በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ


“ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

ዘፍጥረት 39–41

ዮሴፍ በግብፅ ውስጥ

ባሪያ የነበረው መሪ ሆነ

ዮሴፍ ለጲጥፋራ ተሸጠ

ዮሴፍ ጲጥፋራ ለሚባል ሰው እንደ ባሪያ ተሸጠ። ጲጥፋራ የግብፅ መሪ ለሆነው ፈርዖን ይሰራ ነበር። ጌታ ዮሴፍን እንደረዳው ጲጥፋራ ማወቅ ችሎ ነበር። ዮሴፍን አመነው እናም በቤቱና በንብረቱ ሁሉ ላይ አዛዥ አድርጎ ሾመው።

ዘፍጥረት 39፥1–6

ዮሴፍ የጲጥፋራን ሚስት አይሆንም ሲላት

የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን ትወደው ነበር። ዮሴፍ ከእሷ ጋር የጌታን ትእዛዛት እንዲጥስ ትፈልግ ነበር። ዮሴፍ አይሆንም አላት።

ዘፍጥረት 39፥7–10

ዮሴፍ ከጲጥፋራ ሚስት ሮጦ ሲሸሽ

የጲጥፋራ ሚስት አልሰማ አለች፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሮጦ ሸሸ። በዮሴፍ ተናደደች።

ዘፍጥረት 39፥11–12

የጲጥፋራ ሚስት ጲጥፋራን ስታናግር

የዮሴፍን ልብስ ቁራጭ ለጲጥፋራ አሳየችው። ስለዮሴፍ ጲጥፋራን ዋሸችው። ጲጥፋራ ዮሴፍን እስር ቤት አስገባው።

ዘፍጥረት 39፥13–20

ዮሴፍ በእስር ቤት ውስጥ

ዮሴፍ ከቤተሰቡ ተለይቶ ነበር። ባሪያ ሆኖ ነበር፤ እንዲሁም አሁን እስረኛ ሆነ። ነገር ግን ጌታ ዮሴፍን አሁንም ረዳው። ዮሴፍ ተስፋ አልቆረጠም። በዮሴፍ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር እንዲያይ ጌታ የእስር ቤቱን ጠባቂ ባረከው። ጠባቂው እርሱን ማመን ጀመረ፤ ስለዚህ ዮሴፍን በሌሎች እስረኞች ላይ ሾመው።

ዘፍጥረት 39፥21

ዮሴፍ የእስረኞችን ህልሞች ሲፈታ

ዮሴፍ እንጀራ አበዛ እና ጠጅ አሳላፊ በመሆን ለፈርዖን ሲሠሩ የነበሩ ሁለት እስረኞችን አገኘ። ሁለቱም ያልተለመዱ ህልሞችን አዩ። በጌታ ኃይል አማካኝነት ዮሴፍ ህልማቸው ምን ማለት እንደሆነ አብራራ። የጠጅ አሳላፊው ህልም ትርጉም ጠጅ አሳላፊው ነፃ ይሆናል ማለት ነበር። ከሦስት ቀናት በኋላ እንደገና ለፈርዖን እንዲሠራ ተፈታ።

ዘፍጥረት 39፥22–2340፥1–21

ፈርዖን ተቆጥቶ

አንድ ቀን ፈርዖን ባያቸው ህልሞች ተቆጣ። ህልሙ ምን ማለት እንደሆነ ማንም ሊነግረው አልቻለም።

ዘፍጥረት 41፥1–8

ጠጅ አሳላፊው ፈርዖንን ሲያናግር

ከዚያም ጠጅ አሳላፊው ዮሴፍ ህልሞችን ማስረዳት እንደሚችል አስታወሰ።

ዘፍጥረት 41፥9–13

ዮሴፍ የፈርዖንን ህልሞች ሲፈታ

ዮሴፍ የፈርዖንን ህልሞች ለማብራራት ከእስር ቤት ወጣ። ዮሴፍ የህልሞቹ ትርጉም ግብፅ ለሰባት ዓመት በምግብ ትትረፈረፋለች ከዛም ተከትሎ ለሰባት አመት በምግብ እጥረት ረሃብ ይሆናል ማለት ነው አለ። በመልካሞቹ ዓመታት ግብፅ ተጨማሪ ምግብን ማጠራቀም እንዳለባት ዮሴፍ ለፈርዖን ነገረው።

ዘፍጥረት 41፥14–36

ዮሴፍ የምግብ ክምችት ለፈርዖን ሲያሳይ

ዮሴፍ ስለህልሙ የተናገረው እውነት መሆኑን ፈርዖን አወቀ። ዮሴፍን ከእስር ቤት ነፃ አወጣው እንዲሁም ዮሴፍን በግብፅ ውስጥ ታላቅ መሪ እንዲሆን አደረገው። ለሰባት ዓመታት፣ ግብፅ ተጨማሪ ምግብ እንድታከማች ዮሴፍ ረዳ።

ዘፍጥረት 41፥37–53

በግብፅ ሰዎች እየተጓዙ

ከዚያም ረሀቡ መጣ። በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ምንም ምግብ ማምረት አልቻለም ነበር። ሰዎች ዮሴፍ ያከማቸውን ምግብ ለመግዛት ወደ ግብፅ ተጓዙ። በዮሴፍ ምክንያት ግብፃውያኑ ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን ከረሃብ ለማትረፍ የሚያስችላቸውን በቂ ምግብ አከማቹ።

ዘፍጥረት 41፥54–57