“ዳንኤል እና የንጉሱ ህልም፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“ዳንኤል እና የንጉሱ ህልም፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ዳንኤል 2
ዳንኤል እና የንጉሱ ህልም
እግዚአብሔር ለንጉሱ የላከው ሚስጥራዊ መልእክት
የባቢሎን ንጉስ ያበሳጨውን ህልም አየ። የእርሱ ካህናት እና ጥበበኛ ሰዎች ህልሙ ምን ትርጉም እንዳለው እንዲነግሩት በጥብቅ ጠየቀ።
ንጉሱ ህልሙን አልነገራቸውም። ካህናቱ እና ጥበበኞቹ ሰዎች በእውነት ሀይል ካላቸው ህልሙ ምን እንደነበር እና ምን ትርጉም እንዳለው ሊነግሩት እንደሚችሉ ተናገረ።
ካህናቱ እና ጥበበኞቹ ሰዎች ህልሙ ምን እንደነበር ንጉሱ ካልነገራቸው ህልሙን ሊፈቱለት እንደማይችሉ ነገሩት። ማንም ሰው ያንን ማድረግ አይችልም አሉ። ንጉሱ ተናደደ እናም ዳንኤልን እና ጓደኞቹን ጨምሮ በመንግስቱ ያሉትን ሁሉንም ጥበበኞች ሰዎች እገድላለው አለ።
የንጉሱ ጠባቂ ዳንኤልን እና ጓደኞቹን ለመውሰድ ሲመጣ፣ ዳንኤል የህልሙ ትርጉም ምን እንደሆነ ለንጉሱ ለመንገር ይችል ዘንድ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች፣ እንዲሁም ህልሞችን እንደሚያውቅ እና እንደሚያይ ዳንኤል ያውቅ ነበር። ዳንኤል ጓደኞቹ ከእርሱ ጋር እንዲጸልዩ ጠየቃቸው።
እግዚአብሔር የንጉሱን ህልም ለዳንኤል በራዕይ አሳየው እንዲሁም ምን ትርጉም እንዳለው ለዳንኤል አስተማረው። ዳንኤልም እግዚአብሔር ለእርሱ እና ለጓደኞቹ ጸሎቶች መልስ በመስጠቱና ህይወታቸውን በማዳኑ አመሰገነው። ከዚያም የህልሙን ትርጉም ለንጉሱ ለመንገር ሄደ።
ዳንኤል የንጉሱ ህልም ከተራራ በተፈነቀለ ድንጋይ ስለተደመሰሰ ግዙፍ ሀውልት እንደሆነ ተናገረ። ህውልቱ የምድር መንግስታትን ይወክላል። ከተራራ የተፈነቀለው ድንጋይ ምድርን የሚሞላውን የእግዚአብሔር መንግስት ይወክላል። ንጉሱ ዳንኤል እውነቱን እንደተናገረ አውቆ ነበር።