በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነህምያ


“ነህምያ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነህምያ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ነህምያ 1–2፤ 4፤ 6

ነህምያ

የኢየሩሳሌምን ግንብ ዳግም መገንባት

ነህምያ፣ ንጉስ እየተመለከተ

ነህምያ በፋርስ ይኖር የነበረ አይሁዳዊ ነበር። የንጉሱ ታማኝ አገልጋይ ነበር። አንድ ቀን ነህምያ በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁዶች እየተሰቃዩ እንደነበር ሰማ። ኢየሩሳሌምን የሚጠብቁት ግንቦች ተደምስሰው ነበር እና ዳግም አልተገነቡም ነበር። ኢየሩሳሌም አደጋ ላይ ነበረች። ነህምያ ጾመ እንዲሁም የጌታን እርዳታ ለማግኘት ጸለየ።

ነህምያ 1

ንጉሱ ስለግንቡ ነህምያን እያናገረው

ነህምያ ለምን እንዳዘነ ንጉሱ ጠየቀው። በኢየሩሳሌም ስለነበረው አደጋ ለንጉሱ ነገረው። ንጉሱ ማገዝ እንደሚችል ተናገረ። ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም ስለመሄድ እና ግንቡን ዳግም ስለመገንባት ጠየቀ። ንጉሱ ነህምያን መሪ አደረገው እንዲሁም ያስፈልጉት የነበሩትን ቁሳቁሶች ሰጠው።

ነህምያ 2፥2–8

ነህምያ ግንብ እየገነባ፣ ጠላቶች እየተመለከቱ

ነህምያ እና አይሁዶች የኢየሩሳሌምን ግንብ ዳግም መገንባት ጀመሩ። ነገር ግን ጠላቶቻቸው አፌዙባቸው እንዲሁም ሊያስቆሟቸው ሞከሩ።

ነህምያ 2፥17–20

ህዝቡ በነህምያ ላይ ሲያፌዙ

ነህምያ ከተማውን ለቆ እንዲሄድ ለማታለል ሞከሩ። ነገር ግን ነህምያ አልሄደም። በጌታ ታምኖ ነበር። ታላቅ ስራን እየሰራ ነበር።

ነህምያ 6፥2–4

ነህምያ ተገንብቶ በተጠናቀቀ ግንብ ላይ ቆሞ

ህዝቡ እንዳይፈሩ ነህምያ ነገራቸው። ደህንነቱን ለመጠበቅ በግድግዳው ላይ ጠባቂዎችን አደረጉ። አይሁዶቹ ግንቡን መገንባት ቀጠሉ። ጌታ ለአይሁዶች ጥንካሬን ሰጣቸው እናም ግንቡን በ 52 ቀናት ውስጥ አጠናቀቁ። ኢየሩሳሌም ዳግም ከአደጋ ነፃ ሆነች።

ነህምያ 4፥6–156፥5–9፣ 15–16