“የባቢሎን ግንብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]
“የባቢሎን ግንብ፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
ከጎርፉ በኋላ ህዝቡ ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ጀመሩ። አንዳንዶቹ የእግዚአብሔርን እቅድ አላመኑም። እግዚአብሔርን ሳይጠይቁ ወደሰማይ ለመድረስ ግንብ መገንባት ጀመሩ። የባቢሎን ግንብ የሚባል የሐሰት ቤተመቅደስ ነበር።
ዘፍጥረት 11፥4፣ 9
ሰዎች ግንቡን በመሥራታቸው እግዚአብሔር አልተደሰተም። እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን ደባለቀ። እርስ በእርሳቸው መግባባት ባለመቻላቸው ምክንያት ግንቡን መገንባት ማቆም ነበረባቸው።
ዘፍጥረት 11፥6–8፤ ኤተር 1፥33
ጌታ ህዝቡን በተናቸው እንዲሁም በምድር ዙሪያ ሁሉ እንዲኖሩ ላካቸው።
ዘፍጥረት 11፥9