከሩ፣ ነገር ግን አውሎ ንፋሱ ሃይለኛ ነበር። በመጨረሻም፣ ዮናስን ወደ ባህር ጣሉት።

ዮናስ 1፥13–15

ትልቅ አሳ ዮናስን ሲውጥ

አውሎ ንፋሱ ቆመ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ዮናስ በትልቅ አሳ ተውጦ ነበር።

ዮናስ 1፥15፣ 17

ዮናስ በባህር ዳርቻ

ዮናስም በአሳው ሆድ ውስጥ ለሶስት ቀን እና ለሶስት ምሽት ቆየ። በዚያም ጊዜ ዮናስ ጸለየ እንዲሁም ንስሀ ገባ። ትክክል የሆነውን ለማድረግና ጌታን ለማድመጥ ፈለገ። ጌታ የዮናስን ጸሎቶች ሰማና አሳው ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ እንዲተፋው አደረገ።

ዮናስ 1፥172፥1–10

ዮናስ ለሰዎች ሲሰብክ

እንደገናም ዮናስ ለነነዌ ሰዎች እንዲሰብክ ጌታ ነገረው። በዚህ ጊዜ ግን ዮናስ ታዘዘ። ወደ ነነዌ ሄደ፤ ከዚያም ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ አለበለዚያ ጌታ ከተማቸውን እንደሚያጠፋ ነገራቸው። ንጉሱ እና ህዝቡ ንስሀ ገቡ። ጌታ ይቅር አላቸው፤ ነነዌንም አላጠፋም።

ዮናስ 3

ዮናስ ተቆጥቶ

ነገር ግን ዮናስ ሰዎቹ ባለመጥፋታቸው ቅር ተሰኘ። ይቅርታ ማግኘት የሚገባቸው አልመሰለውም።

ዮናስ 4፥1–2

ዮናስ የደረቀ ዛፍን ሲመለከት

ዮናስን ለማስተማርም ጌታ ዮናስን ከጸሀይ ለማስጠለል የሚችል አንድ ዛፍ አሳደገ። ከዚያም ተክሉ ደረቀ፤ እናም ዮናስ ስለተክሉ አዘነ።

ዮናስ 4፥5–9

ዮናስ የተሰበሰቡ ሰዎችን ሲያስተምር

ጌታ ዮናስን ስለልጆቹ እያስተማረው ነበር። ዮናስም ሰዎች ንስሐ በማይገቡበት ጊዜ ማዘን እንዳለበት እና ሲገቡም ደስተኛ መሆን እንዳለበት ተማረ።

ዮናስ 4፥10–11