በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ዮሴፍ እና ረሀብ


“ዮሴፍ እና ረሀቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ዮሴፍ እና ረሀቡ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 42–46

ዮሴፍ እና ረሀቡ

ቤተሰቡን አንድ ለማድረግ የአንድ ወንድም እድል

ያዕቆብ ልጆቹን ወደ ግብፅ ሲልክ

በርሀቡ ምክንያት የያዕቆብ ቤተሰብ ተራበ። ስለዚህ ያዕቆብ ልጆቹ ምግብ እንዲገዙ ወደ ግብፅ ላካቸው። ታናሹ ልጁን ቢንያምን በቤት አስቀረው። ልጁን ዮሴፍን ከብዙ ዓመታት በፊት እንዳጣው ሁሉ ቢንያምንም እንዳያጣ ፈርቶ ነበር። ታላላቅ ልጆቹ ዮሴፍን እንደባሪያ እንደሸጡት አላወቀም።

ዘፍጥረት 42፥1–4

ወንድሞቹ ዮሴፍን ምግብ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት

በዚህ ጊዜ ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ ታላቅ መሪ ነበር። በረሃቡ ጊዜ ምግብ የመሸጥ ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር። ወንድሞቹ ከዮሴፍ ጋር ተገናኙ እናም ምግብ እንዲሰጣቸው ጠየቁት። አላወቁትም ነበር።

ዘፍጥረት 42፥5–8

ዮሴፍ እየተናገረ

ዮሴፍ አውቋቸው ነበር፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው አስመሰለ። አባቱ እና ወንድሙ ቢንያም በህይወት መኖራቸውን ለማወቅ ስለቤተሰቦቻቸው ጠየቀ።

ዘፍጥረት 42፥10–14

ወንድማማቾቹ ምግብ ይዘው ሲሄዱ

ከዚያም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ምግብ ሰጣቸው። ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያምን ይዘው ካልሆነ በስተቀር ለተጨማሪ ምግብ ተመልሰው እንዳይመጡ ነገራቸው።

ዘፍጥረት 42፥15–20

ወንድማማቾቹ ወደ ግብፅ እየተመለሱ

ቤተሰቡ ዳግም ምግብ ሲያልቅባቸው፣ ያዕቆብ ከሌሎች ልጆቹ ጋር ቢንያምን ወደ ግብፅ መላክ እንዳለበት ያውቅ ነበር። ያዕቆብ አሁንም ቢንያምን ለመልቀቅ ፈራ። ከወንድማማቾቹ አንዱ የሆነው ይሁዳ ግን ቢንያምን እንደሚጠብቅ ቃል ገባ።

ዘፍጥረት 43፥1–15

ዮሴፍ ወንድማማቾቹ የብር ጽዋ እንደሰረቁ እየከሰሰ

ወንድማማቾቹ ወደ ግብፅ ሲመለሱ ዮሴፍ ቢንያም የብር ጽዋ የሰረቀ እንዲመስል አደረገ። ታላላቅ ወንድሞቹ ተለውጠው እንደሆነ ለማየት ፈለገ። ቢንያምን እንዳይቀጣው ነገር ግን በምትኩ ይሁዳን እንዲቀጣው ይሁዳ ዮሴፍን ለመነው።

ዘፍጥረት 44

ዮሴፍ ማን እንደሆነ እያሳየ

ዮሴፍ ወንድሞቹ እንደተለወጡ በማየቱ ተደሰተ። ቢንያምን እስከመጠበቅ ድረስ ይወዱታል። ስለዚህ በመጨረሻ ዮሴፍ ማን እንደሆነ ነገራቸው።

ዘፍጥረት 42፥21–2445፥1–4

ዮሴፍ ወንድሞቹን እያቀፈ

ለባርነት ቢሸጡትም ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር አለ። ይህ ቤተሰባቸው ከርሀቡ እንዲተርፍ የረዳበት የጌታ መንገድ እንደነበረ ዮሴፍ ተናገረ።

ዘፍጥረት 45፥5–8

ወንድማማቾቹ ወደ ያዕቆብ እየሮጡ

የዮሴፍ ወንድሞች ወደአባታቸው ወደያዕቆብ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ያዕቆብ መላ ቤተሰቡን ወደ ግብፅ አዛወረ።

ዘፍጥረት 45፥24–2846፥1–26

ዮሴፍ እና ያቆብ በግብፅ፣ ፈረዖን እያየ

ፈረዖን የያቆብን ቤተሰብ ተቀበላቸው። የተትረፈረፈ ምግብ ያገኙ ዘንድ መሬትና እንስሳት ሰጣቸው። የያዕቆብ ቤተሰብ ለረዥም ዘመን በሰላም ኖሩ።

ዘፍጥረት 45፥16–23