“ፋሲካ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ፋሲካ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ፋሲካ
በጌታ መጠበቅ
ፈርኦን እስራኤላውያን ነጻ እንዲሆኑ አልፈቀደም፣ ስለዚህም ጌታ አንድ የመጨረሻ መቅሰፍት እንደሚልክ ለሙሴ ነገረው። በግብፅ ምድር የእያንዳንዱ ቤተሰብ የበኩር ልጅ፣ የእንስሶቻቸው በኩር ሳይቀር ይሞታል።
እስራኤላውያን የእርሱን መመሪያዎች ከተከተሉ መቅሰፍቱ ከእነርሱ እንደሚያልፍ እና እንደማይጎዳቸው ጌታ ቃል ገባ።
ጌታ እያንዳንዱ የእስራኤል ቤተሰብ እንከን የለሽ ወንድ ጠቦት መሥዋዕት በማድረግ የጠቦቱን ደም በቤታቸው በር ላይ እንዲቀቡ ነገራቸው።
ጠቦቱን እንዲያበስሉ እና በፍጥነት እንዲበሉ ጌታ ለእስራኤላውያን ነገራቸው። በሚመገቡ ጊዜ፣ ልብሳቸውን ለብሰው እና ቤቶቻቸውን ጥለው ለመሄድ ይዘጋጁ። ጌታም እነዚህን ነገሮች እስራኤላውያን ካደረጉ፣ የበኩር ልጆቻቸው ከመቅሰፍቱ ይድናሉ አለ።
ጌታ እንዳስጠነቀቀው፣ መቅሰፍቱ መጣ። የፈርዖን የመጀመሪያ ወንድ ልጅን ጨምሮ በግብጽ ሁሉም የበኩር ልጆች ሞቱ። ነገር ግን መቅሰፍቱ በበሩ መቃን ላይ የጠቦት ደም ያለበትን እያንዳንዱን ቤት አለፈ። ለጌታ ታዛዥ በመሆናቸው ምክንያት የእስራኤላውያን የበኩር ልጆች ዳኑ።
ፈርዖን በዚህ መቅሰፍት የገዛ ልጁ መሞቱን ባየ ጊዜ፣ ሙሴንና አሮንን እስራኤላውያንን ሁሉ ይዘው ከግብፅ እንዲወጡ ነገራቸው።
እስራኤላዊያን ሄዱ ነገር ግን ፈርዖን ተናዶ ነበር። ሠራዊቱንና እና ሠረገሎቹን ሰብስቦ እስራኤላውያንን አሳደዳቸው።
እስራኤላውያን በቀይ ባህር ሰፈሩ። ብዙም ሳይቆይ ፈርዖንና ሠራዊቱ ደረሱባቸው። እስራኤላውያን ግብፃውያን ሲመጡ ባዩ ጊዜ ፈርተው ነበር። ሙሴ ግን ጌታ እንደሚጠብቃቸው ለእስራኤላውያን ነገራቸው።
ግብፃውያን እየቀረቡ ሲሄዱ፣ ጌታ ሙሴን በትሩን ከፍ እንዲያደርግ ነገረው። ሙሴም እንደተባለው አደረገ፣ እናም ጌታ ባህሩን ከፈለው። እስራኤላውያን ባሕሩን በደረቅ መሬት ተሻገሩ። ከፈርዖንና ከሠራዊቱ ሸሹ።
የግብጽ ሠራዊት እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። እስራኤላውያን ሁሉ በባሕሩ ማዶ በደህና ሲደርሱ ጌታ ውሃው እንዲመለስ አደረገ። የግብጽ ሠራዊት በባህር ውስጥ ሰመጡ።
እስራኤላውያን በስተመጨረሻ ነጻ ሆኑ። መዝሙሮችን ዘመሩ፣ ጨፈሩ እና ጌታን አመሰገኑ፡፡ ጌታ ህይወታቸውን ያተረፈበት እና ከግብፅ ያወጣቸው ጊዜ እንደመሆኑ ሁልጊዜ ፋሲካን ያስታውሳሉ።