በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ


“ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዳንኤል 1፤ 3

ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ

አደገኛ የእምነት ፈተና

ንጉስ ናቡከደነዖር እና የወርቅ ሐውልት

ንጉስ ናቡከደነዖር ግዙፍ ወርቃማ ሐውልት ሠራና ሕዝቡ እንዲያመልኩት አስገደዳቸው። እምቢ ካሉ ወደ እቶነ እሳት ይጣሉ ነበር።

ዳኒኤል 1፥6–73፥1–6

ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ

የዳንኤል ጓደኞች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ እግዚአብሔርን ይወዱ ነበር እናም የንጉሱን የሐሰት አምላክ አያመልኩም ነበር። ንጉሱም በእነርሱ ላይ ተቆጣ።

ዳንኤል 3፥6–15

ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ፣ ከንጉሱ ጋር ሲነጋገሩ

ሦስቱ ጓደኞች እግዚአብሔርን ብቻ እንደሚያመልኩ ለንጉሱ ነገሩት። እግዚአብሔር ሊጠብቃቸው እንደሚችል ያምኑ ነበር። ነገር ግን ባያድናቸው እንኳን ላመኑበት ይቆሙ ነበር።

ዳንኤል 3፥15–18

ሶስት ሰዎች እና መልአክ በእሳት ውስጥ

ንጉሱ በሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ በጣም ተናድዶ ነበር። ወደ እቶኑ እሳት እንዲጣሉ አደረጋቸው። ነገር ግን ንጉሱ ግን ወደ አቶኑ እሳት ሲመለከት፣ ከሦስቱ ሰዎች ጋር በእሳት ውስጥ አንድ ሰማያዊ ፍጡር በማየቱ ተገረመ። በእሳቱ አልተጎዱም ነበር።

ዳንኤል 3፥19–25

ሶስቱ ሰዎች ከእሳት ውስጥ ሲወጡ

ንጉሱም ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎን ጠራቸው እና ከአቶን እሳቱ ወጡ። እሳቱ ምንም አልጎዳቸውም ወይም ልብሳቸውንም አላቃጠለም።

ዳንኤል 3፥26–27

ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ፣ ከንጉሱ ጋር ሲነጋገሩ

ህይወታቸው በአደጋ ላይ ቢሆንም፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አከበሩ። የእነርሱ ምሳሌ ንጉሱ በእግዚአብሔር እንዲያምን ረዳው።

ዳንኤል 3፥28–29