Scripture Stories
ነቢዩ ሳሙኤል


“ነቢዩ ሳሙኤል፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች [2022 (እ.አ.አ)]

“ነቢዩ ሳሙኤል፣” የብሉይ ኪዳን ታሪኮች

1 ሳሙኤል 2–3

ነቢዩ ሳሙኤል

በጌታ የተጠራ ልጅ

ምስል
ዔሊ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር

ለብዙ ጊዜያት፣ እስራኤላውያን የሚመራቸው የጌታ ነቢይ አልነበራቸውም። በምትኩም፣ መሣፍንት እስራኤልን ለብዙ አመታት ገዙ። በዚህ ጊዜ ሐና ትንሹ ልጇን ሳሙኤልን ከእስራኤል ካህን እና ፈራጅ ከሆነው ዔሊ ጋር እንዲኖር አመጣች። ሳሙኤል ዔሊን በቤተመቅደስ ውስጥ ረዳው።

1 ሳሙኤል 2፥11፣ 18፣ 263፥1

ምስል
የዔሊ ወንድ ልጆች እቃዎችን እየሰረቁ

የዔሊ ሁለቱ ወንድ ልጆችም በቤተመቅደስ ውስጥ ያገለግሉ ነበር፤ ነገር ግን ለጌታ የተሰጡትን መስዋዕቶች ይሰርቁ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ለዔሊ ቅሬታቸውን አሰሙ፣ ነገር ግን ዔሊ አልቀጣቸውም ነበር።

1 ሳሙኤል 2፥12–17፣ 22–23

ምስል
ሳሙኤል

አንድ ምሽት ሳሙኤል አንድ ድምፅ ሲጠራው ሰማ። ይህም ዔሊ መስሎት ነበር፣ ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እርሱ ሄደ። ነገር ግን ዔሊ አልጠራውም ነበር። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው።

1 ሳሙኤል 3፥3–5

ምስል
ሳሙኤል ከዔሊ ጋር ሲነጋገር

ሳሙኤል ድምጹ ለሁለተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። ወደ ዔሊ ሂዶ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። ነገር ግን ዔሊ አልጠራውም ነበር። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው።

1 ሳሙኤል 3፥6

ምስል
ዔሊ ከሳሙኤል ጋር ሲነጋገር

ሳሙኤል ድምጹ ለሶስተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። ወደ ዔሊ ሂዶ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። በዚህ ጊዜ፣ ዔሊ ለሳሙኤል የሚናገረው ጌታ እንደሆነ ተረዳ። ዔሊ ወደ መኝታው እንዲመለስ ለሳሙኤል ነገረው። ጌታ እንደገና ከጠራው፣ ሳሙኤል እንዲያደምጥ ዔሊ ነገረው።

1 ሳሙኤል 3፥8–9

ምስል
ሳሙኤል ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር

ሳሙኤል ድምጹ ለአራተኛ ጊዜ ሲጠራው ሰማ። በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ጌታ እንዲናገር ጠየቀ እና እርሱም አዳምጣለሁ አለ። ጌታም ዔሊ ኃጢያተኛ ልጆቹን በቤተመቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ መፍቀዱ ትክክል እንዳልሆነ ለሳሙኤል ነገረው። የዔሊ ቤተሰብ በዚያ ውስጥ እንደገና ለማገልገል አይፈቀድላቸውም።

1 ሳሙኤል 3፥10–14

ምስል
ሳሙኤል እና ዔሊ ሲነጋገሩ

በሚቀጥለው ቀን፣ ዔሊ ጌታ ምን እንዳለው ሳሙኤልን ጠየቀው። ሳሙኤልም ነገረው። ዔሊ ጌታ በሳሙኤል በኩል እንደሚናገር አወቀ።

1 ሳሙኤል 3፥15–18

ምስል
ሳሙኤል ሰዎችን ሲመለከት

ዜናውም በእስራኤል ምድር ሁሉ ተሰራጨ። ህዝቡም ጌታ ሳሙኤልን እንደ ነቢዩ እንደመረጠ አወቁ።

1 ሳሙኤል 3፥19–20

አትም