በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኤልሳዕ እና የጌታ ሰራዊት


“ኤልሳዕ እና የጌታ ሰራዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ኤልሳዕ እና የጌታ ሰራዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

2 ነገሥት 6

ኤልሳዕ እና የጌታ ሰራዊት

የጌታ የእሳት ሠረገሎች

ወታደሮች ከተማውን ከበው

ሶርያውያን እስራኤላውያንን አይወዷቸውም ነበር። የሶሪያው ንጉሥ ነቢዩ ኤልሳዕን ለመያዝ ሠራዊቱን ላከ። በምሽትም ሠራዊቱ ኤልሳዕ የነበረበትን ከተማ ከበበ።

2 ነገሥት 6፥8–14

ኤልሳዕና አገልጋዩ የሶሪያን ሠራዊት እየተመለከቱ

የኤልሳዕ ወጣት አገልጋይ ከእንቅልፉ ተነሳ እና የሶሪያን ሰራዊት ተመለከተ። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኤልሳዕን ጠየቀ። ኤልሳዕ ወጣቱ እንዳይፈራ ነገረው። ለእነርሱ የሚዋጉት ሰራዊት ከእነርሱ ጋር ከሚዋጉት ሰራዊት እንደሚበልጡ ተናገረ።

2 ነገሥት 6፥15–16

የሰማይ ሰራዊት በእሳት ሠረገሎች

ኤልሳዕ ያየውን ለወጣቱም እንዲያሳይ ኤልሳዕ ጌታን ጠየቀ። እነርሱን ለመጠበቅ ፈረሶች እና የእሳት ሰረገሎች ያሉት ሰማያዊ ሠራዊትን ጌታ አሳየው። የሶርያ ጦር በጌታ ኃይል ታውሮ ነበር። ከዚያም በኋላ እነርሱ ከእስራኤላዊያን ጋር በመዋጋት አልቀጠሉም።

2 ነገሥት 6፥17–23