“የዮሴፍ በመንፈስ የተነሳሱ ህልሞች፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“የዮሴፍ በመንፈስ የተነሳሱ ህልሞች፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
የዮሴፍ በመንፈስ የተነሳሱ ህልሞች
እርስ በእርስ ለመዋደድ የሚደረግ የቤተሰብ ትግል
ራሔል እና ያዕቆብ ወንድ ልጅ ለመውለድ ለብዙ ዓመታት ሲጸልዩ ነበር። ዮሴፍ በተወለደ ጊዜ ጌታ ጸሎታቸውን መለሰ። ዮሴፍ የያዕቆብ ተወዳጅ ልጅ ነበር እናም ለዮሴፍ ልዩ ቀሚስ ሰጠው። የያዕቆብ 10 ታላቅ ወንድ ልጆችም ቀኑ።
ዮሴፍ ወደ 17 ዓመት ገደማ ሲሆነው ከወንድሞቹ ጋር በሜዳ ላይ እህል እየሰበሰበ በመንፈስ አነሳሽነት ህልም አየ። የዮሴፍ እህል ጥቅል ከፍ ብሎ ቆመ። የወንድሞቹ እህል ጥቅሎች ግን ለዮሴፍ ጥቅል ሰገዱ። ዮሴፍ ስለህልሙ ለወንድሞቹ ሲነግራቸው ተቆጡ።
ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ በመንፈስ አነሳሽነት ሌላ ህልም አየ። በዚህ ህልም ፀሀይ፣ ጨረቃ እና 11 ከዋክብቶች ለእርሱ ሰገዱለት። ዮሴፍ ስለህልሙ ለቤተሰቡ ነገራቸው። ይህ ህልም ዮሴፍ በቤተሰቡ ላይ እንደሚመራ አይነት መሰለ። የዮሴፍ ወንድሞች በእርሱ ይበልጥ ተቆጡ። የእሱን ህልሞች አልወደዷቸውም።
አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች በጎቹን ሊመግቡ ከቤታቸው ርቀው ሄደው ነበር። ያዕቆብ ስለእነርሱ ጤንነት እንዲጠይቅ ዮሴፍን ላከው።
አንዳንድ የዮሴፍ ወንድሞች ሊገድሉት ፈለጉ። የዮሴፍን ቀሚስ ወሰዱና እርሱን ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት።
ዮሴፍ በጉድጓዱ ውስጥ ሳለ ወንድሞቹ ወደ ግብፅ የሚሄዱ መንገደኞችን ተመለከቱ። ወንድሞቹ ዮሴፍን ለመንገደኞቹ በ20 ብር ባሪያ አድርገው ለመሸጥ ወሰኑ።
ከዚያም የዮሴፍ ወንድሞች የፍየል ደም በቀሚሱ ላይ አደረጉ። ወንድሞቹ ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ሄደው ቀሚሱን አሳዩት። ያዕቆብን ዋሹትና የዱር እንስሳት ዮሴፍን እንደገደሉ ነገሩት።
ያዕቆብ ዮሴፍ የሞተ ስለመሰለው አለቀሰ።
ነገር ግን ዮሴፍ አሁንም በህይወት ነበር። ከአገሩ ርቆ በግብፅ ውስጥ እንደባሪያ ይኖር ነበር።