በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ንጉስ ዳዊት


“ንጉስ ዳዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ንጉስ ዳዊት፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

1 ሳሙኤል 18–19፤ 31፤ 2 ሳሙኤል 1፤ 5፤ 11–12

ንጉስ ዳዊት

የንጉስ ትግል

ንጉሥ ሳኦል እና ዳዊት ከተማን እየተመለከቱ

የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ንጉሥ ሳኦል ዳዊት ጎልያድን ድል በማድረጉ ተደንቆ ነበር። ሳኦል ዳዊትን በሠራዊቱ ላይ መሪ አደረገው።

1 ሳሙኤል 18፥5

ዳዊት

ዳዊት ጌታን ይወድ ነበር እናም ሁልጊዜ ትክክለኛውን ለማድረግ ይፈልግ ነበር። የእስራኤል ህዝብም ዳዊትን ይወዱት ነበር።

1 ሳሙኤል 18፥ 6–7

ሳኦል እንደተናደደ ሲታይ

ሳኦል በቅናት ተነሳ እናም ዳዊትን ለመግደል ሞከረ። ነገር ግን ዳዊት ጌታን ተከተለ፣ እናም ጌታ እርሱን ከሳኦል ጠበቀው።

1 ሳሙኤል 18፥6–1619፥1

የእስራኤላውያን የቀብር ሥነ ሥርዓት

እስራኤላውያን ብዙ ጦርነቶችን ተዋጉ። አንድ ቀን ሳኦል እና ልጆቹ በጦርነት ተገደሉ። ዳዊት ይወዳቸው ነበር እናም ስለመሞታቸው ሲሰማ በጣም አዘነ። አሁን እስራኤላውያን አዲስ ንጉስ ያሰፈልጋቸው ነበር። ጌታም ዳዊት ንጉስ እንዲሆን መረጠው። ሕዝቡም ደስተኛ ነበሩ።

1 ሳሙኤል 31፥2–62 ሳሙኤል 1፥11–125፥1–5

ዳዊት ሰራዊትን ሲመራ

ጌታ ንጉስ ዳዊትን ባረከው እናም መራው። በጌታ እርዳታም የዳዊት ሰራዊት ጠላቶቻቸውን አሸነፉ።

2 ሳሙኤል 5፥6–10፣ 17–25

ዳዊት ወይን ሲበላ

አንድ ቀን ዳዊት ወደ ጦርነት መሄድ በነበረበት ጊዜ በቤት ቀረ። አንዲት ቆንጆ ሴትን አየ። ስሟም ቤርሳቤህ ነበር፣ እናም ዳዊት እርሷን ለማግባት ፈለገ። ነገር ግን እርሷ ኦርዮ ከሚባል ከዳዊት ሰራዊት ወታደር ጋር የተጋባች ነበረች።

2 ሳሙኤል 11፥1–3

ዳዊት ከኦርዮ ጋር ሲነጋገር

ዳዊት ቤርሳቤህን ለማግባት ፈለገ፣ ስለዚህ ባለቤቷ ኦርዮ እንዲገደል በጣም አደገኛ ወደሆነ ጦርነት ላከው።

2 ሳሙኤል 11፥4–17

ዳዊት እና ቤርሳቤህ

ወዲያውኑም ኦርዮ በጦርነት ውስጥ እንደሞተ ዳዊት ሰማ። ዳዊት ሰራተኞቹ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ እንዲያመጧት ላከ፣ እናም አገባት።

2 ሳሙኤል 11፥24፣ 26–27

ናታን ከዳዊት ጋር ሲነጋገር

ነገር ግን ጌታ ዳዊት ባደረገው አልተደሰተም ነበር። ጌታ ነቢዩን ናታንን ሀጢያቱ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለዳዊት እንዲነግር ላከው። ዳዊት በኦርዮ እና በቤርሳቤህ ላይ ስላደረገውም ነገር በጣም አዘነ። ከጌታ ምህረት ለማግኘት ጸለየ እንዲሁም ጾመ።

2 ሳሙኤል 11፥2712፥1–13